TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ሜሴንጀር እና ዋትስአፕ በአብዛኛው የዓለም ክፍል በአግባቡ #እየሰሩ_አይደለም። ተጠቃሚዎች ፎቶ እና ቪዲዮ መመልከት እና መጫን አይችሉም። የፌስቡክ ቃል አቀባይ ችግሩ መፈጠሩን አምነው #መፍትሔ_ፍለጋ እየሰራን ነው ብለዋል። ባለፈው መጋቢት ፌስቡክ በሶስቱ መተግበሪያዎች ላይ ተመሳሳይ እክል ገጥሞት ነበር።

Via #EshetBekele
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በሚወዛገቡባት የአቢዬ ግዛት የዘመቱ 860 ገደማ የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ 30 ወታደራዊ ሰራተኞችና የተባበሩት መንግሥታት ፖሊሶች የግዛቲቱን ሰላም እና ፀጥታ ለመስጠበቅ ለነበራቸው ሚና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሜዳይ ተሸለሙ። በአቢዬ የተባበሩት መንግሥታት ጊዜያዊ የጸጥታ ጥበቃ ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴየር ጄኔራል ሙሉ ገብረሕይወት በሽልማቱ ወቅት በአቢዬ የደፈሩ ወታደሮችን አመስግነዋል። የኢትዮጵያ ሴት ወታደሮች የአካባቢው ሴቶች ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት ለተጫወቱት ሚና ተመስግነዋል።

Via #EshetBekele
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደኢህዴን ስብሰባ ተጠናቋል!

በሐዋሳ ሲካሔድ የቆየው የደኢሕዴን ስብሰባ መጠናቀቁን ንቅናቄው አስታውቋል። ደኢሕዴን «በክልሉ እየተነሱ ያሉ የአደረጃጀት ጥያቄ ላይ በተደረገው የጥናት ግኝት ላይ ከሐምሌ 18 ጀምሮ» ስብሰባ ላይ ከርሟል፤ ከደቂቃዎች በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል በ319 ወረዳዎች እና በ19 ከተሞች ከ7 ሺሕ 426 ቀበሌዎች የተውጣጡ ከ57,000 በላይ የቀበሌ አመራሮች ከዛሬ ጀምሮ የ10 ቀናት የአመራር ስልጠና መጀመራቸውን የኦሮሚያ ኮምዩንኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው ተናግረዋል።

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
«የጄኔራል ሰዓረ ገዳይ ወታደር መሳፍንት ጥጋቡ «ስለ ቆሰለ እስካሁን በሕክምና ላይ ይገኛል፣ የቆሰለው አንገቱ አካባቢ ስለሆነና መናገር ስለማይችል አዳዲስ ነገር አልተገኘም። በደንብ ሲሻለው የበለጠ መረጃዎች ይገኛሉ» ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 33 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከየምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ ሕግ 20 አንቀጾች እንዲሰረዙ 13 እንዲሻሻሉ በዛሬው ዕለት ጠይቀዋል ጠይቀዋል። የመንግሥት ሰራተኞች ለምርጫ ሲወዳደሩ ሥራቸውን ሊለቁ ይገባል የሚለው አጨቃጫቂ ሆኗል። ከኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ አቶ ገረሱ ገሳ «የመንግሥት ሰራተኞች መልቀቅ ካለባቸው ከጠቅላይ ምኒስትሩና አፈ-ጉባኤው ጀምሮ መልቀቅ አለባቸው» ብለዋል።

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ፓርቲዎች ከ140-160

የኢትዮጵያ ፓርቲዎች ከ140-160 ደርሰናል እያሉ ነው ሲሉ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ተናግረዋል። ዛሬ ባደረጉት ውይይት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚከፍለው የስብሰባ አበል ለምን ቀረ? የሚለው ዋንኛ አጀንዳ ነበር ተብሏል።

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደቡብ አፍሪካ ካሰረቻቸው 600 በላይ የውጭ ዜጎች 150 ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነቢያት ጌታቸው ተናግረዋል። ጆሐንስበርግ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ግን ቁጥሩን 600 ገደማ ያደርሱታል።

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢሕአዴግ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ፦

ኢሕአዴግ "ዝርዝርና ብስል" ግምገማ አድርጊያለሁ ብሏል። አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንዳሉት ሥራ አስፈጻሚው በኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል አንድነትን የሚጎዱ ነገሮች እንዲታረሙ፣ ፓርቲዎቹም እርስ በርስ #ከመወነጃጀል እንዲቆጠቡ ድምዳሜ ላይ ተደርሷል።

"የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በሙሉ ልብ ሁሉም ወስደው በተመሳሳይ ሁኔታ ያለመፈጸም" ችግር በኢሕዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል መኖሩን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንደደረሰበት አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል። በጋራ የተወሰኑ ጉዳዮች እኩል ተግባራዊ አይሆኑም ብለዋል።

የሕግ የበላይነትን ማስከበር ፣ ለውጡን ተቋማዊ ማድረግ፣ "የለውጡን ምንነት ማስረዳት"፣ በ2012 "ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትኃዊ ምርጫ" ለማካሔድ መዘጋጀት፣ ደኢሕዴን ላሰራው "ሳይንሳዊ ጥናት" ድጋፍ ማድረግ ከኢሕአዴግ ውሳኔዎች መካከል ይገኙበታል።

Via #EshetBekele
@tsegabwode @tikvahethiopia
#የመን

ትናንት - ራሱን የደቡብ የሽግግር ምክር ቤት (southern transitional council) ብሎ የሚጠራው የየመን ተገንጣይ ቡድን በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ድጋፍ ኤደንን ተቆጣጠረ -- #ዛሬ-በሳዑዲ አረቢያ ትዕዛዝ እና ዛቻ ጥሎ መውጣት ጀመረ።

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia