TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

የህዝቡን #ደህንነት እና #ሰላም ለመጠበቅ ሲል መንግስት አስፈላጊውን #እርምጃ እንደሚወስድ የፌደራል ፖሊስ ገለፀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይ የመንግስት ትእግስት #ገደብ እንዳለው በመግለፅ #ጉልበተኞችን እንደማይታገስ አስታውቀዋል።

አሁን ላይ እየተስተዋሉ ያሉት #ሁከቶች #በሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች ስም የተቀነባበሩ መሆናቸውን ኮሚሽነር ጀነራሉ ጠቁመዋል።

ባለፉት ሦስት ቀናት በቡራዩና አካባቢው ብዛት ያላቸው ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በመጠቆም፥ በተለያዩ ቦታዎች ተዘርፈው የነበሩ ንብረቶችን የማሰባሰብ ስራ መሰራቱንም ነው ያስታወቁት።

በአጠቃላይም በቡራዩ ከ300 አስከ 400 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ሲያዙ በአዲስ አበባ ደግሞ ከ300 በላይ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ #ገንዘብ ተከፍሏቸው ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት እንዲሁም ብሄርን መሰረት ያደረጉ ስድቦችንም ጭምር በማሰራጨት #የተጠረጠሩ ግለሰቦች መያዛቸውንም አንስተዋል።

ይህ ድርጊት #በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባና በአርባ ምንጭ መታየቱን ጠቅሰዋል።

ኮሚሽነሩ በቡራዩና አካባቢው የተፈፀመውን ግድያ ለማውገዝ በርካታ ሰላማዊ ሰው መውጣቱን ጠቅሰው #የተወሰኑ ቡድኖች ግን አዝሚሚያቸው ሌላ ነበር ብለዋል።

ከእነዚህ የተወሰኑ ግለሰቦች መካከልም #ቦምብ ይዘው የነበሩ በህብረተሰቡ ትብብር መያዛቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በፒያሳና በመርካቶ #ለዝርፊያ የሚቃጡ ግለሰቦች እንደነበሩ ነው የጠቀሱት።

የተወሰኑት የጸጥታ ኃይሎች ደግሞ ጠብመንጃ ለመንጠቅ ሙከራ ያደረጉ ሲሆን በዚህም ከጸጥታ ኃይሉ ጋር #ግብግብ ገጥመው ነበር ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ የአምስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ይህ ግርግር ሆን ተብሎ የተጀመረውን ለውጥ #እንዳይሳካ #ታስቦበት የተከናወነ መሆኑን ነው ያነሱት።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ🔝

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ #በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ከፍተኛ የምክክር ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትራፊክ አደጋ...

#አርባምንጭ

በአርባምንጭ ከተማ #በዛሬው_ዕለት በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የሰው ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

Via Gamo Zone Administration public Relation office

•ወገኖቼ መነጋገር አለብን! እንደወጣን እየቀረን ነው! በየቦታው በየከተማው በትራፊክ አደጋ ብዙ ዜጎቻችን እያለቁ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ #በአርክቴክቸር የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን ተማሪዎች #በዛሬው ዕለት #አስመርቋል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሙስጠፌ ተሸለሙ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን #በዛሬው ዕለት ለሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ መሐመድና ለባልደረቦቻቸው ሽልማት አበርክታለች።

ዛሬ በጅግጅጋ በተካሄደው የኦሮሞና የሶማሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ ላይ የተገኙት የቤተክርስቲያኗ አባቶች ለአቶ ሙስጠፋና ለባልደረቦቻቸው የቤተክርስቲያኗን የክብር ካባ ሸልመዋቸዋል።

ቤተክርስቲያኗ ለአቶ ሙስጠፋና ለባልደረቦቻቸው ሽልማቱን ያበረከተችው በተለይ አዲሱ የክልሉ አስተዳደር ለሰላም ላላው ቁርጠኝነት እውቅና ለመስጠት እንደሆነ በቤተክርስቲያኗ የሶማሌ ክልል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ መቃሪዎስ ገልጸዋል።

ባለፈው ዓመት በጂግጂጋና አካባቢው በተነሳው ረብሻ በርካታ አብያተ ክርስቲያንና የሃይማኖት አባቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወሳል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከአራት ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሬት ሊዝ ጨረታ መውጣቱን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአራት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሬት ሊዝ ጨረታ ያወጣ ሲሆን ለጨረታ የቀረቡት ይዞታዎች መነሻ ዋጋ ከፍተኛው 2,213 ብር መሆኑ ታውቋል። የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓም…
#Update #የመሬት_ሊዝ_ጨረታ

" በ7 ክ/ከተሞች የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ከአፍታ ቆይታ በኃላ ይለያሉ " - የአ/አ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ላለፉት አምስት ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የመሬት ሊዝ ጨረታ ዛሬ አስጀምሯል።

ይህንንም ተከትሎ ቢሮው በሁሉም ክፍለ ከተሞች 14 ነጥብ 13 ሄክታር መሬት በሊዝ ለማጫረት ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በጨረታ የቀረበው መሬት አገራዊ ፋይዳ ላላቸው ለተለያዩ ዓላማዎች የሚውል ነው ተብሏል።

በአስራ አንዱ ክፍለ ከተሞች 24 ሺህ የጨረታ ሰነዶችን በማዘጋጀት ባለፋት አስር ቀናት 21 ሺህ 636 የሚሆኑት የጨረታ ሰነዶች መሸጥ መቻሉም ተጠቁሟል።

የመጀመሪያው ጨረታ #በዛሬው ዕለት በ7 ክፍለ ከተሞች ፦
👉 በቦሌ፣
👉 በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣
👉 በልደታ፣
👉 በአዲስ ከተማ፣
👉 በቂርቆስ፣
👉 በጉለሌና በየካ ክፍለ ከተሞች ተጀምሯል።

በእነዚህ ክፍለ ከተሞች 2 ሺህ 852 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ወደ ጨረታ ሳጥኑ አስገብተዋል።

የጨረታ ሂደቱ አሁን በመካሄድ ላይ ሲሆን አሸናፊዎች ከአፍታ ቆይታ በኋላ የሚለዩ ይሆናል።

በቀጣዮች ቀናት የጨረታ ሒደቱ በሌሎች ክ/ከተሞች እንደሚቀጥል ታውቋል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሺርካ ✦ " 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ✦ " ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር እናቶች ይገኙበታል " - ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ (ለቪኦኤ) ✦ " ጥቃቱን ያደረሰው አሸባሪው ሸኔ ነው " - የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን (ለቪኦኤ) ✦ " እኛ…
#Update

ቤተክርስቲያኗ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በጥብቅ እንደምታወግዝና የጸጥታ ተቋማትም ጥቃት እንዲከላለሉ ጥሪ አቀረበች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ፦
- በሶሌ ሚካኤል፣
- በዲገሎ ማርያም፣
- በሮቤ እንደቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት 36 ኦርቶዶክሳዊያን በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጿል።

በዚሁ ጥቃት በሶሌ ዲገሉ እና ጢጆ ለቡ በተባሉ ቀበሌዎች 28 ኦርቶዶክሳዊያን ከየቤታቸው #ተለቅመው መገደላቸውን ፤ ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ ሴቶችና 21ዱ ወንዶች መሆናቸው መታወቁን አመልክቷል።

በዚህ ጥቃትም እድሜያቸው ከሰባ ዓመት አዛውንት እስከ ሃያ ስምንት ቀን ጨቅላ ሕጻናት እንደሚገኙበት ገልጿል።

#በዛሬው_ዕለት ደግሞ በዲገሉ ማርያም ቤተክርስቲያን 5 ኦርቶዶክሳዊያን መገደላቸውንና የሦስት ኦርቶዶክሳውያን ቤት መቃጠሉን አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም ቤተክርስቲያን በዓለ ማርያምን አክብረው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ 3 ኦርቶዶክሳዊያን ጨለማን ተገን ባደረጉ ነፍሰ ገዳዮች መገደላቸውን ፅ/ቤቱ አስታውሷል።

የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ በሚፈጸመው የኦርቶዶክሳዊያን ጥቃት ዙሪያ በጋራ እየሠሩ እንደሚገኙ የገለፀው ፅ/ቤቱ  " በዚህ ዐይነት የጥቃት ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አንዳንድ አካላት ላይ በመንግሥት በኩል የማያዳግም #ርምጃ_እንደተወሰደባቸው ሀገረ ስብከቱ በላከው ሪፖርት ማረጋገጡን አመልክቷል።

ይህ ዐይነት ሃይማኖት ተኮር ጥቃት በምእመናን ላይ መድረሱ አግባብነት የሌለውና እምነትን በነጻነት የማራመድ መንግስታዊ መብትን የሚጥስ ነው ያለው ፅ/ቤቱ ፤ መሰል ሕገ ወጥ ጥቃትን ለመከላከልና ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት መብቶቻቸውን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ማስከበር እንዲችሉ  ያቋቋሙት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ድርጊቱን በማውገዝ ችግሩ ከመሠረቱ እንዲፈታ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር መፍትሔ መፈለግ ሲገባው በዝምታ በማለፉ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ቅሬታ እንደተሰማት ገልጿል።

" ኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠረ ግድያ እንዲቆምና የወንጀሉ ፈጻሚዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ በሀገረ ስብከቱ ጥረት እየተደረገ ነው " ያለው ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመሆን ፅ/ቤቱም ጉዳዩን የሚከታተለው መሆኑን አሳውቋል።

በሌሎች ስፍራዎች የሚያጋጥሙ ተመሳሳይ ጥቃቶችን በእንጭጩ ለመቅጨትና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ ማበጀት ይቻል ዘንድ አህጉረ ስብከት ችግሮች በሚያጋጥሙ ወቅት በፍጥነት በማሳወቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopia