TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ItsMyDam🇪🇹 ሀገራችን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ከ2022 ጀምሮ ከታላቁ የኅዳሴ ግድብ በዓመት 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር የኢትዮጵያ የኢኖቬስን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ሚኒስትር ደኤታ ሁሪያ አሊ ማህዲ አስታወቁ። ኢትዮጵያ በዚሁ ከመጀመሪያ ዙር እንደምታመነጭ ከሚጠበቀው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አጠቃላይ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት…
#GERD🇪🇹

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዚህ ሳምንት በሰጡት መግለጫ ከተናገሩት ፦

(ከሪፖርተር)

" ... የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኤሌክተሪክ ማመንጨት የሚጀምርበትን ቀን ይህ ነው ብሎ መነገር ባይቻልም፣ በጣም በቅርብ ጊዜ ይጀምራል።

የግድቡ ጉዳይ ሊለወጥ የማይችልና ያለቀ ነገር በመሆኑ፣ የታችኛው ተፋሰስ አገሮች ከዚህ ካለቀ ጉዳይ ጋር አብረው መቆም አለባቸው።

ከዚህ በኋላ ግድቡ ሲያመነጭ ለግብፆችም ሆነ ለሱዳኖች ጠቃሚ ከመሆኑም በላይ ፣ በሚመነጨው ኃይል ሌሎችም አገሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እነዚህ አገሮች ቢሠሩ መልካም ነው። ነገር ግን የሦስትዮሽ ድርድሩ ይቁም ማለት አይደለም።

ሱዳን እና ግብፅ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ከጀመራቸሁ ችግር ይፈጠራል፣ ሰማዩ ይገለባበጣል የሚሉት ነገር አዲስ አይደለም፡፡

ቀድሞውንም ሙሌት ከጀመራችሁ አደጋ ይፈጠራል፣ ጉድ ይፈላል ሲሉ ነበር ይህ ፉከራ የተለመደ ቢሆንም አሁን ግን ያረጀና ጊዜው ያለፈበት ሆኗል።

በህዳሴ ግድቡ ውኃው ተርባይኑን አንቀሳቅሶ አልፎ ስለሚሄድ መጠኑ ስለማይቀንስ፣ ሱዳኖች የግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመር ሊያስደስታቸው እና ሊያከብሩት ይገባል። "

@tikvahethiopia
#GERD #ItsMyDam 🇪🇹

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለአል-አረቢያ ሚዲያ የተናገሩት ፦

" ... ሀገራችን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በፍጥነት እንድታጠናቅቅ ግብፅ ማበረታታት አለባት።

ግድቡ ግብፅን በድርቅ ወቅት እንኳ የውሃ ቋት ሆኖ የሚያገለግል እንደመሆኑ ፕሮጀክቱን ልትደግፈው ይገባል።

ሱዳን በአነስተኛ ግድቦቿ ላይ ይደርስብኛል ብላ የምታነሳውን የደህንነት ስጋት በሚመለከት መደበኛ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ ኢትዮጵያ ዝግጁ እንደሆነች አቋሟን አስርድታለች።

ሀገሪቱ ግን አሁን ላይ የራሷን ብሄራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ይልቅ የሶስተኛ ወገን ጉዳይ አስፈፃሚ አየሆነች መጥታለች።

ኢትዮጵያ አንድ ወገን ብቻ ከአባይ ሀብት ተጠቃሚ ሲሆን ዘላለም አለሟን መጠበቅ አትችልም። በመሆኑም ሱዳን እና ግብፅ አሁን ላይ ከያዙት ግትር አቋም መላቀቅ አለባቸው።

ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ በሚመለከት ብዙ አዎንታዊ የሆኑ እድሎችን አቅርባ ነበር። ግብፅና ሱዳን ባለመቀበላቸው ምክንያት ግን ሳይሳኩ ቀርተዋል።

የህዳሴ ግድብ ከጭቅጭቅ ይልቅ የቀጠናዊ ህብረትና አንድነት ማሳያ ነው። ኢትዮጵያ በታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ ምንም አይነት የጎላ ጉዳት ሳታደረስ የራሷን ሀብት መጠቀም ትችላለች "

(ኤፍቢሲ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ? ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ "የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት ጀመረ" የሚሉ በርካታ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ ይገኛሉ። መንግስት በዚህ ጉዳይ በይፋ ያሳወቀው ነገር ባይኖርም ከዚህ ቀደም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ለማመንጨት መቃረቡ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጩ ለነበሩት የግድቡ መረጃዎች ምንጫቸውን ለማወቅ ብናስስም ልንደርስበት…
#GERD

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ነገ እሁድ የካቲት 13 ቀን 2014 ዓ.ም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር አጀንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ሁለት ስማቸው ያልተገለፀ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ በዛሬው ዕለት ዘግቧል።

ዛሬ አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣን [ስማቸው ያልተገለፀ] " ነገ የግድቡ የመጀመሪያው የሃይል ማመንጫ ይሆናል" ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ሌላ ሁለተኛ ከፍተኛ ባለስልጣን መረጃውን ማረጋገጣቸውን ገልጿል።

ሁለቱም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት ጉዳዩ በይፋ ስላልተገለፀ ነው ተብሏል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በቅርቡ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር የገለፀ ሲሆን መቼ ? ለሚለው ግን መረጃ አልሰጠም ነበር።

ይኸው ጉዳይ ባለፉት ቀናት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር ነበር፤ ነገር ግን በመንግስት በኩል ይፋዊ መረጃ አልተሰጠም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አንደኛው ሁኒት [ ዩኒት 10 ] ኃይል ማመንጨት መጀመሩን የግድቡ ሰራተኞች ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል። @tikvahethiopia
#GERD

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ክፍሌ ሆሮ ፦

"... ማመንጨት ተጀመረ እንጂ ፕሮጀክቱ ተጠናቀቀ ማለት አይደለም።

ፕሮጀክቱን ለመጠናቀቅ አሁን ብለው ሁኔታ ከሁለት ዓመት ተኩል እስከ ሶስት ዓመት ሊፈጅብን ይችላል።

ስለዚህ ህዝቡ ከመጀመሪያውም ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያውያን ፕሮጀክት ነው። ፋይናንስ ሚደረገው በመንግስትና በኢትዮጵያ ነው ስለዚህ ይሄን ተገንዝበን ፕሮጀክቱን እስከመጨረሻው ፋይናንስ ማድረግ አለብን።

የኢትዮጵያን እውነታ አሁን ተርባይኑን መቶ ነው ውሃ እየፈሰሰ ያለው ስለዚህ ኢትዮጵያ ከዚህ ውሃ ምንም የምትቀንሰው ነገር ስለሌለ ዓለምም ይህን እንዲረዳ እያንዳንዳችን ተረባርበን ለፕሮጀክቱ ዲፕሎማት ሆነን መንቀሳቀስ አለብን። "

@tikvahethiopia
#GERD

" ግድቡን እኛ ሳንሆን እነሱ ናቸው የሚጠብቁት " - የቀድሞ የሀገራችን ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ

@tikvahethiopia
#GERD

" ... በወንዞቻችን ለመጠቀም እና ድህነትን ለማስወገድ የምናደርገው ጥረት እራሳችንን እና ጎረቤቶቻችንን ጭምር ለመጥቀም እንጂ ማንንም ለመጉዳት እንዳልሆነ ለዓባይ ልጆች ሁሉ ለማረጋገጥ እፈልጋለሁ " - የቀድሞ የሀገራችን ጠ/ሚ ሀኃይለማርያም ደሳለኝ

@tikvahethiopia
#GERD

" ... የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን። የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው " - የአሁኑ የሀገራችን ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ

@tikvahethiopia
#GERD🇪🇹

" የታላቁ ህዳሴ ግድብ 3ኛውን የውሃ ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ ነው ፤ ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ በትኩረት እየተሰራ ነው " - ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ

የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ ፥ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው የምትገኘው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲከናወን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ሌ/ጀኔራል ደስታ " ሠራዊቱ የተሠጠውን ተልኮ ሌት ተቀን በቁርጠኝነት መፈፀም በመቻሉ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውሉ ግብአቶች በሰላም ተጓጉዘው እንዲደርሱ እና ሰራተኞችም ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ማድረግ ተችሏል " ብለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ #3ኛውን_የውሃ_ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት ሌ/ጀኔራሉ " የግድቡ ግንባታ ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ የተቀናጀ የፀጥታ ሃይሉ በትኩረት እየሰራ ነው " ብለዋል።

አክለውም " የተቀናጀ የፀጥታ ሃይሉ ዕድገታችንን ለማደናቀፍ #ከሱዳን ሰርገው የሚገቡ ኃይሎችን እየተከታተለ ሴራቸውን እያከሽፈው ይገኛል ፤ በቀጣይም ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ሲቪል አመራሮች ጋር ተቀናጅቶ ግዳጁን በአስተማማኝ ለመወጣት ዝግጁነቱ የላቀ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

#FDRE_Defense_Force🇪🇹

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#GERD

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 3ኛ ዙር ሙሌት ከመጪው ሐምሌ ወር አንስቶ መከናወን እንደሚጀምር አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልወደዱ የግድቡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊን ዋቢ አድርጎ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ ወደ ግድቡ የሚፈሰው የውኃ መጠን ከሰኔ አጋማሽ ጀምሮ ከፍ እያለ ከሄደ በኋላ ወደ ግድቡ የሚገባውን ውኃ በመያዝ በሐምሌ ወር ሙሌቱ ይጀመራል ብለዋል ኃላፊው።

በዚህ ዓመት ወደ ግድቡ እንዲገባ የሚጠበቀውን የውኃ መጠን ለመያዝ የግድቡን ቁመት የመጨመር ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ገልፀዋል። የውኃ ሙሌቱ ሲጀመር የግድቡ ቁመት በሚፈለገው መጠን እንደሚደርስ አስረድተዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት በሰኔ ወር መጨረሻ ሲጀመር በነሐሴ ወር አጋማሽ እንደሚጠናቀቅ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ በዓመቱ በነበረው ከፍተኛ መጠን ያለው የዝናብ ፍሰት የተነሳ መጠናቀቁ የተበሰረው ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ነበር።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia