TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹እየተገነባ ያለው #የመከላከያ_ሠራዊት ዛሬ የሁሉንም #ሉዓላዊነት የሚጠብቅ ነገ ደግሞ የሕዝብ ውክልና አግኝታችሁ ሥልጣን የምትይዙ ተረክባችሁ የምታስቀጥሉት ተቋም ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር #ዐብይ_አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #US የማይክ ሐመር ስለ ኢትዮጵያ ቆይታቸው ምን አሉ ? አሜሪካ የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነቷን እና #የግዛት_አንድነቷን_በማክበር ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያላትን ፍላጎት እንደሚያረጋገጡ የሀገራቸውን አቋም ገልፀዋል። በአሜሪካ ህዝብ ለጋስነት ሀገሪቱ ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን አመልክተዋል። ሰላምን በማረጋገጥ በኩል የጋራ ፍላጎቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት…
#USA

በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሏል።

ልዩ መልዕክተኛው ከነገ ጀምሮ ወደ እስከ መስከረም 5 /2015 ኢትዮጵያ እና ወደ ቀጠናው ሀገራት እንደሚጓዙ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳውቋል።

በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ዳግም ያገረሸው ግጭት እንዲቆም እና የሰላም ንግግር እንዲጀመር ግፊት ያደርጋሉ ተብሏል።

አምባሳደር ሐመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው የኢትዮጵያ መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናትን ያነጋግራሉ።

በተጨማሪ የተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎችን ከሚወክሉ የሲቪል ማህበራት እና የፖለቲካ ተዋናዮች ጋር በመገናኘት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሁሉም ህዝብ ዘላቂ ሰላም፣ ደህንነት እና ብልፅግና ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማጎልበት እንደሚቻል ይወያያሉ።

አሜሪካ ለኢትዮጵያ #አንድነት#ሉዓላዊነት እና #ለግዛት_አንድነት ቁርጠኛ ነኝ ስትል በድጋሚ አረጋግጣለች።

አምባሳደር ሐመር ከሳምንታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አዲስ አበባ እና መቐለ ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እና ህወሓት አመራሮች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ህወሓት /TPLF/ ከትግራይ ውጭ እየፈፀመ ያለውን ጥቃት ፤ የኢትዮጵያ መንግስትን የአየር ጥቃት እና የኤርትራን ዳግም ወደ ግጭት መግባቷን እንደምታወግዝ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒ ብሊንከን በኩል አሳውቃለች።

ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እና በሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ የሚደረገውን ጥረት እንዲያጠናክሩ ጠይቃለች።

Via US Embassy AA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
* Update

የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር መነጋገራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳውቋል።

ሐመር በዚሁ ወቅት ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ ፤ በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት ወደ ሰላም ድርድር ማምራት እንደሚያስፈልግ መወያየታቸውን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

ሐመር ከህወሓት ሊቀመምበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር እንዴት/በምን ተገናኝተው እንደተነጋገሩ ባይገለፅም ለእሳቸውም ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ወደ ሰላም ድርድር ማምራት እንደሚያስፈልግ እንዳስገነዘቧቸው ተገልጿል።

እንደ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም እና ወደ ድርድር ለመግባት በመጪዎቹ ቀናት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሀፊ ሞሊ ፊ ፣ አምባሳደር ማይክ ሀመር እና ሌሎችም የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከአፍሪካ ህብረት እንዲሁም ከቀጠናው ቀልፍ ናቸው ከሚባሉት ተዋናዮች ተመድ ፣ አውሮፓ ህብረት ፣ ከዩናይትድ ኪንግደም ልዑካን ጋር ይመክራሉ።

መስሪያ ቤቱ ፤ የአሜሪካ ዓላማ በኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ፤ ኤርትራም ወደ ድንበሯ እንድትመለስ ዴፕሎማሲያዊ ግፊት ማድረግ ነው ብሏል።

ለግጭቱ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ የለውም ያለው የአሜሪካ መንግስት መፍትሄድ በሁሉም ወገን ዘንድ የሰላም ድርድር ማድረግ ብቻ ነው ብሏል።

አሜሪካ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ለኢትዮጵያ #አንድነት#ሉዓላዊነት#የግዛት_አንድነት ቁርጠኛ አቋም አለኝ ስትልም በድጋሚ ማረጋገጧን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UpdateAU #ETHIOPIA የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ፤ የትግራይ ክልል መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚካሄደው የሰላም ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኝነቱን መግለፁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል። ይህን የገለፁት የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ከፌዴራል መንግስት…
#USA #ETHIOPIA

" አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች " - አንቶኒ ብሊንከን

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው።

ብሊንከን ፤ የአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ላለው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለማበጀት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት (TPLF) በተቻለ ፍጥነት ወደ ውይይት እንዲመጡ ለማድረግ እየሰራ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ሲባል ከህወሓት ጋር " በየትኛውም ስፍራ፣ በማንኛውም ጊዜ "  ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን እንደገለፀ ያስታወሱት ብሊንከን ለዚህ የመንግስት ዝግጁነት የሚሰጥ ምላሽን እናበረታታለን ብለዋል። ህወሓት (TPLF) ግጭት ለማቆም እና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ያወጣውን መግለጫ እናበረታታለን ሲሉም አክለዋል።

ዓለም አቀፍ አጋሮች የሰላም ሂደቱን ለማገዝ ዝግጁ ናቸውም ብለዋል።

ኤርትራ እና ሌሎችም ግጭቱን ማቀጣጠል ማቆም አለባቸውም ሲሉ ገልፀዋል።

አሜሪካ የኢትዮጵያን #አንድነት#ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት እንደምትደግፍ የገለፁት አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ #ጠንካራ_አጋርነት መመለስ ትፈልጋለች ሲሉ ገልፀዋል።

" የአዲስ ዓመት መንፈስን ታሳቢ በማድረግ የአገሪቱ መሪዎች አገሪቱ መከራዋ ወደሚያበቃበት እና ዘላቂ ሰላም ሊያስገኝ ወደሚያስችል መንገድ እንደሚሯት ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #ETHIOPIA " አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች " - አንቶኒ ብሊንከን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል። ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው። ብሊንከን ፤…
#USA #ETHIOPIA

" ለኢትዮጵያ አንድነት ፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ቁርጠኛ ነን " - አሜሪካ

አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋ አምባሳደር ማይክ ሀመር ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር #ውጤታማ ውይይት አድርገዋል ስትል አሳወቀች።

ሀገሪቱ ይህን ያሳወቀችው ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲው በኩል ነው።

የአምባሳደር ማይክ ሐመር የኢትዮጵያ ጉብኝት ውጤታ ነበር ያለችው አሜሪካ  " ለኢትዮጵያ #አንድነት#ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት ቁርጠኛ ነን " ስትል አስታውቃለች።

በተጨማሪ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲበለጽጉ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ እንደምትፈልግ ገልፃለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሰላም ስምምነቱን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና አቶ ጌታቸው ረዳ ተፈራርመዋል። ከተፈራረሙ በኃላም እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል። በአጠቃላይ የተደረሱትን የስምምነት ነጥቦችን የያዘው እና በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል (አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና አቶ ጌታቸው ረዳ) የተፈረመበት ወረቀት እንደደረሰን የምንልክላችሁ ይሆናል። @tikvahethiopia
#Update

ዛሬ በፕሪቶሪያ ፤ በኢትጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነትን በተመለከተ የወጣው የጋራ መግለጫ 12 ነጥብ የያዘ ነው።

ከዚህም ስምምነት መካከል ፦

- የህወሓት ቡድን #ትጥቅ_እንዲፈታ ከስምምነት ተደርሷል።

- የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት ለማረጋገጥ እና የኢፌደሪ ሕገ-መንግሥቱን ለማስከበር የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ተስማምተዋል።

- ኢትዮጵያ #አንድ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል ብቻ አላት በሚለው ስምምነት ተፈርሟል።

- በመሬት ላይ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የህወሓት ተዋጊዎችን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ተዋጊዎችን ከሠራዊቱ እንዲወጡ ለማድረግ እና መልሶ ወደ ማኅበረሰቡ ለመቀላቀል ስምምንት ላይ ተደርሷል።

- #የጥይት_ድምጽ_በዘላቂነት_እንዳይሰማ  በመስማማት፣ ጦርነቱ እንዲያበቃ የሚያስችል ዘላቂ የግጭት ማስወገድ ስምምነት ተፈርሟል።

-  በትግራይ ክልል ህገ መንግስታዊ ስርዓትን ወደነበረበት ለመመለስ እና የሽግግር እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ተፈርሟል።

- የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ለማቆም ስምምነት ላይ ተደርሷል።

- በትግራይ ክልል መሰረታዊ አገልግሎት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ስምምነት ተፈፅሟል።

@tikvahethiopia
" በደቡብ አፍሪካ በነበረው ድርድር ኢትዮጵያ መቶ በመቶ ያቀረበችው ሀሳብ ተቀባይነት አግኝቷል " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በስራ ጉብኝት በጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ይገኛሉ።

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ በተካሄደ ስነስርዓት ላይ ለአርባምንጭና ለአካባቢው ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህ ወቅት ስለ ደቡብ አፍሪካ ድርድር ስምምነት የተወሰኑ ሀሳቦችን አንስተው ተናግረዋል።

ምን አሉ ?

- የኢትዮጵያ #ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት ለድርድር አይቀርብም በሚለው በሁለቱም ወገን (በመንግስት እና ህወሓት ማለታቸው ነው) ተቀባይነት አግኝቷል።

- በአንድ ሀገር ወስጥ #ከአንድ መከላከያ በላይ አያስፈልግም በሚለውም ጉዳይ ከስምምነት ተደርሷል።

- በትግራይ ክልል ህገወጥ በሆነ መንገድ የተደረገው ምርጫ በህጋዊ ምርጫ መተካት አለበት የሚለውም በሁለቱም ወገኖች (በኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት) ተቀባይነት አግኝቷል።

- በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ያለው የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው እና አከራካሪ ቦታዎች የሰው ልጆችን ህይወት ሳይጠይቁ በሰላም፣ በድርድር እና በሀገሪቱ ህግ መሰረት ብቻ ምላሽ እንዲያገኙ በሁለቱም ወገኖች መተማመን ላይ ተደርሷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ በደቡብ አፍሪካ በነበረው የሰላም ድርድር ኢትዮጵያ መቶ በመቶ ያቀረበችው ሀሳብ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia