TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማትና_እውቅና_ፈቃድ_የተሰጣቸው_የትምህርት_መስኮች.pdf
6 MB
#ETA

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም ድረስ ያጠናቀራቸውን አጠቃላይ የ350 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት መስኮቻቸውን የእውቅና ፈቃድ የሚገልጽ የተሟላ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

ከ350ው 330ዎቹ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ 20 ተቋማት በርቀት ትምህርት እውቅና የተሰጣቸው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በክልል መንግስታት የሚተዳደሩ ተቋማት ይገኙበታል።

የእውቅና ፈቃድ ባልታደሰባቸው የትምህርት መስኮች #አዲስ_ተማሪ_መቀበል_እንዳይችሉ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

ይፋ የተደረገው መረጃ እስከ የካቲት ወር ድረስ ያለውን የእውቅና ፈቃድ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል።

በሂደት ላይ ያሉ የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄዎች ውሳኔ ሲያገኙ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የእውቅና ፈቃድ ሲሰረዝና በሌሎች ምክንያቶች የውሳኔ ለውጦች በሚኖሩበት ወቅት የመረጃ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል አሳውቋል።

በመሆኑም ፦
- ተማሪዎች፣
- ወላጆች፣
- ቀጣሪና የሙያ ፈቃድ የሚሰጡ ድርጅቶች ፣
- የሚዲያና ማስታወቂያ ተቋማት ፣ እንዲሁም መላው ህብረተሰብ የተቋማቱን ወቅታዊ መረጃ በመከታተል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ በጥብቅ አሳስቧል።

ተቋማት ይፋ ከተደረገው የእውቅና ፈቃድ መረጃ ውጪ ተማሪ ተቀብለው ቢያስተምሩ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ባለስልጣኑ አሳውቋል፡፡

ይፋ በተደረገው መረጃ የማስተካከያ ጥቆማ የሚኖራቸው ተቋማት በህጋዊ ተወካዮቻቸው በኩል ለባለስልጣኑ ማሳወቅ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

[ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና እውቅና ፈቃድ የተሰጣቸው የትምህርት መስኮች ከላይ በ #PDF ተያይዟል ]

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
#ETA

የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አሁን በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ እንዲልኩ አሳሰበ።

ባለሥልጣኑ አሁን በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የተመዘገቡበትን አግባብ ማየት አስፈላጊ ሆኖ በማግኝቱ እውቅና በሰጣቸው የትምህርት መስኮች በትምህርት ላይ የሚገኙ የተማሪዎችን የስም ዝርዝር የያዘ መረጃ በሶፍትና በሀርድ ኮፒ በማጠናቀር በ30 ቀናት ውስጥ እንዲልኩ አሳስቧል፡፡

የሚላከው የተማሪዎች መረጃ #በፕሬዝዳንት ወይም #በበላይ_ኃላፊ ተፈርሞ መውጣት እንዳለበት ከዚህ ውጪ ፈራሚ አካል ካለ ስምና ኃላፊነት የሚገልጽ ደብዳቤ በነዚሁ የበላይ ኃላፊዎች እንዲገለጽ እና የተማሪዎችን መረጃ በተናጥል በሚልኩ ተቋማት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

(ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመረቁ)

የአፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የመንግስትም ሆነ የግል  ቀጣሪ  ድርጅቶች ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመራቂ ሠራተኞቻቸው እና አዲስ ሰራተኞች ከመቅጠራቸው በፊት የተቀጣሪዎች የትምህርት ማስረጃዎች ህጋዊነትና ትክክለኛነት መረጋገጥ ይኖርበታል ብሏል።

ተገልጋዮች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በኩል ይህን አገልግሎት ለማግኘት ወደ ባለሥልጣኑ ከመምጣታቸው በፊት የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት አገልግሎቱን ማግኝት  ይችላሉ ብሏል።

1. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ዲግሪ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤

2. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ትራንስክሪፕት/Student Copy/ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤

3. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘ ኦሪጅናል ዲፕሎማ ወይም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤

4. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ከሆነ በትምህርት ምዘናዎችና ፈተናዎች አገልግሎት ድርጅት ትክክለኛነቱ  የተረጋገጠ  ከኮፒ  ጋር በማያያዝ ፤

5. ዲግሪውን  ለመማር  በመግቢያነት  የተያዘው  ዲፕሎማ  ከሆነ  ዲፕሎማው  በተገኘበት ክልል የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ወይም የዞን/የከተማ መስተዳደር የስራና ስልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ እንዲሁም  የደረጃ  4  ብቃት  ማረጋገጫ(COC) ካገኙበት ማዕከል የተረጋገጠ መሆን አለበት  ከኮፒ  ጋር በማያያዝ እና

6. የስም ለውጥ ካለ የፍርድቤት ውሳኔ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ናቸው፡፡

የማስተርስ ዲግሪ ለማረጋገጥ በቅድሚያ የመጀመሪያው ዲግሪ ከላይ በተገለጸው መንገድ መረጋገጥ ሲል ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳስቧል።

#ETA

@tikvahethiopia
#ETA

" ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም "

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፤ ባዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይም የስልጠና ተቋማት በሁሉም መርሃ ግብሮች #የሕግ እና #የመምህርነት ትምህርት ዘርፎችን #አሁንም ማስተማር እንደማይችሉ ተገልጿል።

ከዚህ በፊትም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁሉም መርሃግብሮች የሕግ እንዲሁም የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ የተደረገ ሲሆን አሁንም በአዲሱ መመሪያ የሕግ እና የመምህርነት ትምህርት መስጠት አይችሉም ተብሏል።

ሌሎች በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ #ረቂቅ መመሪያ ላይ ምን ተካቷል ?

