TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቴዎድሮስ ካሳሁን⬆️

ለአዲስ አመት #ዋዜማ በሚሊኒም አዳራሽ ሊያደርገው የነበረው ኮንሰርት የተስተጓጎለበት #ቴዲ_አፍሮ አሁን መስከረም 5 ቀን 2011 ኮንሰርቱን ለማድረግ መወሰኑ ታውቋል፡፡

በዚህ መሰረት በትላንትናው እለት ለሚሊየም አዳራሽ አስፈላጊውን ክፍያ መፈፀሙ ታውቋል፡፡

ቴዲ ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሚሊኒየም አዳራሽ የሙዚቃ ኮንሰርቱን ለማቅረብ ጠይቆ አዳራሹ ለሌላ #ፕሮግራም ይፈለጋል ተብሎ #ሳይፈቀድለት መቅረቱ ይታወሳል።

©z
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሲዳማ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ ዐመታዊ በዓል በሀወሳ ከተማ በመከበር ላይ ነው፡፡ በበዓሉ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሸመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ ተገኝቷል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድም ለሲዳማ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ፊቼ ጨምበላላን የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በልዩ ባህላዊ ቅርስነት መዝግቦታል፡፡ በተያያዘ ዜና የብሄረሰቡ መብት ተሟጋቾች “የሲዳማ ሜዲያ ኔትወርክ” የተሰኘ የሳተላይት ቴሌቪዥን ሥርጭት ዛሬ መጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡

Via #ዋዜማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በቀድሞው የአዲስ አበባ መንገዶች ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ፍቃደ ኃይሌ ላይ የከፈትኩትን የሙስና ወንጀል ክስ አቋርጫለሁ ብሏል፡፡ ሪፖርተር እንዳስነበበው ከሥራ አስኪያጁ ጋር ተከሰው የነበሩት ሙሉጌታ አብርሃ (ኢንጅነር)፣ አህመዲን ቡሴር (ኢንጅነር)፣ ዋስይሁን ሽፈራው (ኢንጅነር) የተባሉ የሥራ ሃላፊዎችና እስራኤላዊው ሜናሼ ሌቪ ጭምር ክሳቸው ተቋርጦላቸዋል፡፡ ግለሰቦቹ በግንቦት 2009 ዓ.ም ከመንገድ ግንባታ ጋር በተያያዘ ከ198.9 ሚሊዮን ብር በላይ በመንግሥት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል ነበር በቁጥጥር ስር ውለው የተከሰሱት፡፡ ተከሳሾቹ ቀደም ሲል የጉዳቱን መጠን ከፍለው እንዲፈቱ ሲጠየቁ አልተስማሙም ነበር- ብሏል ዘገባው፡፡

Via #ሪፖርተር/#ዋዜማ
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ችሎት

ትናንት ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት የወሰነላቸው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላትና አመራሮች አልተፈቱም፡፡ ምክንያቱ ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ በመጠየቁ ነው- ብሏል አብን በፌስቡክ ገጹ፡፡

በተያያዘ ዜና...

ፖሊስ የአማራ ተማሪዎች ማኅበር ጸሃፊ #ሮዛ_ሰለሞንን ፖሊስ ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧታል፡፡ ዐቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት እከሳታለሁ በማለቱ ችሎቱ 28 የምርመራ ቀናት ፈቅዷል፡፡ ፍርድ ቤት በሌላ ችሎት “በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ” የተከሰሰው የአሥራት ቴሌቪዥን ባልደረባ ጋዜጠኛ በሪሁን አዳነ፣ ዳኛ ይነሱልኝ ሲል ያቀረበውን አቤቱታ ችሎቱ ዛሬ ውድቅ ያደረገበት ሲሆን፣ ያለ አሳማኝ መነሻ አቤት ብሏል በማለትም የ300 ብር መቀጮ እንደጣለበት አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡

Via #AddisStandard/#ዋዜማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ለግብፅ ጫና ትንበረከክ እንደሁ ይለያል!

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሀ አሞላል ላይ ከነገ እሁድ መስከረም 4 2012 አ.ም ጀምሮ እስከ ሰኞ ድረስ የግብጽ ; የሱዳንና የኢትዮጵያ ውሀ ሚኒስትሮች በካይሮ ይወያያሉ።የኢትዮጵያ የውሀ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለም ለዚሁ ጉዳይ ወደ ካይሮ የሚያቀኑ ይሆናል። ሱዳንም አዲስ ባገኘችው የውሀ ሚኒስትር ያሲር አባስ መሀመድ ተወክላ የኢትዮጵያን ጨምሮ ከግብጹ የውሀ እና መስኖ ሚኒስትር መሀመድ አብደል አቲ ጋር ነው ውይይቱ የሚደረገው።

የካይሮው ስብሰባ ምናልባትም በህዳሴው ግድብ የውሀ አሞላል ላይ የስምምነት ፊርማ ሊካተትበት እንደሚችል ምንጮቻችን ነግረውናል።ሆኖም ኢትዮጵያን የወከሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ቢቻል በግድቡ ውሀ አሞላል ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብር አዲስ ሀሳብ ቢያቀርቡ ካልሆነ ደግሞ አሁን ለውይይት የተያዘው አጀንዳ ላይ በፍጹም ከስምምነት መድረስ የለባቸውምም ብለውናል።

ነገ በካይሮ በህዳሴው ግድብ ውሀ አሞላል ላይ ውይይት የሚደረገው የግብጹ የውሀ ሚኒስትር መሀመድ አብደል አቲ ከወር በፊት የሀገራቸውን እቅድ ካቀረቡ በሁዋላ ነው። አብደል አቲ በዚህ ባቀረቡት ሰነድ ውስጥ ኢትዮጵያ ግድቡን በሰባት አመት እንድትሞላ የሚጠይቅና ሌሎች ሀሳቦችም የተነሱበት ነው። በኢትዮጵያ በኩልም እነዚህ የካይሮ ፍላጎቶች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን የሚያሳዩ ምላሾች ተሰጥቷቸዋል። እነዚህ በእንዲህ እያሉ ነው የነገው የሶስትዮሽ ውይይት የሚካሄደው።

#ዋዜማ_ሬድዮ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-14-8