TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ደዴሳ⬆️

እለተ እሁድ የሀይማኖት አባቶች በታደሙበት እንዲሁም የአካባቢው አስታራቂ ሽማግሌዎች ወደ ሁለቱም ተጎጂ ቤተሰቦች ቤት በማቅናት በባህሉ መሰረት እርጥብ ሳር በማቅረብ፣ በግ በማረድ እና አጥንት በመስበር ብሎም በሌሎች ክንውኖች ቂም በቀልን አጥፍቶ እርቅ፣ #ሰላምና #አንድነትን የሚያበስረው ስነ-ስርአት ተካሂዷል፡፡ በሎይጅጋንፎ ወረዳ በለው #ደዴሳ ቀበሌ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ እና በአማራ ተወላጆች መካከል ግጭት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንድማማችነት ከባንዲራ በላይ ነው⬇️

በሀገራችን የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እና ትዉልድ መስዋዕትነት የከፈለበትን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን እዉን ለማድረግ በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ ይታወቃል።

በዚህ ሂደትም በሀገራችን የዴሞክራሲ ምህዳር ከመጥበቡ የተነሳ የትጥቅ ትግልን ለማራመድ ተገድደዉ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ትግል ለማድረግ የተፈጠረዉን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ወደ ሀገር በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

በተፈጠረዉ ምቹ ሁኔታ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ላይ የሚገኙትን የፖለቲካ ድርጅቶችንም ሆነ ግለሰቦች ደጋፊዎቻችዉ እና አድናቂዎቻቸዉ የተለያዩ ዓርማዎች፣ #ባንዲራ እና ምልክቶችን በመያዝ አቀባበል እያደረጉ፣ ድጋፋቸዉን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

በነዚህ የአቀባበል እና የድጋፍ ሂደቶች ማንኛዉም ሰዉ የመሰለዉን ዓርማ፣ ባንዲራ ወይም ምልክት ይዞ አቀባበል ወይም ድጋፍ ቢያደርግ የሌላዉን ዜጋ መብት እስካልተጋፋ ድረስ ምንም ችግር የለዉም። ዴሞክራሲያዊ መብትም ነዉ!

#ነገር_ግን አሁን አሁን በድጋፍ እና በአቀባበል ወቅት የሚያዙ ባንዲራዎች እና ምልክቶች #የልዩነት እና የዉዝግብ እልፎም #የግጭት መነሻ እየሆኑ እንደመጡ እያስተዋልን ነዉ። ይህ ሁኔታ ከባንዲራ፣ አርማ እና ምልክቶች ጋር ተያይዞ መግባባት ለመፍጠር ሰፊ ስራ መስራት እንዳለብን ያመላክተናል። ሁኔታዉ በቶሎ መስመር እንዲይዝ ካልተደረገም ለግጭት ነጋዴዎች ቶምቦላ ሎተሪ ይሆንላቸዋል።

ትግላችንም ነፃነት፣ እኩልነት እና ወንድማማችነት የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለመገንባት ከሚደረግ ወሳኝ ትግል ወደ ዓርማ እና ባንዲራ ፉክክር እና ንትርክ ብሎም ግጭት ዝቅ ሊል ይችላል። እንደዚህ አይነቱ ሂደት ደግሞ ከማንም በላይ የግጭት ነጋዴዎችን የሚጠቅም ይሆናል።

ትግላችን #ነፃነት፣ እኩልነት እና ወንድማማችነት የሰፈነባት #ዴሞክራሲያዊት ሀገር መገንባት እንደሆነ ሁሉም የለዉጥ ደጋፊ ሊያሰምርበት ይገባል።

በዚህ ወሳኝ ምዕራፍ ልዩነትን ከሚያጎሉና ወደ ግጭት ሊያመሩ ከሚችሉ ጉዳዮች ይልቅ አንድነትን ሊያጠናክሩ #ሰላምና #መተጋገዝን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ማትኮር ወሳኝ ይሆናል። ይህ ካልሆነ ግን በጠንካራ ክንድ ትግሉን ወደ ስኬት ከማንደርደር ይልቅ በባንዲራ፥ በአርማ እና በትናንት ታሪካችን ተፈጥረዉ በነበሩ ድክመቶችንና ትናንሽ የልዩነት ነጥቦች ላይ ንትርክ ዉስጥ ለመግባት ያስገድደናል። እንደዚህ አይነት ጠቃሚ ያልሆነ ዉዝግብ አንድነታችንን ይፈታተናል። ጠንካራ የትግል ክንዳችንን ያዝላል። ለሽንፈትና ለዉርደትም ይዳርገናል።

ስለሆነም የትግልና የድል ጉዞአችን እንዳይገታ ከልዩነቶቻችን ይልቅ አንድ በሚያደርጉን ነገሮች ላይ አትኩረን እንሻገር። ከተሻገርን በሗላ በልዩነቶቻችን ዙሪያ በሰከነ እና በሰለጠነ አግባብ ተወያይተን መፍታት እንችላለን።

ነፃነት፣ ወንድማማችነትና እኩልነት ካለፈዉ ታሪክም ሆነ ከባንዲራ በላይ ነዉ!

©አቶ አዲሱ አረጋ(OPDO)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊስ‼️

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኢፌዲሪ ህገመንግስት መሰረት በማድረግ የህግ የበላይነት እንዲሰፍን ፤ የዜጎች #ሰላምና ደህንነት #እንዲረጋገጥ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በ2011ዓ/ም የከፍተኛ ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት #በሰለማዊ መንገድ እንዲቀጥል ከወትሮ በተለየ በሁሉም ሀገሪቱ #ዩንቨርሲቲዎች እና #ኮሌጆች በተለያዩ አከባቢዎች ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ እያካናወነ ሲሆን የመማርና ማስተማር ሂደትም እንዳይስተጓጎል ከሌሎች ጥምር ኮሚቴዎች ጋር ተቀናጅቶ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ እየሰራ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የተመደባችሁ አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋም በመሄድ #ያለምንም የፀጥታ #ስጋት ትምህርታችሁን መማር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ደህንነታችሁ በተመለከተ በሁሉም ዩንቨርሲቲዎችና አካባቢዎች ከወትሮ በተለየ ጥብቅ ቁጥጥርና ጥበቃ እያደረግን እንደምንገኝ በድጋሜ እናሳውቃለን፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ቦታ ሲሆዱም ሆነ ግቢ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ስጋት እንዳይኖር አስቀድመን ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቂ ዝግጅት በማድረግ እየሰራን እንደምንገኝና ምንም ዓይነት የደህንነት ስጋት እንደሌለ ለተማሪዎችና ለቤተሰቦቻቸው እንገልፃለን፡፡

©የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዮስ ለክልሉ #ሰላምና #ፀጥታ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መውሊድ!

ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድን በዓል ሲያከብር ለአገር #ሰላምና #አንድነት ጸሎት በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ። ምክር ቤቱ ጥሪውን ያቀረበው 1493ኛውን የነብዩ መሃመድ የልደት በዓል (መውሊድ)ን አስመልክቶ ለኢዜአ በላከው የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ #ሰላምና #መረጋጋት ለማምጣት የየተቋማቱ ኃላፊዎችና መምህራን ሥራቸውን በአግባቡ እየተወጡ #አለመሆኑ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር #ጣሰው_ወልደሀና እንዳሉት፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ ለውጥ ለማምጣት ህዝቡ ተቃውሞዎች ሲያደርግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ተሳታፊዎች ነበሩ፤ ለውጡ ከመጣ በኋላም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ መንግሥትና የየተቋማቱ ኃላፊዎችና መምህራን ሥራቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ሁከቶቹ ተበራክተዋል ብለዋል፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚታዩትን የሰላም መደፍረስ ምክንያት የሚያጠና ቡድን ማዋቀሩን በመጥቀስ፤ በቀጣይ ለሚሠራቸው ሥራዎች አንድ ሚሊዮን ብር መመደቡንም ገልጸዋል፡፡ ሰላም ከሌለ ልማትና የመኖር ነፃነት ስለማይኖር በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን ለሰላም ዘብ መቆም እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጉዞ ሉሲ ለአንድነት እና ለፍቅር!

ጉዞ ሉሲ የአንድነት እና የፍቅር ፕሮጀክት የካቲት 14 ይጀምራል፡፡ ጉዞ ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ ነው፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ሁሉም #ኢትዮጵያውያን የአንድ #የሉሲ ልጆች መሆናችንን በማሳወቅ #ሰላምና #ፍቅር በኢትዮጵያ እንዲነግስ የማድረግ ዓላማን የያዘ ነው፡፡ ሀገራችን የዓለም ዘር መገኛ መሆኗን በመገንዘብ ለትውልዱ የተመቸች እና የበለጸገች ኢትዮጵያን መፍጠር ያለመ ነውም ተብሏል፡፡ ያለፈውን ቂምና ጥላቻ በመተው በመደመር እና እርቀ ሰላም እንዲመጣ በሁሉም ክልሎች ሉሲን በአስታራቂነት እና በሰላም አምባሳደርነት በመጠቀም በሀገሪቱ ሰላምና ፍቅርን በመስበክ አንድነትን በማጉላት የተሻለች ኢትዮጵያን መፍጠርም ሌላው ዓላማ ነው፡፡

ምንጭ፦ AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሸዋሮቢት~መንገዶች ተከፍተዋል‼️

በሸዋሮቢት ከተማ የተከስቶ የነበረው #አለመረጋጋት በአሁኑ ሰዓት ወደ ነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የሸዋሮቢት ከተማ ከንቲባ አቶ #አካሉ_ወንድሙ ተናገሩ።

እንደ ከንቲባው ገለጻ በአሁኑ ሰዓት የተዘጉ መንገዶች #ተከፍተው የጸጥታ ሀያሉ እና የአካባቢው ማህበረሰብ መንገደኞችን #በመሸኘት ላይ መሆናቸውን ተናግረው የሸዋሮቢት ከተማ ህዝብ #መቻቻልና #መረዳዳት ባህሉና ወጉ የሆነው ህዝባችን ድርቶችን ሁሉ በተለመደውን የችግር መፍቻ መንገዶችን፣ ህግን በማክበርና በማስከበር ስራ ላይ #ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የጸጥታ ሀይሉ፣ የሀይማኖት አባቶች እና ሀገር ሽማግሌዎች ከተማውን #ለማረጋጋት ላያደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል። በአሁኑ ሰዓት ሽዋሮቢት ወደነበረችበት #ሰላምና መረጋጋት እየተመለሰች መሆኑን ከንቲባው ተናግረዋል።

Via Shewa Robit City Administration Kentiba office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥለቻ ንግግር ወጊውን መልሶ #ይጎዳል!
(በሚራክል እውነቱ)

የጥላቻ ንግግር የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በፖለቲካዊ አመለካከት፣ በሚከተሉት እምነት፣ በዘር፣ በትምህርት ደረጃ፣ በሃብት ደረጃ በቀለማቸው በእነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች ከእኛ ሃሳብ ተቃራኒ ናቸው ብለን የምንፈርጃቸውን ሰዎች ስብእናቸውን በመጋፋት፣ ማንነታቸውን ጭምር በሚያሳንስና በሚያዋርድ መልኩ የሚሰነዝር ቃል ነው፡፡ አለፍ ሲልም ሰዎችን በማይሆን ፍረጃ ይገደል ይታሰር ይሰደድ የሚል ፍርድ በማሳለፍ ጭምር ሚዛናዊነትን የሚያስት ነው የጥላቻ ንግግር፡፡ እከሌ እንዲህ ካልሆነ፤ እክሌ ይሄ ፍርድ ይገባዋል፣ እክሌ ንፁህ ነው፤ ይሄኛው ደግሞ በደሉ ክልክ በላይ ሆኗል፤ ይሄ ወገን ይሄ ፍርድ ይገባዋልና መሰል የጥላቻ መርዞችን በመርጨት የሰዎችን አብሮ የመኖር እሴት እንዲሸረሸር የማድረግ አባዜ ነው፡፡

በግለሰቦች ላይ የሚሰነዘር የጥላቻ ንግግር የሰዎችን ስብዕና በመጋፋት ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ እንዲገቡ ሊያደርግ እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡ ጠንካራ ስነልቦና ያለው ሰው እንኳን በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩ ክብረ ነክ በሆኑ የጥላቻ ንግግሮች ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ሲገቡ ይስተዋላል፡፡ የዚህን ትርፍና ኪሳራ መመዘን እንግዲህ የባለቤቱ ነው፡፡

ማንም ሰው ወደዚህ ምድር የመጣው በምክነያት ነው፡፡ እኔ የተፈጠርኩት በምክንያት ነው ብሎ ማመን ግድ ይላል፡፡ ያኔ እያንዳንዳችን በምንዘራው ልክ የምናጭድ መሆናችን ይገባናል፡፡ በጎ በጎውን ተናግሮ ተፅእኖ መፍጠርና የተሳሳተ አስተሳሰብ ማራመድና የጥላቻ ንግግር የሚያመጣውን መመዘን ይገባል፡፡

በመሆኑም በግለሰቦች ወይም በህዝቦች መካከል አለመግባባት፣ ብሎም #ግጭትን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ የጥላቻና #አደገኛ ንግግሮች መባባስ የማህበራዊ ሚዲያዎች አሉታዊ አስተዋጽኦ በእጅጉ የጎላ መሆኑ እርግጥ ነው በመሆኑም የሚጠቅመውን መምረጥ ግድ ይላል ማለት ነው፡፡

ማህበራዊ ሚዲያዎች ማህበረሰቡን ለሚጎዱ መጥፎ ተግባራት ማራመጃነት እንዳይውሉ ይልቁንም ለአገር #ሰላምና የጋራ #መግባባት በጎ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማድረግ ሁሉም ከራሱ ጀምሮ ከጥላቻ ንግግር ራሱን መቆጠብ ይገባዋል፡፡ መጨረሻው ለራስ የሚኖር ግምት ያነሰ እንዲሆን በማድረግ ራስን ጭምር ለማህበራዊ ቀውስ የሚከት ነውና፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥለቻ ንግግር ወጊውን መልሶ #ይጎዳል!
(በሚራክል እውነቱ)

የጥላቻ ንግግር የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በፖለቲካዊ አመለካከት፣ በሚከተሉት እምነት፣ በዘር፣ በትምህርት ደረጃ፣ በሃብት ደረጃ በቀለማቸው በእነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች ከእኛ ሃሳብ ተቃራኒ ናቸው ብለን የምንፈርጃቸውን ሰዎች ስብእናቸውን በመጋፋት፣ ማንነታቸውን ጭምር በሚያሳንስና በሚያዋርድ መልኩ የሚሰነዝር ቃል ነው፡፡ አለፍ ሲልም ሰዎችን በማይሆን ፍረጃ ይገደል ይታሰር ይሰደድ የሚል ፍርድ በማሳለፍ ጭምር ሚዛናዊነትን የሚያስት ነው የጥላቻ ንግግር፡፡ እከሌ እንዲህ ካልሆነ፤ እክሌ ይሄ ፍርድ ይገባዋል፣ እክሌ ንፁህ ነው፤ ይሄኛው ደግሞ በደሉ ክልክ በላይ ሆኗል፤ ይሄ ወገን ይሄ ፍርድ ይገባዋልና መሰል የጥላቻ መርዞችን በመርጨት የሰዎችን አብሮ የመኖር እሴት እንዲሸረሸር የማድረግ አባዜ ነው፡፡

በግለሰቦች ላይ የሚሰነዘር የጥላቻ ንግግር የሰዎችን ስብዕና በመጋፋት ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ እንዲገቡ ሊያደርግ እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡ ጠንካራ ስነልቦና ያለው ሰው እንኳን በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩ ክብረ ነክ በሆኑ የጥላቻ ንግግሮች ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ሲገቡ ይስተዋላል፡፡ የዚህን ትርፍና ኪሳራ መመዘን እንግዲህ የባለቤቱ ነው፡፡

ማንም ሰው ወደዚህ ምድር የመጣው በምክነያት ነው፡፡ እኔ የተፈጠርኩት በምክንያት ነው ብሎ ማመን ግድ ይላል፡፡ ያኔ እያንዳንዳችን በምንዘራው ልክ የምናጭድ መሆናችን ይገባናል፡፡ በጎ በጎውን ተናግሮ ተፅእኖ መፍጠርና የተሳሳተ አስተሳሰብ ማራመድና የጥላቻ ንግግር የሚያመጣውን መመዘን ይገባል፡፡

በመሆኑም በግለሰቦች ወይም በህዝቦች መካከል አለመግባባት፣ ብሎም #ግጭትን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ የጥላቻና #አደገኛ ንግግሮች መባባስ የማህበራዊ ሚዲያዎች አሉታዊ አስተዋጽኦ በእጅጉ የጎላ መሆኑ እርግጥ ነው በመሆኑም የሚጠቅመውን መምረጥ ግድ ይላል ማለት ነው፡፡

ማህበራዊ ሚዲያዎች ማህበረሰቡን ለሚጎዱ መጥፎ ተግባራት ማራመጃነት እንዳይውሉ ይልቁንም ለአገር #ሰላምና የጋራ #መግባባት በጎ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማድረግ ሁሉም ከራሱ ጀምሮ ከጥላቻ ንግግር ራሱን መቆጠብ ይገባዋል፡፡ መጨረሻው ለራስ የሚኖር ግምት ያነሰ እንዲሆን በማድረግ ራስን ጭምር ለማህበራዊ ቀውስ የሚከት ነውና፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጨፌ_ኦሮሚያ

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የህዝብን #ሰላምና #ደህንነት ለማረጋገጥ የህግ የበላይነት ለማስከበር ትኩረት እንዲሰጥ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ አሳሰቡ።

አፈ ጉባዔዋ ዛሬ በአዳማ ከተማ የከልሉን ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ጉባዔ ሲከፍቱ እንዳስገነዘቡት ለሕግ የበላይነት መከበር ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ ይገባል፤ የህዝብ የመልካም አስተዳደርና የእኩልነት ጥያቄ መመለስ አማራጭ እንደሌለው ያስገነዘቡት አፈ ጉባዔዋ ፣ በክልሉ ያለው ችግር የህግ የበላይነት ጥስትና የህዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ያለመመለስ ነው ብለዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ህዝቡ በትግሉ የተጎናፀፈውን ድልና ለውጥ ማደናቀፍ ሳይሆን ፣ የሰፈነውን የፖለቲካ ምህዳር በመጠቀም በምርጫ ተወዳድሮ ለማሸነፍ እንዲሰሩ አሳስበዋል። ጨፌው ችግሮቹን ለማስወገድና ለውጡን ለማስቀጠል ድጋፍ እንደሚያደርግም አፈ ጉባዔዋ አረጋግጠዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮማንድ ፖስት!

በጌዴኦ ዞን #ሰላምና #መረጋጋትን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን በዞኑ የተቋቋመው ንዑስ ኮማንድ ፖስት ገለጸ፡፡ ንዑስ ኮማንድ ፖስቱ በዞኑ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ከባለ ድርሻዎች ጋር ትናንት በዲላ ውይይት አካሂዷል። የንዑስ ኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ኮሎኔል መስፍን በየነ የዞኑን ሰላም ወደ ቀደመው ደረጃ ለመመለስ በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምስራቅ_ዕዝ

የህብረተሰቡን #ሰላምና #ደህንነት የማስጠበቅ ስራን እንደሚያጠናክር የምስራቅ ዕዝ አስታወቀ። የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ስራን በተጠናከረ መልኩ እንደሚያስቀጥል በሀገር መከላከያ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ዘውዱ በላይ አስታወቁ።

ዋና አዛዡ ዛሬ በጅግጅጋ ገርባሳ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም የመካከለኛ አመራሮች ስልጠና በተጀመረበት ወቅት እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት የህብረተሰቡን ሰላም የሚያውኩ አካላትን በመከላከሉ ረገድ ሰራዊቱ ከነዋሪው ጋር በመሆን የሚጠበቅበትን ግዳጅ ተወጥቷል።

“በአሁኑ ወቅትም በቀጠናው የተለያዩ የጸብ አጫሪነትና የጸረ ሰላም ተግባር ሲፈጠሩ ሰራዊቱ ከክልል የጸጥታ አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ሰላምን የማስከበር ስራ እያከናወነ ይገኛል” ብለዋል። በዚህም የቀጠናው የሰላም ሁኔታ ከዓመት ዓመት መሻሻል እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።

በቅርቡ በቀጠናው አንዳንድ ከተሞች በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ለማሰማት ዜጎች ወደ አደባባይ የወጡበትን አጋጣሚ በመጠቀም የራሳቸውን አጀንዳ ለማራመድ የሞከሩ ጥቂት ግለሰቦች እንደነበሩ አስታውሰዋል። ይህም ህብረተሰቡ በብሔርና በሃይማኖት ግጭት ውስጥ እንዲገባ ለማድረግ እንደነበረ ጠቅሰዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia