TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ደራሲ ፍቅረማርቆስ⬇️

ታዋቂው ደራሲ #ፍቅረማርቆስ_ደስታ ከ9 አመታት ስደት በኋላ አገሩ ገብቷል። ፍቅረማርቆስ ደስታ በደቡብ ውስጥ በሚገኙት #በሃመር ብሄረሰቦች ላይ ተመርኩዞ ከቡስካ በስተጀርባ ከተሰኘው ልቦለድ መጽሃፍ ጀምሮ አያሌ መጽሃፍትን አሳትሟል።

ፍቅረማርቆስ በጎጃም ቢወለድም #በመምህርነት ወደ ሃመር ሄዶ በሃመሮች ባህልና ቱፊት ተማርኮ በባህሉም መሰረት የብሄረሰቡ አባል
ሆኗል።

ፍቅረማቆስ በሃመር ውስጥ እጅግ ተወዳጅ ሰው ነው ለ9 አመታት የተለያቸውን ሀመሮች ለማግኘት #ዛሬ ወደ ሀመር ይበራል።

ፍቅረ ማርቆስ ሀመር ሲደርስ ጠፍቶ የመጣ ሰው ከማህበረሰቡ ጋር ለመቀላቀል #መገረፍ ስላለበት በጎረምሶች ከተገረፈ በኋላ ከማህበረሰቡ ጋር ይቀላቀላል።

©አሀዱ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia