TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ይህ ጉባኤ ትግራይን እና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ አውጥተዋል።

ጉባኤው " በችኮላና የጋራ መግባባት ሳይደረስበት ፤ በማደናገርና በአቋም አልባነት አሰባስበናቸዋል በሚሉት ኔትወርክ  ' ይቃወሙናል ' የሚሉዋቸው የተወሰኑ #አመራሮች_ለማስወገድ በማለም የሚካሄድ ጉባኤ ነው " ብለውታል።

" ይህ ጉባኤ ትግራይን እና ህዝቡን ወደ አደጋ ከመክተት የዘለለ እርባና የለውም " ሲሉ ገልጸዋል።

ምክትል ሊቀመንበሩ  ፤ " የተሻሻለው የፓለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ ህወሓት እንደ አዲስ እንደሚዘገብ የሚያደርግ ፣ ወርቃዊው የትግራይ ህዝብ ትግል የሚያጎድፍ በቀጣይ ቅርቃር ውስጥ የሚከት መሆኑን በመገንዘብ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ በማእከላዊ ኮሚቴ አባላት መግባባት ተደርሶ ነበር " ብለዋል።

" ይሁን እንጂ የተደረሰው መግባባትና መተማመን ወደ ጎን በመተው ' ከፌደራል መንግስት ተማምነናል ' በሚል ማደናገሪያ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመነጋገር  ከማእከላዊ ኮሚቴ እና ካድሬ በመደበቅ የተሄዴበት ሂደት ወዳልተፈለገ ወጥመድ እንድንገባ ተደርገናል " ብለዋል።

" በዚህ ምክንያት የሚፈጠር ማንኛውም ጥፋት ተጠያቂው ለጠባብ ቡድናዊ ፍላጎቱ ብቻ የሚንቀሳቀሰው ቡድን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ፥ " የህዝቡ ሰላም እንዳይደፈርስና እንዳይረበሽ ከህዝባችንና ከመላ አባላችን በመሆን እንታገላለን " ብለዋል።

" ሁሉም የትግራይ አቅሞች በማቀናጀት በተደራጀ ትግል ከፍተኛ ፓለቲካዊ ድርድር በማካሄድ የህወሓት ህጋዊነት በመመለስ ካጠላብን ዙርያ መለስ ፈተና በመውጣት የትግራይ የተሟላ ደህንነትና እድገት እንደሚረጋገጥ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia