TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሶማሌ ክልል

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞ ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሃመድ ዑመር በተጨማሪ ሌሎች ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳባቸው 6 የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት የቀድሞ የክልሉን ፕሬዝዳንት አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ የ7 ከፍተኛ አመራሮችን #ያለመከሰስ መብት እሁድ እለት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤው ማንሳቱ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት የክልሉ ቁልፍ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል በተለይም ለFBC አስታውቀዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች በፍጥነት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡና ሌሎች በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው የክልሉ አመራሮችን በፍጥነት በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚሰራም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተጨማሪ በአብዲ መሃመድ ዑመር እንደተቋቋመ የሚነገርለት “ሄጎ” የወጣት ቡድን አባላትና አመራሮች፤ እንደዚሁም ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሰዎች ዝርዝር በማዘጋጀት የመለየት ስራ መሰራቱንም ኮሚሽነር ዘይኑ አስታውቀዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት የክልሉ የቀድሞ ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሃመድ ዑመር በክልሉ ፈፅመውታል ተብለው የተጠረጠሩባቸውን ወንጀሎች በተመለከተ ላለፉት 15 ቀናት በክልሉ የኢሶህዴፓ አመራሮች፣ የክልሉ ምሁራን፣ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ውይይት የተካሄደ ሲሆን፥ በአመራሩ መሪነት አሰቃቂ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙ በውይይቱ ጎልቶ ወጥቷል።

ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ባለፈም አቶ አብዲ የህዝብን ሃብት ለግል ጥቅም በማዋል፣ በከፍተኛ ዝርፊያ፣ የመንግስት አሰራርን ወደ ጎን በመተው የህዝብ ሃብት በግለሰቦች እንዲዘረፍ በማድረግና በሌሎች በርካታ ወንጀሎች መጠርጠራቸውን ኮሚሽነር ዘይኑ ተናግረዋል።

የአብዲ መሃመድ ዑመር በቁጥጥር ስር መዋል ለኢትዮጵያ ብዙ ትርጉም እንዳለው የተናገሩት ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል፥ ህዝብን በድሎ፣ የሰብዓዊ መብትን ረግጦ፣ የህዝብን ስልጣን ለግል ጥቅምና ዝና ከማዋልም ባለፈ ሰውን #በመግደልና መስዋዕት በማድረግ በስልጣን እቆያለሁ ብሎ ማሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ የማይቻል መሆኑን ያመላክታል ብለዋል።

ከዚያም ባለፈ የአቶ አብዲ መሃመድ በቁጥጥር ስር መዋል በኢትዮጵያ ውስጥ የህግ የበላይነት የማክበርና የማስከበር ጉዳይ ከጊዜ ወደጊዜ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ከመጠቆሙም ባለፈ የህግ የበላይነት አይመለከተንም ብለው የሚያስቡ ሰዎች ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚያደርግ መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

©ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦቦ ዳውድ ኢብሳ⬇️

በሀገሪቱ አየታየ ያለው ለውጥ እንዳይደናቀፍ ጥያቄዎች #በሰላማዊ መንገድ ሊቀርቡ አንደሚገባ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ገልጸዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ #ዳውድ_ኢብሳ ከfbc ጋር በነበራቸው ቆይታ ለውጡ እንደዚህ ቀደም ለውጦች በጅምር እንዳይቀር ሁሉም የየበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በተለይም ወጣቱ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎችንም ሆነ ቅሬታዎች ሲገልጽ፥ ህግና ስርዓትን በተከተለና የሌሎችን መብት በማክበር ብቻ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ይህ ካልሆነ ብዙ #መስዋትነት የተከፈለበት ለውጥ ከግቡ ሳይደርሰ ሊጨናገፈና ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ሊወስድ እንደሚችል ነው አቶ ዳውድ የተናገሩት።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወደ ሀገር የገባውም #ልዩነትን ለማጥፋት እንዳልሆነ የገለጹት ሊቀመንበሩ የሰው ልጆች እስካሉ ድረስ ልዩነቶች መኖራቸውንም አስረድተዋል።

ይሁን እንጂ ልዩነቶን #ለማጥበብ በተረጋጋ መንፈስና በሰከነ አካሄድ ውይይቶችን ማድረግ እደሚየስፈልግ ተናግረዋል ተናግረዋል።

ሰውን #በመግደልና ንብረትን በማውደም ልዩነት ይሰፋል እንደሆነ እንጂ የማይጠብ መሆኑንም ያመላከቱት የግንባሩ ሊቀመነበር ይህንን አይነት ድርጊት መቼም ቢሆን ድርጅታቸው የማይደግፍና የማይቀበል መሆኑን አስገንዝበዋል።

አብዛኛው ህዝብ ለውጡን እንደሚፈልገው የተናገሩት የኦሮሞ ነጻነት ግናባር የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

እንደ አቶ ዳውድ ገለጻ አብዛኛው ህዝብ ለውጡን እንደሚፈልገው ሲሆን፥ የኦሮሞ ነጻነት ግናባር እና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

መስዋትነት የተከፈለውም የሰባዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበርና ለመስጠበቅ መሆኑንም አመላክተዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia