TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና~አዴፓ⬇️

ብአዴን(አዴፓ) ዛሬ ምሽት በሚያካሂደው የማዕከላዊ ኮሚቴነት ምርጫ ባይወዳደሩ ያላቸውን 13 አመራሮች መነሻ አቀረበ፡፡

ድርጅቱ በማዕከላዊ ኮሚቴነት የማይወዳደሩ ብሎ ያቀረበው በትምህርት፣ በአምባሳደርነት እና በክብር የተሰናበቱ የድርጅቱ አባላት በሚል
ነው፡፡

• በትምህርት የሚሰናበቱ አቶ ዓለምነው መኮንን፣አቶ ለገሰ ቱሉ ፣አቶ ጌታቸው ጀምበር፣ አቶ ኢብራሂም ሙሀመድ፣አቶ ደሳለኝ አምባው እና ወይዘሮ ባንቺ ይርጋ መለሰን ባይወዳደሩ ብሎ መነሻ አቅርቧል፡፡

• በክብር ደግሞ አቶ #ደመቀ_መኮንን ፣አቶ ከበደ ጫኔ፣ አቶ መኮንን የለውም ወሰን፣ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው እና አቶ ጌታቸው አምባየን በክብር ቢሰናበቱ ብሎ አቅርቧል፡፡

• በአምባሳደርነት እያገለገሉ ያሉትን አቶ ካሳ ተክለብርሀንና ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰን ከውድድሩ ውጭ ቢሆኑ ብሎ ማዕከላዊ ኮሚቴው መነሻ አቅርቧል፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ያቀረበውን ማሻሻያ ሲያስረዳ በፌዴራል ደረጃ የሚገኙ አመራሮች ካላቸው የስራ ጫና ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው በክልሉ እንዲሰሩ ታሳቢ በማድረግ እና የአመራር መተካካት አስፈላጊ በመሆኑ ብሏል፡፡

ለትምህርት የተላኩት ደግሞ ፓርቲውን በረዥም ጊዜ ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ #ማዕከላዊ ኮሚቴው ይህንን መነሻ ይዞ ቀርቧል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት 13 አመራሮች ለቀጣይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባይወዳደሩ ብሎ መነሻ አቅርቧል፡፡

ዛሬ ምሽት 65 አባላትን ያካተት የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ይመረጣል፡፡

ከተመረጡት ውስጥም 13 ለብአዴን(አዴፓ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ 9 ደግሞ ለኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ይመረጣሉ፡፡የማዕከላዊ ኮሚቴው ምርጫ ከእራት በኋላ ይቀጥላል፡፡

ብአዴን ስያሜውን ወደ #አዴፓ መቀየሩ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ነገ ሐምሌ 06/2011 በባሕር ዳር ስብሰባውን እንደሚጀምር ታውቋል። #ADP #አዴፓ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አፅህሮተ-ስያሜውን ያካተተው ዓርማ ከላይ የምትመለከቱ ነው፡፡ #ADP #አዴፓ

@tsegabwolde @tikvahethiopia