TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ፓስፖርት

ከዓለም አገራት ፓስፖርቶች ሁሉ ሴንጋፖር ፓስፖርት " ጠንካራው " ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ፓስፖርት ደግሞ ከነበረበት ደረጃ መሻሻል አሳይቷል።

ከዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር / ሄንሌይ እንደተገኘው መረጃ የሲንጋፖር ፓስፖርትን የያዙ ሰዎች ከ227 መዳረሻዎች 192 ወደሚሆኑት ያለ ቪዛ ለመጓዝ በማስቻል ከሁሉ ልቆ ተገኝቷል።

በዓለም ካሉ ደካማ ፓስፖርቶች መካከል የሚመደበው የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከዚህ ቀደም ከነበረበት 97ኛ ደረጃ ጥንካሬው ተሻሽሎ ወደ 89ኛ ከፍ ብሏል።

የሀገራት የፓስፖርት ደረጃ ምን ይመስላል ?

- በጥንካሬው አንደኛ ደረጃ የተቀመጠው የሲንጋፖር ፓስፖርት ነው። ከ227 መዳረሻዎች ወደ 192ቱ ያለ ቪዛ ማስገባት ይችላል።

-  የጀርመን፣ የጣሊያን እና የስፔን ፓስፖርትን የያዙ ተጓዞች ወደ 190 መዳረሻዎች ያለ ቪዛ መጓዝ ይችላሉ።

- ጃፓን ለበርካታ ዓመታት ቁጥር አንድ ባለ ጠንካራ ፓስፖርት የነበራት ሲሆን አሁን ላይ ከኦስትሪያ፣ ከፊንላንድ፣ ከፈረንሳይ፣ ከላክሰመበርግ፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከስዊድን ጋር በእኩል 189 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

- ዩናይትድ ኪንግደም 4ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጠ አሜሪካ ደግሞ 8ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ፓስፖርት ደረጀ . . .

ከዚህ ቀደም ድርጅቱ ባወጣው የደረጃ ሰንጠረዥ የኢትዮጵያ ፖስፖርት ከ109 ፓስፖርቶች ጋር ተነጻጽሮ በ46 ነጥብ 97ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ነበር።

በ2023 ሦስተኛ ሩብ ዓመት ሪፖርቱ ላይ የኢትዮጵያ ፓስፖርት በ47 ነጥብ 14 ደረጃዎችን አሻሽሎ ከ103 ፓስፖርቶች 89ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ይህ ማለት የኢትዮጵያን ፓስፖርት የያዙ ተጓዦች አሁን ላይ ቀድሞ ቪዛ ሳያስፈልጋቸው ወደ 47 መዳረሻዎች መጓዝ ይችላሉ ማለት ነው።

ደካማዎቹ ፓስፖርቶች የትኞቹ ናቸው ?

አፍጋኒስታን፣ ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ፓኪስታን እና የመን አምስቱ እጅግ ደካማ ፓስፖርት ያላቸው አገራት ሆነዋል።

ከአፍሪካ ደካማ ፓስፖርት ያላቸው 10 አገራት፦
- ሊቢያ
- ሱዳን
- ኤርትራ
- ደቡብ ሱዳን
- ናይጄሪያ
- ኢትዮጵያ
- ጅቡቲ
- ላይቤሪያ
- ኮንጎ ሪፓብሊክ እና ቡሩንዲ ናቸው።

ሄንሌይ ደረጃው እንዴት ነው የሚያወጣው ?

ሄንሌይ የፓስፖርቶችን ጥንካሬ የሚለካው፤ ተጓዦች በያዙት ፓስፖርት ምክንያት ቪዛ ቀድመው ሳያስፈልጋቸው ወደ ስንት አገራት መጓዝ ይችላሉ የሚለውን በማጤን ነው።

ቀድሞ ቪዛ አለማስፈለግ ማለት ወደ መዳረሻ ለመጓዝ ቪዛ አለመጠየቅ አልያም በመዳረሻ ቪዛ የማግኘት መብት ማለት ነው።

ተቋሙ የፓስፖርት ደረጃን የሚያወጣው ያለ ቪዛ ለሚደረግ የጉዞ መዳረሻ አንድ ነጥብ በመስጠት ነው።

የፓስፖርት ጥንካሬ የሚወሰነው በምንድን ነው ?

የዓለም ባንክ እንደሚለው የአንድ አገርን የፓስፖርት ጥንካሬ ከሚወስኑ ዋነኛ ጉዳዮች መካከል እነዚህ ይጠቀሳሉ።

- ዜጎች የሚያገኙ የነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን ፤ ከፍተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያላቸው አገራት ከደሃ አገራት በተሻለ ወደ በርካታ አገራት ቪዛ ቀድሞ ማግኘት ሳይጠበቅባቸው መጓዝ ይችላሉ።

- የአንድ የአገር #ሁለንተናዊ_ሰላም ከአገሪቱ የፓስፖርት ጥንካሬ ጋር በቀጥታ ይገናኛል። በአንድ አገር የሽብር ጥቃቶች እና የውስጥ ግጭቶች የበረከቱ ከሆነ እንዲሁም በተደራጁ ቡድኖች የሚፈጸሙ ወንጀሎች ካሉ የዚያች አገር ዜጎች ዓለም አቀፍ ጉዟቸው የተገደበ ይሆናል።

- ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት የሌላቸው እና ከፍተኛ ተፈናቃይ ያለባቸው አገራት ዜጎችም በተመሳሳይ ቪዛ የሚጠየቁባቸው መዳረሻዎች ከፍተኛ እንዲሆኑ አድርጓል።

ሪፖርቱን በዚህ ይመልከቱ ፦ www.henleyglobal.com/passport-index/ranking

Via BBC

@tikvahethiopia