TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሪሴል ፒክፒክ ኃ/የተ/የግ/ማህበር👇

ከመስከረም 2010 ጀምሮ ከአንድ ሺህ በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ጋር የስራ ስምምነት ውል በማድረግ ከባንክ ጋር የ70% ብድር በማመቻቸት በደንበኖቹ ስም ከ1000 ሺህ በላይ ታክሲዎችን በመጠቀም በአዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ የሚገኝ ነው።

​እንደሚታወቀው መኪኖችን #ገጣጥሞ በሚያቀርበው ኩባንያ መኪኖችን ለማቅረብ የሚያስችሉ ግብአቶችን ካዘዘ እና የ ውጭ ምንዛሪ ወረፋ በ 6 የተለያዩ ባንኮች ከያዘ ከ 1 ዓመት ከ7 ወር ባላይ የሆነው ሲሆን ኩባንያችን ወደ ስራ የገባበት ጥር 2010 ሀገራችን በለውጥ ሂደት ውስጥ የነበረችበትና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ያጋጠመበት ወቅት ነበር። ነገር ግን ይህንን እጥረት ከአጋር ኩባንያዎችና ባንካችን ጋር በመሆን እስካሁን ድረስ 300 መኪኖችን ያስገባ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 198 መኪኖች ለባለ ንብረት ሊብሬ በማውጣት ስራ እንዲጀምሩ የተደረገበት ወቅት ላይ እንገኛለን። ቀሪዎቹንም 99 መኪኖች ለደንበኞች ለማስተላለፍ የባንክ ብድር ሂደት ቀጥሏል። ለቀሪዎቹም የተለያዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር #የማሳለጥ እንቅስቃሴዎችን ጀምረናል።

ይሁን በማህበራዊ ትስስር ገፅ #የሃሰት_መረጃ እና #ቅስቀሳ በማድረግ ኢፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለመበልፀግ በደቦ፣ በግርግር እና በሚዲያ በማስፈራራት በራስ ፍላጎት ቢዝነስን እንዳሻቸው በማድረግ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች እና ጥቂት ነገሩ ያልገባቸውን በማስተባበር ከውል እና ህግ ውጭ ፤ በአውቅልሃለሁ በሚል ሰበብ የስራ ፈጣሪዎችን ላብ በመቀማት ኩባንያዎችን በማተራመስ ማትረፍ ስራቸው ያደረጉ ግለሰቦች በመኖራቸው ምክንያት የሚደረግ እንቅስቃሴ መሆኑን ለመገንዘብ ችለናል።

#ህግን እና #ውልን መሰረት አድርጎ ትክክለኛ አሠራርን ተከትሎ የሚሠራ ድርጅት በመሆናችን ዛሬም ሪሴል ፒክ ፒክ ለደንበኞቹ እና ለቤተሰቦቹ በቀናነት ማገልገሉን ይቀጥላል፤ “ከስራ ሁሉ ህግን ማክበር ቀዳሚ ነው” ህግን የማክበርም የማስከበርም ድርሻችን እንወጣለን። ስለዚህም የፒክ ፒክ ቤተሰቦች በሙሉ እንደተለመደው ማንኛውንም መረጃ ከቢሮአችን ማግኘት እንደምትችሉ በትህትና ለመግለፅ እንወዳለን።

/ሪሴል ፒክፒክ ኃ/የተ/የግ/ማህበር/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀገር_አቀፍ_ፈተና2011 ብሄራዊ ፈተና ወሳጅ ተማሪዎች በፈተና ወቅት ህብረተሰቡ #የሃሰት መረጃዎችን ባለመቀበልና ባለማሰራጨት እንዲተባበራቸው ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፌስቡክ

ፌስቡክ ከሳውዲ አረቢያ ጋር የተገናኙ #የሃሰት ፕሮፓጋንዳ የሚሰራጭባቸው መለያዎችን የሚጠቀሙ አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዳሉ ደርሸበታለሁ በሚል መለያዎችን አገደ፡፡ ዘመቻው መካከለኛው መስራቅን እና ሰሜን አፍሪካ ላይ ያነጣጠረ እንደሁነና የመልዕክቱ ይዘት በአብዛኛውም በአረበኛ ቋንቋ የሚተላለፍ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል ፌስቡክ። እስካሁን ድረስም ከ 350 በላይ የሃሰት አካውንቶችን ዘግቻለሁ ብሏል። ሳውዲ ጉዳዩን አስመልክቶ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት አስተያየት እንዳልሰጠች ተገልጿል።

Via ቢቢሲ/#ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia