TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ወይኔ አመለጠን ሳንገለው.."‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐብይ_አሕመድ ባለፈው መስከረም 30 ቀን ከነ ትጥቃቸው ወደ ፅሕፈት ቤታቸው የተጓዙ ባለ ቀይ ቆብ ወታደሮች ጋር ተወያይተው ከተለያዩ በኋላ «ወይኔ አመለጠን ሳንገለው የሚሉ ኃይሎች» እንደነበሩ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደሮቹ ወደ ፅሕፈት ቤታቸው የሔዱበት አላማ «ማሻሻያውን #ለማስተጓጎል ነው» ሲሉ ተናግረዋል። ጠቅላይ ምኒስትሩ ይኸን ያሉት በዛሬው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በመንግሥታቸው ሥራዎች እና አንገብጋቢ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ በሰጡት ማብራሪያ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደሮቹ ወደ ቤተ-መንግሥት እንዲያቀኑ ትዕዛዝ ያስተላለፉ አሊያም የሸረቡ አካላት ስለመኖራቸው በግልፅ ባይናገሩም «ያን ያደረጉ በቁጥራቸው ያነሱ ሰዎች ቢሆኑም አብዛኛው ወጣት ስለሆነ ደሞዝ ጭማሪ የሚያገኝ መስሎት ተንጋግቶ የመጣ ነው» ሲሉም ተናግረዋል። ጄኔራል #ሰዓረ_መኮንን ባለፈው ቅዳሜ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ «ግለሰቦች የገፋፉት እና ያርገበገቡት ነው። እነዚህን ግለሰቦች ማን ነው የገፋቸው? የሚለውን አጣርተን #እርምጃ እንወስዳለን።» ብለው ነበር። «የመጡት ሰዎች ሁሉም ክፉ ሐሳብ ነበራቸው ወይ የሚለው የተሟላ ማስረጃ የለም። ቀድሞ ይኸ ችግር እንደሚያጋጥም የሚያውቅ የለም» ሲሉ የተደመጡት ጠቅላይ ምኒስትሩ እርሳቸው «በሳል እና ጠንቃቃ» ያሉትን የአመራር ሥልት ባይከተሉ ኖሮ ጉዳዩ አደገኛ እንደነበር ገልጸዋል። ጉዳዩን ሰፋ አድርገው ሊያብራሩ እንደሚሹ የገለጹት ጠቅላይ ምኒስትሩ «ሁሉ እንኳን ችግር አለባቸው ብለን ብናስብ እና በአየር ወይም በተለየ ኃይል ብንመታ ብንታኮስ እና የተወሰነ ሰው ብንገድል ማሻሻያው ተስተጓጉሏል እንኳ ባንል በራሱ የመከላከያ ኃይል ተቃውሞ የሚገጥመው ማሻሻያ ተብሎ በዓለም ደረጃ ቅቡልነታችንን ገደል ይከተዋል» ብለዋል። ወታደሮቹ ወደ ቤተ-መንግሥት ለመሄድ የወሰኑት «በተበተነ አኳኋን» እንደሆነ የገለጹት ጄኔራል ሰዓረ የተፈጸመው ጥፋት ተራ የዲሲፕሊን ግድፈት እንዳልሆነ ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በብዙ ቅሬታ እና በተሳሳተ መረጃ ወደ ቢሯቸው አምርተዋል ያሏቸውን ወታደሮች #ማረጋጋት ቀዳሚው ሥራ እንደነበር ገልጸዋል። «ሰዎች ፑሽ አፕ ተሰራ ሲባል እንደ ዋዛ አይተውታል» ያሉት ዐብይ በስፖርት ወታደሮቹን ለማስከን መሞከራቸውን አስረድተዋል። በምትኩ ሌላ እርምጃ መንግሥታቸው ቢወስድ መዘዙ የከፋ ሊሆን ይችል እንደነበርም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። በብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ በቀጥታ በተላለፈው ንግግራቸው «ብዙዎች ውጭ ሆነው የሚተርቱትን ተረት ብናደርግ የሚፈጠረው አደገኛ ነው» ያሉት ጠቅላይ ምኒስትሩ «መጀመሪያ ስሜትን አርግበን ከቀዘቀዘ በኋላ ውይይት አካሔድን 'ራሱ እከሌ ቀሰቀሰኝ፤ እከሌ አደራጀኝ' ብሎ አውርቶ ለሕግ እያቀረበ ነው አሁን» ሲሉ የተከተሉትን ሥልት አብራርተዋል።

ጄኔራል ሰዓረ መኮንንም ከወታደሮቹ ድርጊት በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች መኖራቸውን ባለፈው ቅዳሜ ገልጸው ነበር። ጄኔራል ሰዓረ «እስካሁን በቁጥጥር ስር ያስገባናቸው ከፍተኛ አመራሮች አሉ። በቀጣይ ደግሞ በየደረጃው የማጥራት ሥራውን እንቀጥልበታለን» ቢሉም በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች ብዛትንም ሆነ ያላቸውን ወታደራዊ ሥልጣን ግን አልገለጹም።

የልዩ ኃይል አባላቱ «ቤተ-መንግሥት ሲገቡ ትጥቃችሁን ከፈታችሁ በኋላ የሆነ ሰው ሊያነጋግራችሁ ይፈልጋል ሲባሉ ትጥቃችንን አንፈታም» ብለው እንደነበር ያስታወሱት ጄኔራል ሰዓረ ስናይፐር እና ብሬልን ጨምሮ የተለያዩ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ታጥቀው እንደነበር ዘርዝረዋል። «ቀስ አርገን ትጥቃቸውን እንዲፈቱ አደረግናቸው» ያሉት ጄኔራል ሰዓረ በምኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የነበሩት ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አሕመድ እንዳገኟቸውም ገልጸዋል። ኩነቱ «ጥይት ሳይተኮስ፤ ሰው ሳይሞት» እልባት ማግኘቱን የገለጹት ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አሕመድ ግን የከፋ ኹኔታ ሊፈጥር ይችል እንደነበር በዛሬው ዕለት በይፋ ተናግረዋል። በዕለቱ ጉዳዩን ለጋዜጠኞች ሲያብራሩ «በከፍተኛ መዝናናት እና መሳቅ» እንደነበር ያስታወሱት ዐብይ «ውስጤ እርር ድብን እያለ» ሲሉ ትክክለኛ ስሜታቸው የተለየ እንደነበር አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ «ከቡራዩ፣ ከሰበታ፣ ከለገጣፎ አርሶ አደር ወጣት መንግሥታችን ተነካ ብሎ ሊዋጋ ተደራጅቶ እየመጣ ነው» ሲሉ ሕዝቡን ለማረጋጋት መሞከራቸውንም አስረድተዋል። የዕለቱን ኩነት «አቃለን አንመልከተው» ያሉት ዐብይ «በነገራችን ላይ ወይኔ አመለጠን ሳንገለው የሚሉ ኃይሎች ነበሩ» ሲሉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ምኒስትሩ «ሳንገለው አመለጠን» ብለዋል ያሏቸው ኃይሎችን ማንነት ግን በግልፅ አልጠቀሱም። የተባሉት «ኃይሎች» #በመከላከያ_ሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ ስለመሆናቸውም ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአገር መከላከያ ሰራዊት ባለፉት 100 ቀናት ኢትዮጵያ ውስጥ #ምርጥ ስራ ከሰሩ ተቋማት መካከል ዋነኛው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ባለፉት አመታት ኢትዮጵያን ከልዕልናዋ ለማውረድና ለመድፈር ተሞክሮ የመከላከያ ሰራዊቱ ሰንፎ ያሳለፈበት ጊዜ የለም። ባለፉት ወራት ክልሎች ሰላምን ለማረጋገጥ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ምክንያት ችግሮች ሲገጥሟቸው ሰራዊቱ ገብቶ #መስዋእትነት በመክፈል #ማረጋጋት መቻሉንም አስታውሰዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia