TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ አበባ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከአዲስ አበባ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ሀሳቦች አዲስ አበባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ባህር ዳር፣ መቐለ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ነቀምት ሂዶ እንደሚሰራውና የኔ ናቸው እንደሚለው ሁሉ አዲስ አበባም ተመሳሳይ ነች፤ #የሁሉም ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ነች ብለዋል። #ODP

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማእከላዊ ኮሚቴ ላለፉት 3 ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቋል። #ODP #ኦዴፓ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ODP

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። ማእከላዊ ኮሚቴው ስብሰባውን በአዲስ አበባ ከተማ ነው በማካሄድ ላይ የሚገኘው። የኦዲፒ ማእከላዊ ኮሚቴ በስብሰባውም የፓርቲውን እና የክልሉን መንግስት የስራ አፈፃፀም በመገምገም አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል። በዚህም ኮሚቴው የነበሩ ጥንካሬዎችን እና ድክመቶችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ነው የተባለው። እንዲሁም ማእከላዊ ኮሚቴው በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ተጠቁሟል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ODP

የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በማግኘታቸው ደስታቸውን በመግለፅ ስጦታ አበረከቱላቸው፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ሽልማቱን የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ አባላቱን በመወከል አበርክተዋል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ODP #ADP #SPEDM

ኦዴፓ (የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) እና አዴፓ (አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) በቅርቡ ተግባራዊ ሊደረግ ጫፍ ስለደረሰው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ጥምር እና አጋር ፓርቲዎች ውህደት በተመለከተ ለመወያየት አስቸኳይ ጉባኤ መጥራታቸው ተሰምቷል።

ኦዴፓ ዛሬ ኅዳር 16/2012 አስቸኳይ ጉባዔ የጠራ ሲሆን ኦዴፓ ወህደቱን በተመለከተ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። በተመሳሳይ አዴፓ በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ጉባዔ የጠራ ሲሆን በተመሳሳይ ርዕስ ላይ ለሁለት ቀናት እንደሚወያይ ተልጿል። እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ደኢሕዴን) አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ሐሙስ ኀዳር 18/2012 መጥራቱ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ODP #ADAMA

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) የክልል አመራሮች በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም እና መተዳደሪያ ህገ ደንብ ዙሪያ እየመከሩ ነው። በአዳማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ውይይት በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የኦዲፒ የዞን አመራሮች ተሳትፈዋል።

በምክክር መድረኩ በውህድ ፓርቲው ፕሮግራም፣ በመተዳደሪያ ህገ ደንብና የድርጅቱ አወቃቀር ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ይገኛል። ከዚህ ባለፈም በፓርቲው ዙሪያ በሚነሱ የተለያዩ የግልጸኝነት ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት የሚደረግ መሆኑን ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

(ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia