TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

በኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ላይ የተደረገው ማስተካከያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 13/2016 ዓ.ም መጽደቁ ይታወሳል።

ይህ ተከትሎ  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት የታሪፍ ማሻሻያው ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሽፈራው ተሊላ የታሪፍ ጭማሪው የደንበኞችን የኃይል የአጠቃቀም መሰረት ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም፦

የቤት ደንበኞች፤ የንግድ ተቋማት፤ ዝቅተኛ ኢንዱስትሪ፤ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ እንዲሁም የመንገድ መብራት ተጠቃሚዎች በሚል መከፋፈሉን አስታውቀዋል።

የቤት መብራት ተጠቃሚዎችን በተመለከተ " እንደ አጠቃቀማቸው አሁን ከሚከፍሉት እና ጭማሪ ከተደረገበት መካከል ያለውን ልዩነት ሲከፍሉ እንደ አጠቃቀማቸው ድጎማ ተደርጓል " ሲሉ አስረድተዋል።

ድጎማው ምን ይመስላል ?

50kW በታች ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 75 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፤

ከ50kW - 100KW ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 40 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፤

200kW - 300 Kw ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 4 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፤

400kW - 500 KW የሚሆነውን ማሻሻያውን ያለምንም ድጎማ ይከፍላሉ

ከ500kW በላይ የሚሆነውን ደግሞ ሌላውን ተጠቃሚ የሚደግፉበት የጎንዮሽ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ ይደረጋል።

የአከፋፈሉ ሁኔታ ምን ይመስላል ?

እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ ይህ የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያው (የተጨመረው 6 ብር) የሚከፈለው በአንድ ጊዜ ሳይሆን በ16 ዙር በሚደረግ የሂሳብ ማስተካከያ [ከመስከረም 1 /2017 ጀምሮ] በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

ኢንጂነር ሽፈራው ይሄንን ሲያስረዱ 50KW የሚጠቀሙ ደንበኞች አሁን የሚከፍሉት 27 ሳንቲም እንደሆነ ገልጸው ከመስከረም ጀምሮ የሚከፍሉት 35 ሳንቲም ይሆናል ብለዋል።

ከአራት ዓመታት በኋላ ደግሞ [በ16 ዙሮች በሚደረግ ማስተካከያ] 1.56 ብር መክፈል ይጀምራሉ ሲሉ አስረድተዋል።

ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ያለው ጫና ተጠንቷል ወይ ?

ይህ ጥያቄ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ሲሆን በሰጡት ምላሽ በዚህ ላይ ጥናት መደረጉን ጠቅሰው ይህም #ከአራት_ዓመት በኋላ የሚኖረው ተጽዕኖ 2 በመቶ እንደሆነ አንስተዋል።

" ከአከራይ ተከራይ ጋር ያለው ተጽዕኖም በጣም አነስተኛ ነው፤ የሚያጣላቸው ነገር አይኖርም " ሲሉ አስረድተዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለው ይህ የታሪፍ ማሻሻያው በዋነኛነት የወጣበትን ወጪ ለመሸፈን (A cost reflective tariff) መሰረት ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

#ማብራሪያ: ከላይ የተያያዘው ሰንጠረዥ ድጎማ የተደረገበት የሂሳብ ታሪፍ ሲሆን። በዓመት 4 ጊዜ በ4 ዓመት ደግሞ 16 ጊዜ የሚተገበር የሂሳብ ማስተካከያ የያዘ ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia