TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትዝብት‼️

በተወሰነ መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ መተው የሚሰሩ #ቻይና_የኮንስትራክሽን_ድርጅት በአገራችን ሰራተኞች ላይ የሚያሳዩት #ንቀት እና ዝቅተኛ የክፍያ መጠን የተወሰነ ፅፈህ ነበር።

እኔም ይህን አሳብ እጋራለው። እነኚህ ቻይኖች ህዝቡ ከሚያወራው የስራቸው ጥራት ማነስ እና መንግስት ያስቀመጣቸውን ተቆጣጣሪዎችን በሙስና ማጨማለቅ ውጪ ደግሞ የሰራተኛ ክፍያ አነስተኛ መሆን፣ የሰራተኛ አያያዝ ፣የሰራኛ የመብት ጥሰት፣ የሰራተኛ አስተነጋገድ ሁኔታ፣የደሞዝ ክፍያ ሰሌዳ፣ ስራ ላይ የተጎዳን (በስራ ቦታ የተጎዳ)፣ ሰራተኛን አያያዝ፣ሰራተኛ ሲቀነስ ወይም ሲቀነስ የሚከፈል አገልግሎት ክፍያ መከልከል በተጨማሪ ንዑስ ተቋራጮች (sub contractor) አያያዝ፣ አከፋፈል፣ የስራ አለካክ ላይ በጣም ችግር አለ!!!

እኔ sub contractor ነኝ ምሰራው ሀዋሳ ጩኮ መንገድ ስራ ላይ ነው። ይህን የሚሰራው sino hydro የኮንስትራክሽን ድርጅት መንገድ ስራውን የያዘው። ይህ ድርጅት ከላይ ከጠቁስክልህ ችግር ውጪ ሚሰራውን መንገድ ስራ በሚሰራበት ወቅት በጣም መንገድ ለመንገዱ የሚጎዳ በጣም አፀያፊ ስራ እየሰሩ ነው።

ለምሳሌ፦

1. ከዚህ በፊት የነበረውን ተነሺ አስፋልት ያነሱ እና እንደ ውሉ መጣል ነበረበት እነሱ ከዚህ በፊት የተነሳውን አስፋልት ከአዲስ ጋር ደባልቀው አስፋልቱን እየሰሩ ነው።

2. የመሬት ስራው በሚሰራበት ወቅት የመሬት ስራው ቆረጣ አለው። አላስፈላጊ የሆነውን የተቆፈረውን አፈር እንደ መጣለል Re use ነው ሚያረጉት። ይህ አስፋልት ከዚህ በፊት በህንዶች የመንገድ ስራ ተቋራጮች ተይዞ የነበረ መንገድ ስራ ነበር ነገር ግን ስንት ያገሬ ንብረት ወጥቶበት በጥራት ምክንያት ህንዶቹን ተባረዋል። ከዚያም እነኚህ የመጡት።

3. የአስፈልቱ ውፍረት እንደሰማነው 5 ሳሜ ነው። ፀግሽ ታምነኛለህ 3 ሳሜ ውፍረት ያለው አስፋልት የተሰራ እጅግ በጣም ብዙ ነው።

4. አስፋልት ከመሰራቱ በፊት የነበረው የመሬት ስራ በግርድፉ ሲታይ ሁለት ነገር አለው። አንደኛ sub base እና base course። ሰብ ቤዙ እንዳልኩ አንዳንድ ቦታ የተቆፈረውን መልሰው ይጠቀማሉ። ይህ ደግሞ ለአስፋልቱ መሰረት ስለሆነ ይህ sub base ደረጃ ሚጠብቀው ስላልሆነ የላይኛውን አስፋልት እድሜ እንዳይኖረው ዋነኛ ምክንያት ነው። ሁለተኛው base course ደግሞ ተመርጦ የመጣውን የአፈር አይነት ካለቀ ቡኃላ የሚደረግ የተቀመመ የተፈጨ የጠጠር አይነት ነው። ይህ ጠጠር በትንሹ ውፍረት ከ 30 ሳሜ ማነስ የለበትም። ቻይኖቹ መንገዱን ሲሰሩት ከስር የሚደረገውን አፈር ከመጠን በላይ ያደርጉ የምትደረገውን የጠጠር ውፍረት ከ10–20 ሳሜ ያደርጉት እና ማውጣት ያለባቸውን ሳያወጡ አገራችንን "ድህነት" ላይ ጥለው የተከለከለ ወንጅል ትርፍ ያጋብዛሉ።

ይህ ሁሉ ሲሆን ማንም ምንም አላለም ልትል ትችላለህ። ለሆዳቸው ያላደሩ ተቆጣጣሪዎች ባለሙያተኞች አሉ ነገር ግን እነኚህ ሰዎች ቻይኖቹ ከጣሊያናዊው ሽማግሌ ተቆጣጣሪ ጋር በመመሳጠር ባለው መብት ተጥቅሞ ተባረዋል። እነኚህ ሰዎች ሰሚ ቢያገኙ ሊናዘዙ ይችላሉ። ፀግሽዬ ከተጨመረው ውጪ መንገዱ የተያዘው በ44 USD ነው። በኛ ምን ያህል እንደሚመጣ ላንተ ልትወውና ይሄ ብር መንገስት በዚህ የዶላር ህጥረት ለስንት ችግሩ ማስታገሻ ያደርገው ነበር!!!
አደራ አደራ አደራ ፀግሽ ለሚመለከተው!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ አድርጉ‼️

#ከኢትዮጵያ ወደ #ቻይና የምትሄዱ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሰዎች ይህን እቃ እዛ ላለ ሰው አድርስልኝ/አድርሺልኝ ሲሏችሁ በደንብ የሚላከውን ነገር ፈትሹ። ቻይና ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ለመረዳት እንደቻልነው አንዳንዶች በሚላከው እቃ ውስጥ አደንዛዥ እፆችን በመጨመር እንደሚልኩ ጠቁመዋል። በተለይ ምግብ ነክ ነገሮች ውስጥ የአደንዛዥ እፆችን በመክተት ይልካሉ። ወዳጆቻችን ሳታውቁት በወንጀል እንዳትጠየቁ ቅድመ ጥንቃቄ አድርጉ።

ለማሳያነት፦ ባለፈው ሳምንት አንዲት ኢትዮጵያዊ በኤርፖርት ስትፈተሽ ያልተገቡ ነገሮችን ይዛ በመገኘቷ ለእስር ተዳርጋለች (ሰው አድርሽልኝ ብሏት) እንዲሁም አንድ ኢትዮጵያዊ ከወራት በፊት በተመሳሳይ ለእስር ተዳርጓል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮዽያ አየር መንገድ #ቻይና ስሪት የሆኑ ሲ919 ሞዴል አውሮፕላኖችን ለመጠቀም የሚያስችለውን ምክክር እያደረገ እንደሆነ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያምን ጠቅሶ ዥንዋ ዘግቧል። ሲ919 ቻይና ስሪት የመንገደኞች አውሮፕላንን ጥቅም ላይ ለማዋል አየር መንገዱ ኮሚቴ አቋቁሞ ከሚመለከታቸው የቻይና ኩባንያዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ እንደሆነም ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል። ኮማክ (COMAC) በተሰኘ ምህፃረ ቃል የሚታወቀው የቻይና የንግድ አውሮፕላኖች አምራች ኮርፖሬሽን የምርት ውጤት የሆኑትን አውሮፕላኖች ወደ ኢትዮዽያ በማምጣት ሃገሪቷን የአፍሪካ የቻይና አቪዬሽን ማዕከል የማድረግ ሃሳብ እንዳለ ዋና ስራ አስፈፃሚው መግለፃቸውን መረጃው ጠቁሟል። አየር መንገዱ በቻይናና አፍሪካ መካከል የሚኖረውን ግንኙነት የቻይናን የአቪዬሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማጠናከር አላማ እንዳለውም አቶ ተወልደ ተናግረዋል። የኢትዮዽያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደምም ከመንገደኞች አውሮፕላን ጋር የተያያዙ የተለያዩ ማሽነሪዎች እና መገልገያዎችን ከቻይና እንደሚያስመጣ የጠቆመው ዘገባው አየር መንገዱ የቻይና ከተሞች ወደሆኑት ጉዋንⶱ እና ቤጂንግ በየቀኑ እንዲሁም በሳምንት ሶስቴ ደግሞ ወደ ቼንግዱ በረራ እንደሚያደርግ አመልከቷል። በተጨማሪም አየር መንገዱ በየቀኑ ወደ ሆንኮንግ እና ሻንሃይ የካርጎ በረራዎችን ያደርጋል። ቻይና ሰራሹ ሲ919 እኤአ በሜይ 5/2017 ሻንሃይ ከሚገኘው ፑዶንግ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የተሳካ የሙከራ በረራ ማድረጉንም ዥንዋ በዘገባው ማጠቃለያ ላይ አንስቷል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለኬንያ ፓርላማ የተላከ ላፕቶፖ የያዘ ኮንቴይነር ባዶ ሆኖ ተገኘ!

#ቻይና ለኬንያ ፓርላማ ድጋፍ ያደረገቻቸው ላፕቶፕ የያዘው ኮንቴይነር ሲከፈት ባዶ ሆኖ ተገኝቷል። ኮንቴነሮቹ እንዴት ባዶ ሆነው ከቻይና ወደ ኬንያ ሊጫኑ እንደቻሉ ባለስልጣናትን ግራ አጋብቷል። የኬንያ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክተር ጆርጅ ኪኖቲ፣ “ኮንቴይነር ከቻይና ባዶውን ተጭኖ መላኩ ሊገባኝ አልቻለም” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ አክለውም፣ ይህ አይነቱ ክስተት በኬንያ ሲፈጸም ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፤ ቢቢሲ/#ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom #WHO #DonaldTrump

ትላንት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ለWHO የምትሰጠውን ከፍተኛ ገንዘብ እንደምታቅብ ተናገረዋል። የዓለም የጤና ድርጅት ኮቪድ-19 የዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን በጊዜ አልተናገረም ብለዋል ፕሬዘዳንቱ።

ድርጅቱ ይህን ያደርገው በሽታው ለተጀመረባት #ቻይና ሲል ሊሆን ይችላል ሲሉ ግምት አዘል አነጋገር ተናግረዋል። "በጣም ቻይና ተኮር ይመስላሉ ፣ ይህን ማጤን ይኖርብናል' ሲሉ ተደምጠዋል ዶናልድ ትራምፕ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ ባለበት በዚህ አይነት ሁኔታ ለጤናው ድርጅት /WHO/ የሚዋጣ ገንዘብ መከልከ ተገቢ ነው ወይ? ተብለው ከጋዜጠኛ የተጠየቁት ትራምፕ 'እኔ አንሰጥም አላልኩም፣ እናጤነዋለን ነው ያለኩት' ሲሉ መልሰዋል።

ከፍተኛ ዘመቻ እየተካሄደባቸው የሚገኙት የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ዛሬ በሰጡት ዕለታዊ መግለጫቸው ላይ የግድያ ዛቻ እንደደረሰባቸው ፤ እሳቸው ግን ግድ እንዳልሰጣቸው ተናግረዋል። በማን ይህ ሊደረግ እንደቻለ ግን አልተናገሩም።

ከሁለት (2) እና ከሦስት (3) ወር በላይ #ዘረኛ ጥቃቶች ተሰንዝረውብኛል ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ 'ጥቁር ተብያለሁ። እውነቱን ለመናገር እኔ በጥቁርነቴ እኮራለሁ። የሚባለው ነገርም ግድ አይሰጠኝም' ሲሉም ተደምጠዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ፣ ቪኦኤ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmbassadorTayeAtskeSelassie ትላንት በነበረው የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስበስባ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ንግግር አድርገው ነበር። አምባሳደር ታዬ በህወሓት የተፈጸመው የክህደት ስራ በእጅጉ የሚያሳዝንና ኢትዮጵያ በዚህ ወንጀለኛ ቡድን ያሳለፈችውን ጊዜ ለመርሳት የአንድ ትውልድ ጊዜ የሚፈጅ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ቡድኑ ያን ሁሉ ደም መፋሰስ እንዲፈጠር ባያደርግ…
#UNSC

በትላንትናው የፀጥታው ምክር ቤት ሰብሰባ ላይ የሀገራት ተወካዮች ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው አንድ (1) ዓመት ከህወሓት የተቃጣበትን ወታደራዊ አደጋ መመከቱን አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ተናግረዋል።

መንግሥት ምግብን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ለሚፈልጉ ሰዎች ከUN ጋር በመተባበር ሲያቀርብ እንደነበር ተናግረዋል።

ለሰብአዊ ድጋፍ እንዲያመች በሚል የተናጠል የተኩስ አቁም ማድረጉን ተናግረዋል። ነገር ግን የተደረገው ጥረት ሁሉ በወንጀለኛው ቡድን ምክንያት ከንቱ ሆኖ ቀርቷል ብለዋል።

"በዚህ የወንጀል ቡድን ምክንያት የትግራይ ክልል ሕዝብ ያስፈልገው የነበረውን አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እያገኘ አይደለም" ሲሉ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

በአማራ ክልል እና በአፋር ክልል በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎችም በዚህ ቡድን በየበራቸው ላይ መገደላቸውን ገልጸዋል።

#ቻይና

ቻይናን የወከሉት ዣንግ ጁን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ያለው ሁኔታ የፖለቲካ፣ የታሪክ፣ የብሔርና ሌሎች ምክንያቶች ጥምር ውጤት መሆኑን ጠቁመው መፍትሔ የሚገኘው በአገር ውስጥ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት አፍሪካዊ መፍትሄዎች ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት በድጋሚ ድጋፍ እንሰጣለን ብለዋል።

በተለይ አሜሪካና የተለያዩ አገራት የሚያደርጉትን ማዕቀብ በተመለከተም አስተያየታቸውን የሰጡት ተወካዩ፣ በንግድ ላይ ገደብ ማድረግ እና እርዳታን ማቋረጥ በፖለቲካው መፍትሄ ላይ ጣልቃ መግባት እንደሆነ አስረድተዋል።

ለፀጥታው ምክር ቤት አባላት ምክራቸውን ያስተላለፉት የቻይናው ተወካይ አባል አገራቱ የአገሪቱን ሉዓላዊነትና አመራር በማክበር ኢትዮጵያ የሰብአዊ አቅሟን እንድታሻሽል እና የሚሰጠው እርዳታም ሊጨምር ይገባል ብሏል።

#አሜሪካ

አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ 1 አመት ባስቆጠረው ግጭት ውስጥ ለተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፥ "ሁሉም ኃሃይሎች ጥፋተኞች ናቸው፤ ጥፋት የለሌለበት የለም" ሲሉ ተናግረዋል።

አምባሳደር ሊንዳ የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል እና አፋር ክልል እንዲወጡ እና ጥቃታቸውን ወደ አዲስ አበባ እንዳያሰፉ አሳስበዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም አቀፍ የጦርነት ሕጎችን እንዲሁም የሰብአዊ መብት ሕጎችን እንዲያከብር ጠይቀዋል።

ሰላምን ሊያመጡ የሚችሉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ናቸው ሲሉም አምባሳደሯ ተናግረዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/UNSC-11-09
#CHINA

ሹዌ ቢንግ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ተሾሙ።

#ቻይና በአሁኑ ወቅት በግጭት እየታመሰ ላለው የአፍሪካ ቀንድ ሹዌ ቢንግን ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ መሾሟ ታውቋል።

ሹዌ ቢንግ ቀደም ሲል በፓፑዋ ኒው ጊኒ የቻይና አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል። በአፍሪካ፣ በአሜሪካ እና በኦሺንያ የመሥራት ልምድ እንዳላቸው የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ዛሬ ማክሰኞ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ 📣

➡️ #ካሜሮን፦ በካሜሩን መገንጠልን አላማቸው አድርገው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ታጣቂዎች ናይጄሪያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ መንደር በፈጸሙት ጥቃት በትንሹ 20 ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል። ጥቃቱ ባሳለፍነው እሁድ በደ/ምዕራብ የካሜሩን ክፍል ኦቦኒ ሁለት በተሰኘ መንደር የተፈፀመ ሲሆን ከሞቱ ሰዎች ባሻገር ከ60 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ታጣቂዎቹ ነዋሪዎቹ በየወሩ ገንዘብ እንዲከፍሏቸው ይፈልጋሉ፤ ነዋሪዎቹ ደግሞ ፍቃደኛ አልሆኑም። ለዚህም ነው ጥቃት ያደረሱባቸው ተብሏል።

➡️ #ሜክሲኮ ፦ በደቡባዊ ሜክሲኮ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ በትንሹ 10 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች የገቡበትን ማወቅ እንዳልተቻለ ተሰምቷል።

➡️ #ቻይና ፦ የሻንጋይ ነዋሪዎች ከሁለት ወር በኃላ የኮቪድ-19 የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳቱን ተከትሎ ነፃ ሆነዋል። ነዋሪዎች ባለፉት 2 ወር ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል በተጣለ የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ከእንቅስቃሴ ርቀው ቆይተዋል።

➡️ #ዩክሬን ፦ የየክሬን ኬርሰን ግዛት በሩስያ ቁጥጥር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ሁሉንም የግንኙነት መስመሮች እንዲዘጉ ማድረጋቸው ተነግሯል።

➡️ #አሜሪካ ፦ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ሀገራቸው ለዩክሬን 'ቁልፍ ኢላማዎችን' ለመምታት የሚያስችላትን እጅግ የዘመኑ ሮኬቶችን እንደምትልክ አሳውቀዋል።

➡️ #ሶማሊያ ፦ ወደ ባይዶዋ እንደሚሄዱ የተነገረላቸው አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ፕሬዝዳንት ከሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ግዛት መሪ አብዲአዚዝ ሀሰን ሞሀመድ እና ከባህላዊ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ፕሬዜዳንቱ ወደ ባይዶዋ ያደረጉት ጉዞ ዳግም ፕሬዜዳንት ሆነው ከተመረጡ በኃላ የመጀመሪያቸው ነው።

#ቲአርቲ #ቢቢሲ #ፍራንስ24 #ሲጂቲኤን

@tikvahethiopia
የተመድ ፀጥታ ም/ቤት በኢትዮጵያ ገዳይ መክሯል ?

ትላንት ለሊት የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ #ኢመደበኛ_ዝግ ስብሰብ ያደርጋል ተብሎ ነበር። ስብሳባው ስለመደረግ አለማደረጉ እስካሁን በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም።

ስለዚህ ስብሰባ የሚታወቀው ነገር የሚከተለው ነው ፦

- ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ መስከረም 2 (እኤአ) አይርላንድ ከአልባኒያ ፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጋር በመሆን ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ በክፍት እንዲሰብሰብ ጠይቃ ነበር። አይርላንድ " በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በግጭት ምክንያት በረሃብ እየተሰቃዩ በመሆናቸው ለሰብአዊ ዕርዳታ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች በጣም ያሳስበናል " በሚል ነው ክፍት የሆነ ስብሰባ እንዲካሄድ ጥያቄ አቅርባ የነበረው፤ ሀገሪቱ ሁሉም ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙና በአፍሪካ ህብረት (AU) ወደሚመራው የሰላም ንግግር እንዲመለሱ እንደምትፈልግ ነው የገለፀችው።

- የክፍት ስብሰባ ጥያቄው በ #A3 ሀገራት ማለትም #በኬንያ#በጋቦን እና #በጋና ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ሀገራቱ ይህን የስብሰባ ይዘት የተቃወሙ ሲሆን የተስማማቱ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ (IID) እንዲካሄድ ነው። ይህም ኢትዮጵያ የምትመርጠው አይነት የስብሰባ ይዘት እንደነበር ተነግሯል።

ℹ️ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ (IID) ማለት ምንድነው ? IID መደበኛ ያልሆነ ዝግ ስብሰባ ሲሆን የምክር ቤት አባላት ያልሆኑትን እንዲሳተፉ የሚያስችልም ነው። የዚህ  የስብሰባ ይዘት የስብሰባ መዝገቦች የሌሉት ሲሆን በም/ቤቱ ወርሃዊ የስራ መርሃ ግብር ውስጥም አይካተትም።

- አይርላንድ ሁሉም ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት እንዲያቆሙ እና ለተቸገሩ ሰዎች ሁሉ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚጠይቅ ረቂቅ ጋዜጣዊ መግለጫ አሰራጭታ ነበር ሆኖም ግን #A3#ቻይና እና #ሩሲያ በረቂቅ ጽሑፉ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልነበሩም። ሀገራቱ መግለጫውን ከስብሰባው በኃላ ከግምት ውስጥ ማስገባትን ነው የመረጡት ተብሏል። በዚህም በመግለጫው ላይ የነበረ ውይይት ባለበት እንዲያዝ ተደርጓል።

- ትላንትና ይካሄዳል የተባለው እና እስካሁን ተካሂዶ ስለመሆን አለመሆኑ በይፋ ያልታወቀው የተ.መ.ድ. ፀጥታ ምክር ቤት የIID ስብሰባ ላይ የመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሃና ተቴህ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ነበር። የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆም አጭር መግለጫ እንዲሰጡ ተጋብዘው እንደነበር ታውቋል ፤ በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍም ተጋብዛ ነበር።

- ትላንት ለሊት በተያዘው እቅድም መሰረት ኢመደበኛ ስብሰባው (IID) መካሄዱ ከተረጋገጠ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነጋገረበት ነው የሚሆነው።

መረጃው ከSCR ፣ ከተመድ የአይርላንድ እና ኖርዌይ ተልዕኮ ፅ/ቤት የተሰባሰበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#China ቻይና ከ3 ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ድንበሯን #ለጎብኚዎች ከፍት አድርጋለች። ቻይና በመጋቢት 2020 ዓ/ም የኮቪድ  19 ወረርሽኝን ተከትሎ ነበር የጉዞ እግድ የጣለችው። ከአሁን በኃላ ገቢ መንገደኞች ማቆያ ስፍራ መቆየት ሳያስፈልጋቸው በቀጥታ መግባት ይችላሉ። ይሁንና ገቢ መንገደኞች #በ48_ሰዓታት ውስጥ የወሰዱትን የክትባት ማስረጃ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ቢቢሲ ፅፏል። @tikvahethiopia
#Ethiopia 🛫 #China 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ #ቻይና ሳምንታዊ የበረራ ምልልሱን ከፍ ሊያደርግ ነው።

በቻይና መንግስት ተጥለው የነበሩ የኮቪድ-19 ክልከላዎች መነሳታቸውን ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው የካቲት ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ቻይና ወደሚገኙ መዳረሻዎቹ የሚያደርገውን ሳምንታዊ የበረራ ምልልስ ከፍ በማድረግ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑን አየር መንገዱ ዛሬ አሳውቋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
#ቻይና

በኦሮሚያ ክልል፤ ሰሜን ሸዋ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አንድ የቻይና ዜጋ መገደሉን ተከትሎ እዚህ አዲስ አበባ የሚገኘው የሀገሪቱ ኤምባሲ ለቻይና ዜጎች የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ ፤ ከአዲስ አበባ በሰሜን በኩል 160 ኪ/ሜ ርቀት ላይ " ገብረ ጉራቻ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የነበሩ 9 ቻይናውያን ተኩስ ተክፍቶባቸዋል።

በዚም ጥቃት አንዱ ቻይናዊ ተገድሏል። በሌሎቹ ላይ ጉዳት ስለመድረስ አለመድረሱ እንዲሁም ስለታጣቂዎቹ ማንነት በኤምባሲው በኩል የተገለፀ ነገረ የለም።

የቻይና ኤምባሲ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩና ኢትዮጵያን የሚጎበኙ ዜጎቹ ለአደጋ ከሚያጋልጡ ቦታዎች ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል።

NB. ጉዳዩን በተመለከት ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም።

ምንጭ፦ በአዲስ አበባ የቻይና ኤምባሲን ዋቢ አድርገው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ / የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ናቸው የዘገቡት።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ቻይና

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ቻይና አቅንተው በቻይና ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ናቸው።

ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በወጣ መረጃ የቻይናው ጠ/ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኃላም የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከሪያ መንገዶች ላይ መክረዋል ተብሏል።

ከሁለትዮሽ ውይይቱ በመቀጠል ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ጠ/ሚ ሊ ኪያንግ በተገኙበት በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮች 12 ያህል የትብብር ስምምነቶች እና ሁለት የፍላጎት ሰነዶች ተፈርመዋል።

ዶ/ር ዐቢይ በቻይና ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ ከአራት ዓመት በኃላ ሲሆን በቀጣይ በሚካሄደው 3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ አለም አቀፍ ትብብር መድረክ ላይም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፎቶ፦ #PMOffice

@tikvahethiopia