TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የማረጋጋት ስራ እየሰራሁ ነው" - መከላከያ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ግጭት ተከስቶ በነበረባቸው በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች መካከል በመግባት የማረጋጋት ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚንስቴር የማረጋጋት ስራውን በመስራት ላይ የሚገኝው የአማራ ክልል መንግስት ባቀረበለት ጥሪ መሰረት እንደሆነ ገልጿል፡፡

አሁን ላይ አካባቢዎቹ #እየተረጋጉ ቢመጡም አልፎ አልፎ በመንገድ ዳርቻዎች ላይ #የተኩስ ልውውጦች አሉ ነው የተባለው፡፡ የተኩስ ልውውጡ የሚሰማው በገጠራማ አካባቢዎች መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

አካባቢዎቹ ሰፊ እንደመሆናቸው በብቃት ለመቆጣጠር #ተጨማሪ ሀይል ወደ ስፍራዎቹ #እየገባ መሆኑን ሚንስቴሩ ይፋ አድርጓል፡፡

ተዘግተው ያሉ የደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረ ሲናና እና ደብረ በርሃን መንገዶችን የማስከፈት ስራ #እንደሚከናወንም ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ-#ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢንተርን ሃኪሞች እና በተለያዩ የጤና ባለሙያዎች በሚነሱ ጥያቄዎችና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ሀገር አቀፍ ውይይት እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከሁሉም የጤና ባለሙያዎች ፣ ከሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ከክልል መንግስታት ፣ ከሙያ ማህበራትና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የሚዘጋጅ ውይይት መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን አስታውቀዋል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱት የውይይት መድረኮች ወደ መፍትሄ ሃሳቦች ለማስቀመጥ የሚያስችሉ መሆናቸውን ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት፡፡ እነዚህ መድረኮች በቅርብ በየደረጃው ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ክፍት እንዲሚሆኑ ነው የተነገረው፡፡

#ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከአማራ ክልል፣ ከኦሮሚያ ምስራቅ ወለጋ ዞኖችና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው የመመለሱ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል ተባለ።

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሼና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር፥ በምስራቅ ወለጋ ዞን የተጠለሉ ከ69 ሺህ በላይ ዜጎችን በሳምንቱ መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ወደ መጡበት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ በቀለ ገልጸዋል።

ተፈናቃዮቹ ወደ መጡበት ሲመለሱም በመኸር እርሻ እንዲሳተፉ ለማድረግ የሚያስችል ድጋፍ፥ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመሆን ለማከናወን ዝግጅት ተደርጓልም ብለዋል።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተጠልለው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ መኖሪያቸው ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑም ተገልጿል።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአደጋ መከላከል ጽህፈት ቤት ተወካይና የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ቡድን መሪ አቶ አብደላ ኑር፥ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው ተመልሰው የእርሻ ስራቸውን ማከናወን እንዲችሉ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

የወደሙ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባትም እስካሁን ከ17 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮችን ወደ ሁለቱም አካባቢዎች መመለስ ተችሏል ብለዋል። በአካባቢዎቹ በነበረው የፀጥታ ችግር የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባርም እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

በአካባቢዎቹ ዳግም የጸጥታ ችግር እንዳይከሰትም እየተከናወኑ ያሉ የህዝብ ለህዝብ የሰላም መድረኮችም ቀጣይነት እንደሚኖራቸው ሃላፊዎቹ ገልጸዋል።

Via #ፋና_ብሮድካስት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
/የአክሱም ዩኒቨረስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፀሐይ አስመላሽ/ የተናገሩት፦
.
.
"ከአክሱም ከተማ ነዋሪዎች፣ ከሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን ውይይት ተጀምሯል፤ የተደረገው ውይይት ተማሪዎችን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል"

"በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን ለህግ ለማቅረብ ፖሊስ ምርመራ የጀመረ ሲሆን ህብረተሰቡም መረጃ በማቅረብ ትብብር እያደረግ ይገኛል"

"የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከመሰል ድርጊቶች ራሳቸውን በማራቅ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመጡበት ዓላማ ሊቆሙ ይገባል"

Via #ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
/የደብረማርቆስ ዩኒቨረስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ/ የተናገሩት፦
.
.
"ተማሪዎች ከየትኛውም የፖለቲካ እንቅሰቃሴዎች ራሳቸውን ነፃ በማድረግ ለያዙት #ዓላማ ተገዥ እና የመፍትሄ አካል ሊሆኑ ይገባል"

"የተለያዩ አካላት ድርጊቱን #ከማውገዝ ይልቅ #ለፖለቲካ ጥቅም ለመጠቀም ሞክረዋል ብለዋል"

"ከከተማው ነዋሪ ጋር በተከታታይ የተደረጉ ውይይቶች ተማሪዎች #ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ አስችሏል"

"መሰል ድርጊቶች እንዳያጋጥሙ አሁንም ከአካባቢው ማህበረስብ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል"

Via #ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የአሸንዳ በዓል ለሰላምና አንድነታችን"

የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የዘንድሮውን የአሸንዳ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ። የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ ብርክቲ ገብረመድህን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፥ በዓሉ ከነሐሴ 16 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመቐለ ከተማና በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ብለዋል። የዘንድሮው በዓል “የአሸንዳ በዓል ለሰላምና አንድነታችን" የሚል መሪ ሃሳብ እንዳለውም ተናግረዋል።

Via #ፋና_ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia