TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ድሬዳዋ ፖሊስ⬇️

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ሐምሌ 29/2010 ዓም ለ13 ሰዎች ህልፈትና ለንብረት መውደም ምክንያት በሆነው ግጭት ላይ ምርመራውን አጠናቆ ለአቃቤ ህግ ለመላክ መዘጋጀቱን ይፋ አደረገ ኮሚሽኑ ዛሬ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በእለቱ በተፈጠረው ሁከት በሶስት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የ13 ንፁሀን ዜጎች #ህይወት ማለፋንና በ42 ቤቶች ላይ ቃጠሎና ዝርፊያ መካሔዱን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ባደረገው ምርመራ 4 ግለሰቦች በቤት ቃጠሎ ፣21 ግለሰቦች ደግሞ በቀጥታ በግድያው መሳተፋቸውን በማስረጃ ማረጋገጡን ገልጾ በ5 #ተጠርጣሪዎች ላይ ማስረጃ እያሰባሰበ መሆኑን በመግለጫው አስረድቷል።

ከ13ቱ ሟቾች 8ቱ የአንድ አመት ህፃንን ጨምሮ ከ15 አመት በታች እድሜ ያላቸው ሲሆኑ በንብረት ረገድም ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

በግጭቱ ወቀት የነፍስ ግድያ ፣ የቤት ቃጠሎና የዝርፊያ ተደራራቢ ወንጀል በመፈፀሙ ምርመራውን ለማጠናቀቅ ጊዜ መውሰዱን በመግለጫው ተመልክቷል።

የተፈጠረውን ግጭት የብሔር ግጭት ለማስመሰል ሙከራ መደረጉን፣ የድሬዳዋ ሕዝብ ያዳበረው የአብሮ መኖር እሴት ለእንዲህ አይነቱ ኋላ ቀር አስተሳሰብ የማይመች በመሆኑና ፖሊስ ሁኔታውን መቆጣጠር በመቻሉ የታሰበው ሊሳካ አለመቻሉን የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግኑኝነት ዲቪዥን ሀላፊ ዋና ሳጅን ባንታለም ግርማ ገልፀዋል።

ከሀምሌ 29 በኋላ ነሀሴ 29/2010 ዓም በድጋሚ ግጭት ለማስነሳት መሞከሩን የገለጹት ዋና ሳጂን ባንታለም ግርማ ፖሊስ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ሁኔታውን በመቆጣጠር 300 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎችን የያዘ ሲሆን ከተያዙት ውስጥ በ77 ቱ ላይ ምርመራ አጣርቶ
ለአቃቤ ህግ በመላኩ አቃቤ ህግ በፍርድ ቤት #ክስ መመስረቱን ተናግረዋል።

ሰሞኑን በቤቶች ላይ የተደረገውን ምልክት በተመለከተም ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር እጅና ጓንት ሳይሆን መዳፍና ጣት ሆኖ በመስራቱ ምልክቱ ወደ ተግባር እንዳይለወጥ መደረጉን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊው ገልፀዋል።

ከነገ ጀምሮ በክርስትና እምነት ተከታዮች የሚከበረው የደመራና የመስቀል በአል ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የገለጹት ዋና ሳጂን ባንታለም ግርማ ሰላም ወዳዱ የድሬዳዋ ሕዝብም ከስሜታዊነት ርቆ እንደ ሁልጊዜው ከፖሊስ ጋር በመተበባር ለሰላሙ ዘብ እንዲቆም ጠይቀዋል።

ኮሚሽኑ ህብረተሰቡ በተለይም #ወጣቶች እንዲሁም የአስተዳደሩ አመራሮች ሁከትን ለማክሸፍና ሠላምን ለማረጋገጥ ላሳዩት ቁርጠኝነት #ምስጋናውን አቅርቧል ።

ምንጭ፦ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጎንደር⬆️

የጎንደር ከተማ #እስልምና ዕምነት ተከታዮች #የመስቀል በዓል በከተማዋ በድምቀት እንዲከበር ቀድመው ያደመቁት እነርሱ ናቸው፡፡ የመስቀል በዓል የሚከበርበትን ቦታ ቀድመው በማጽዳት #አንድነታቸው መቼም እንደማይላላ ያሳዩበት ነው፡፡ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከትም ለከተማዋ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች #ምስጋናውን ችሯል፡፡ እውቅናም ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia