TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰው ሰራሽ ዜና አንባቢ‼️

ቻይና በአለም #የመጀመሪያውን ሰው ሰራሽ ዜና አንባቢ ይፋ አደረገች፡፡ ሰው ሰራሽ ዜና አንባቢው ማሽን የሰው መልክ ያለው ሮቦት ነው፡፡

ሮቦቱ በቻይና ብሔራዊ የዜና ተቋም በሆነው ሽንዋ ዜናዎችን ሲያነብ የድምጽ አወጣጡ፣ የፊትና የእጅ እንቅስቃሴ እውነተኛ ሰውን እንደሚመስል ለመመልከት ተችሏል፡፡

‹‹ሶጎዮ›› በሚባል የቻይና የኢንተርኔት መረብ እና በሽንዋ የበለፀገው ሮቦት እረፍት ሳያደርግ በቀን ለ24 ሰዓት መረጃን የማቀበል አቅም አለው ተብሏል፡፡

ሮቦቱ በቻይንኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች መረጃዎችን ለተመልካቾች እንደሚያቀርብ ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ ዘ ጋርዲያን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ከተመረቀ #የመጀመሪያውን አመታዊ የኮካኮላ የሽያጭና ግብይት ስብሰባ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በ450 ተሳታፊዎች በሚያምረው ግዙፍ አዳራሽ ያስተናግዳል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopi
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 24/2011 ዓ.ም.

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከጅቢቲ ወደ የመን በማምራት ላይ ሳሉ በሰጠሙት ሁለት ጀልባዎች ውስጥ ከተጫኑት #ኢትዮጵያውያን ናቸው ከተባሉ ስደተኞች መካከል #የሞቱት ቁጥር ወደ 52 ከፍ ማለቱ ተነገረ።
.
.
የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሰድስት ወራት ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ መያዙን ገልጿል።
.
.
ኢትዮጵያዊው ሌተናል ጀነራል #ጥጋቡ_ይልማ_ወንድማገኝ በሶማልያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ አዛዥ በመሆን ተሹመዋል።
.
.
32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ከጥር 30 2011 ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል #ግብር አሰባሰብ ችግር በፈጠሩ 75 ባለሙያዎች ላይ ሕጋዊ #እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን አስታውቋል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በተለያየ ጊዜ ለልማት መሬት ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ122 ኢንተርፕራይዞች ላይ #እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
.
.
በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ የዞንና የክልል ጥያቄዎችን በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ #ለመመለስ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ተናግረዋል።
.
.
ባለፉት 6 ወራት 7ሺህ 8 መቶ ባለቤት አልባ ውሾችን ማስወገዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
.
.
የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታን #ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ #በተጠናከረ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
.
.
24 የአልሸባብ ቡድን አባላት በአየር ድብደባ #መሞታቸውን የአሜሪካ ጦር ኃይል አስታውቋል።
.
.
በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ የተገነባው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መታሰቢያ ኀውልት የካቲት 3 ቀን 2011 የሚመረቅ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
.
.
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ነጋዴዎች #መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።
.
.
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ #ሊከለስ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው እንደገለጹት አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ፖሊሲ በማስፈለጉ ነው ክለሳ የሚደረግበት፡፡
.
.
16ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ "ቅድሚያ ለሴቶች" ከመጋቢት 1 ጀምሮ ይካሄዳል።
.
.

ጉዞ ሉሲ የአንድነት እና የፍቅር ፕሮጀክት የካቲት 14 ይጀምራል፡፡ ጉዞ ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ ነው፡፡
.
.
የሀገሪቱ መደበኛ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናግረዋል።
.
.
ከጥረት ኮርፖሬት፣ ላፓልማ እና ባህርዳር ሞተርስ አክሲዮን ማህበር #የሙስና_ወንጀል ጋር በተያያዘ ከጠረጠሩት አምስት ግለሰቦች መካከል አራቱ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
.
.
በቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ #ግጭት ሰባት ሰዎች #መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #የሽዋስ_አለሙ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
.
.
የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ከተመረቀ #የመጀመሪያውን አመታዊ የኮካኮላ የሽያጭና ግብይት ስብሰባ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በ450 ተሳታፊዎች በሚያምረው ግዙፍ አዳራሽ ያስተናግዳል።
.
.
የቀድሞው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አምባሳደር #ዳዊት_ዮሐንስ የቀብር ስነ ስርዓት የፊታችን እሁድ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክረስቲያን ይፈፀማል፡፡
.
.
የጎፋ ዞን ዛሬ #በይፋ ተመስርቷል። የዞኑ ይፋዊ የምስረታ በዓል በሳውላ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የዞኑ ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ተከብሯል፡፡
.
.
ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው የመኪና መንገድ #ባቢሌ ከተማ ላይ #በመዘጋቱ መቸገራቸውን አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ አሽከርካሪዎች ተናግረዋል።
.
.
ምንጭ፦ ኢዜአ፣etv፣fbc፣ ዋዜማ ራድዮ፣ BBC አማርኛ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የጀርመን ድምፅ ራድዮ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት...

(ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ)
#STOP_HATE_SPEECH

በሀገር አቀፍ ደረጃ TIKVAH-ETH "የፀረ ጥላቻ ንግግር" ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛል። በተለይም በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ያሉ የጥላቻ ንግግሮች ሀገራችንን #ወደማትወጣው መከራ ውስጥ የሚከታት በመሆኑ ጊዜው ሳይረፍድ ይህን እኩይ ተግባር በጋራ መዋጋት ያስፈልጋል።

በቅድሚያ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገራችን ወጣቶች በሚገኙባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ትኩረት በማድረግ የጥላቻ ንግግር ሊያመጣ የሚችለውን ችግር የማስገንዘብ ስራ እየሰራን እንገኛልን።

ሀሳቡን ካቀረብንላቸው የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ሀሳቡን በመደገፍ እንዲሁም ዘመቻውን ለማገዝ ፍቃደኝነቱን ያሳየን #የመጀመሪያውን ተቋም ነው። በዚህ አጋጣሚ በዶክተር #ታከለ ለሚመራው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እንዲሁም #ለተማሪዎች_ህብረቱ ያለንን ላቅ ያለ ምስጋናና ክብር እንገልፃለን!!
.
.
.
ውድ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኑ ...3 ተከታታይ ምሽቶችን ከTIKVAH-ETH ጋር አሳልፉ! ስለጥላቻ ንግግሮች እና ከጊዜ ወደጊዜ እየከፋ ስለመጣው አግባብነት የሌለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እንነጋገር! የሀገራችሁ ጉዳይ ካሳሰባችሁ ሀሳባችሁን ስጡ...የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ጠቁሙ!

ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ በተከታታይ!

🔹ቦታ - ዋናው ግቢ(በተማሪዎች መግቢያና መውጫ በር አካባቢ)

⌚️ሰዓት - ከምሽቱ 12:30 ጀምሮ

እንግዶች ይኖራሉ!!

#በፍቅር ኢትዮጵያን እንገንባ!!
ከጥላቻ ንግግሮች #እንቆጠብ!!

(የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት)

በቀጣይ፦

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
አምቦ ዩኒቨርሲቲ
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
መቀለ ዩኒቨርሲቲ
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

#ለቀጣዩ_ትውልድ ከጥላቻ የራቀችን ሀገር እናወርሳለን! ሀሳቡን ለመደገፍ የምትፈልጉ፦
0919 74 36 30 @tsegabwolde

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE😷

የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ ፦

🇮🇹 በጣልያን በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ሲሆን በትላንትናው ዕለት 98,030 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 148 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

🇫🇷 ፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 208,000 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጋለች። በሀገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው።

🇧🇦 ቦሲኒያ #የመጀመሪያውን የኦሚክሮን ልውጥ ቫይረስ ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች። 10 ሰዎች በኦሚክሮን መያዛቸው ሲረጋገጥ ምናልባትም ብዙ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል።

🏴󠁧󠁢󠁳󠁣󠁴󠁿 የስኮትላንድ ጠ/ሚ ስኮት ሞሪሰን አስቸኳይ ብሄራዊ የካቢኔ ስብሰባ ጠርተዋል። በሀገሪቱ የኮቪድ-19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እተባባሰ ነው ተብሏል።

🇵🇱 ፖላንድ በ4ኛው የኮሮና ቫይረስ ማዕበል እየተፈተነች ሲሆን በ1 ቀን 794 ዜጎቿ እንደሞቱባት የሀገሪቱ ምክትል የጤና ሚኒስትር አሳውቀዋል።

🇪🇸 በስፔን በአንድ ቀን ብቻ 100,760 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ በቀን ከ100,000 በላይ ኬዝ ሲመዘገብ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነው። ለወረርሽኙ በዚህ ደረጃ መጨመር የኦሚክሮን ዝርያ መስፋፋት አንዱ ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።

🇪🇹 በኢትዮጵያ ሀገራችን ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ 11,749 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

🇺🇸 CDC በአሜሪካ በሚቀጥሉት 4 ሳምንታት ከ44 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ሊሞቱ እንደሚችሉ ተንብይዋል።

🌍 በዓለም አቀፍ ደረጃ እኤአ ከታህሳስ 22 እስከ ታህሳስ 28 ድረስ ባሉት ቀናት በየዕለቱ በአማካኝ 935,863 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የነበረ ሲሆን በአጠቃላይ 6,550,000 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

@tikvahethiopia