TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ጥንቃቄ ሁሉ በመተግበር በሳምንት አራት ቀናት ወደ #ዱባይ በረራ መጀመሩን አስታውቋል።

በተጨማሪ አየር መንገዱ ከምዕራብ አፍሪካ መዳረሻዎች መካከል የቤኒን ፣ አይቮሪ ኮስት እና ካሜሩን ከተማዎች በረራ መቀጠሉን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ኢንስታግራምን ዘጋች። ሜታ ኩባንያ በኢንስታግራም ላይ በሩስያውያን ላይ የጥቃት ፣ የግጭት ቀስቃሽ ፣ እና የጥላቻ ጥሪዎች እንዲተላለፉ መፍቀዱን ተከትሎ ሀገሪቱ ከዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎት እንዳይሰጥ አድርጋዋለች። ኢስታግራም ከመዘጋቱ 48 ሰዓት በፊት ተጠቃሚዎች የፎቶ እና ቪድዮ ፋይሎቻቸውን ወደሌላ የማህበራዊ ሚዲያ እንዲያዞሩ ጊዜ ተሰጥቷቸው ነበር። 2021 ላይ ኢንስታግራም…
#Telegram

በአሁን ሰዓት ቴሌግራም በሩስያ ቀዳሚው እና ተመራጩ የመልዕክት መለዋወጫ ሆኗል።

በተለይ ሩስያ ኢንስታግራም እና ፌስቡክን ማገዷን ታከትሎ ቴሌግራም በቀዳሚነት ተመራጩ የመልዕክት መለዋወጫ ሊሆን ችሏል።

የዩክሬን ፕሬዜዳንት ዜሌስንኪን ጨምሮ በርካታ የዩክሬን እና የሩስያ ባለስልጣናት ፣ ሚዲያዎች ፣ ፖለቲከኞች ፣ ተቋማት መልዕክት ለመለዋወጥ ቴሌግራምን የሚጠቀሙ ሲሆን በሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት በመረጃ ልውውጥ ትልቁን ስፍራ የያዘ የማህበራዊ ሚዲያ ሆኗል።

ቴሌግራም ከዚህ በፊት ማለትም በ2018 ላይ በሩስያ ባለስልጣናት ለሁለት ዓመታት ታግዶ እንደነበር እና እገዳው 2020 ላይ መነሳቱ ይታወሳል። በወቅቱ እገዳው የተጣለበት የተጠቃሚዎችን መረጃ እንዲሰጥ ተጠይቆ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነበር።

በአሁን ሰዓት እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ ቴሌግራም የዩክሬን ተጠቃሚዎቹን መረጃ ለሩስያ ያቀብላል ተብሎ ስሙ ቢነሳም የኩባንያው መስራች በትውልድ ሩስያዊው እና በኡሁን ሰዓት በዩኤኢ #ዱባይ ነዋሪነቱን ያደረገው ፓቨል ዱሮቭ ኩባንያው የዩክሬን ተጠቃሚዎችን መረጃ አሳልፎ እንዳልሰጠ ፥ ይህንንም እንደማያደርግ በምንም ሁኔታ ለተጠቃሚዎቹ መብት እንደሚቆም ገልጿል።

የቴሌግራም መስራቹ ፤ በእናቱ በኩል ቤተሰቦቹ ከኪየቭ እንደሆኑ ጠቁሞ እስከ አሁን ድረስም በዩክሬን የሚኖሩ ብዙ ዘመዶች እንዳሉት ገልጿል። አሁን ያለው አሳዛኝ ግጭትም " ለእኔም ሆነ ለቴሌግራም ግላዊ ነው " ሲል ነው ሁኔታውን የገለፀው።

የድምፅ እና ቪድዮ ጥሪዎችን፣ የምስጥራዊ የመልዕክት ልውውጦች (ቻት) እንደማያነብ የሚናገርለት ቴሌግራም በምንም ሁኔታ የተጠቃሚዎቹን መረጃ አሳልፎ እንደማይሰጥ የገለፀ ሲሆን ለተጠቃሚዎቹ መብት እንደሚቆም አረጋግጧል።

@tikvahethiopia
#EthiopianCargo 🇪🇹

በትላትናው ዕለት በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፣ #ዱባይ በተካሄደ የ " አረቢያን ካርጎ አዋርድ " በደንበኞች ምርጫ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ " በአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አየርመንገድ " ተብሎ ተመርጧል።

በዚሁ የሽልማት ዘርፍ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ  ኦፕሬት የሚያደርጉት አየር መንገዶች በእጩነት ቀርበው የነበረ ቢሆንም አየር መንገዱ ሁሉንም በመብለጥ ነው በአፍሪካ - ምርጡ የካርጎ አየር መንገድ ተብሎ የተሸለመው።

@tikvahethiopia