- ማንኛውም ተቋም አዲስ ፕሮግራም ለመከፈት ወይም ነባሩን ፕሮግራም ለማስቀጠል የፍላጎት ዳሰሳ፣ የገበያ ጥናት እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውደ ጥናት ማካሄድ ይኖርበታል፡፡

- ለማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፕሮግራም ፈቃድ የሚሰጠው ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል፡፡

- የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከፍቷቸው ፕሮግራሞች ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን የመመዘኛ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

- ለማንኛውም ተቋም የሚሰጥ ፈቃድ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ተገምግሞ ለተፈቀደለት ካምፓስና የትምህርት መስክ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም ተቋም የጤና የትምህርት መስኮችን መስጠት የሚችለው በመደበኛ መርሃ ግብር ብቻ ይሆናል፡፡

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ማስተማር የሚችለው ከድንበር ተሻጋሪ ወጪ በመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም፡፡

- ማንኛውም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም የትኛውንም ስልጠና በርቀት መርሃ ግብር ለማሰልጠን የሚቀርብ የፈቃድ ጥያቄ የማይስተናግድ ይሆናል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም #በህክምና_ዶክትሬት እና #በስፔሻሊቲ ትምህርት ፈቃድ ለማግኘት ተቋሙ #የህክምና_ሆስፒታል ሊኖረው ይገባል።

- በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ ጊዜው ሳያበቃ የስርዓተ ትምህርት ወይም የዲግሪ ስያሜ ለውጥ ካለባለስልጣኑ ፈቃድ ወጪ ማድረግ አይችልም።

- በሀገር ደረጃ በትምህርት ፖሊሲ ስርዓተ ትምህርቱ እስካልተቀየረ ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ወይም በካምፓስ ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ/ፈቃድ እድሳት ጊዜው እስካላበቃ ድረስ በሌሎች ካምፓሶች መተግበር ወይም መጠቀም ይችላል።

- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበየነ መረብ ወይም በርቀት ትምህርት መርሃ-ግብር ፈቃድ ሲጠይቁ በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ስርዓተ-ትምህርቱ ቀድሞ መገምገም እና ተገቢ ማስተካከያ ተደርጎ መፅደቅ ይኖርበታል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በብሎክ ኮርስ ትምህርት ለመስጠት ያለው አመቺነትና ተገቢነት እንዲሁም የትምህርት ጥራት ላይ የሚኖረውን ተፅህኖ ከግምት በማስገባት ስርዓተ ትምህርቱ ከጸደቀ በኃላ ሊተገብር ይችላል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መሪ አስፈፃሚ ሕይወት አሰፋ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አልተገኙም " - ባለስልጣን መ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ አስጠንቅቋል። የግል እና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞዴል የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ከዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም መሰጠት ተጀምሯል፡፡…
#ETA

ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በድጋሚ ማሳሰቢያ ተሰጣቸው።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ወደሚያስፈትኑበት የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመሔድ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያጠናቅቁ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በድጋሜ አሳስቧል።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የሚያስፈትኗቸውን ተማሪዎች ፦

- ፎቶ፣
- የይለፍ ቃል፣
- የተጠቃሚ ሥም እና የትምህርት ቤት ህጋዊ መታወቂያ በመያዝ ወደተመደቡበት ተቋም በመሔድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አስታውሷል።

ባለስሥልጣን መስሪያ ቤቱ ፤ በአሁኑ ወቅት ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረሶኛል ባለው መረጃ መሰረት ከላይ የተዘረዘሩ ጉዳዮችን በማሟላት ያቀረቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አነስተኛ ናቸው።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ አላስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ባለማሟላታቸው ምክንያት ተማሪዎች ለፈተና የማይቀመጡበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ባለሥልጣኑ ገልጿል።

በዚህም ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊነት የሚወስዱ መሆኑን ባለሥልጣኑ ጠቁሟል።

(ባለሥልጣኑ ዛሬ ያወጣው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)

Via @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ 87 በመቶ የሚሆኑት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የዘንድሮውን የመውጫ ፈተና ማለፍ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ገልጸዋል።

የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል ማሳለፍ የቻሉት 13 በመቶ ብቻ ነው ብለዋል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ ማሳለፋቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል።

#ETA

@tikvahethiopia