TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Gambella የጋምቤላ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ገለፁ። ፕሬዝዳንቱ ይህን የገለፁት የከተማውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። " በክልሉ የሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ባካሄዱት ቅንጅታዊ ማጥቃት ከተማውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል " ያሉት አቶ ኡሞድ " በጥቃቱ በጠላት በኩል ከፍተኛ…
#ማስታወሻ

የጋምቤላ ነዋሪዎች #ከምሽት_2_ሰዓት_በኃላ ቤት በመቀመጥ / ከቤት ባለመውጣት እና አካባቢን በንቃት በመጠበቅ ለሰላም ተባባሪ እንዲሆኑ ክልሉ ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፦

የቲክቫህ አባላት በጋምቤላ ትላንት የነበረው ሁኔታ እየተረጋጋ መምጣቱን የገለፁ ሲሆን አንዳች ስጋት ያደረባቸው ሁኔታ መኖሩን አመልክተዋል።

ይኸውም የኦነግ ሸኔ / OLA ታጣቂዎች በከተማ መታየታቸው እና ተኩስ መለዋወጣቸውን ተከትሎ አንዳንድ ወጣቶች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ሆነው በተለይ ንፁሃን ላይ የማዋከብ እና አንዳንድ ቦታም የማጠቃት ምልክት ታይቷል።

ከተማው ሰላሙ እየተመለሰ ነው ያሉን የቤተሰባችን አባላት አንዳንድ ወጣቶች በፖሊስ ታግዘው የዛው የክልሉ ተወላጅ ያልሆነን ሰው መደብደብ፣ ማዋከብ፣ ድርጊት እየፈፀሙ ነው ብለዋል።

ይህን መሰል ኢፍትሃዊ ድርጊት ቶሎ መቆም አለበት ፤ TPLFም ሁሉንም ኦሮሞ እንደ OLF ይቆጥር ነበር ይህ ግን እውነት አልነበረም። አሁን እያየን ያለነው ምልክት ይኸው ነው ይህ ሀገሪቱ እንዳትረጋጋ ያደርጋል ንፁሃንን ከአማፅያን ጋር አንደባልቆ ማየት ተገቢ አይደለም ብለዋል።

በአሁን ሰዓት መድሃኒዓለም ፣ ጎንደሬ፣ ወሎ ሰፈር ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ፤ በአግባቡ ህግ ሊከበር እና ንፁሃን እንዳይሳቀቁ ማደረግ ተገቢ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የመውጫ ፈተና ውጤት እየታየ ይገኛል።

በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተመራቂ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከእሁድ ረፋድ ጀምሮ እየተመለከቱ ይገኛሉ።

ውጤቱ መታየት ከጀመረበት ሰዓት አንስቶ ለረጅም ሰዓታት በመንግስት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ብቻ ውጤታቸውን ማየት የቻሉ ሲሆን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ደግሞ #ከምሽት አንስቶ ውጤታቸውን ማየት ጀምረዋል።

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ " ውጤት መመልከቻው ድረገፅ ላይ ገብተው username ሲያስገቡ የሚያገኙት ምላሽ የተቋማቸው " የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ አልተደረገም " የሚል እንዲሁም የአንዳንዶቹ " ያስገቡት ስም የማይሰራ " መሆኑን የሚገልፅ ነው።

ውጤታቸውን የተመለከቱ በርካታ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ደግሞ 50 እና ከዚያ በላይ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ቢሆንም " fail / ወድቀዋል " የሚል ምላሽ እያገኙ መሆኑን በመግላፅ ትምህርት ሚኒስቴር በሲስተሙ ላይ ያለውን ችግር #እንዲያስተካክል ጠይቀዋል።

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፤ የመውጫ ፈተና የተቀመጡት 72,203 ተማሪዎች ሲሆኑ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተው ያለፉት 12,422 ተማሪዎች ወይም 17.2 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ፤ በመውጫ ፈተና አመርቂ ውጤት ካልተመዘገበባቸው / እጅግ በርካታ ተማሪዎች ከወደቁባቸው የትምህርት ክፍሎች አንዱ የ " Accounting and Finance " ሲሆን በፈተናው ላይ  ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች የፈተናው ምዘና ድጋሚ እንዲፈተሽ ጠይቀዋል።

በተመሳሳይ የ " Information Technology " ተማሪዎችም መሰል አቤቱታ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ የተሰጠው ፈተናው ከነበረው ዝግጅት ጋር የሚራራቅ እንዲሁም ደግሞ ከ ተሰጣቸው ' ብሉለሪንት ' ጋር የማይቀራረብ በመሆኑ ሚኒስቴሩ እንዲያይላቸው አቤቱታ አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደም የ ' መካኒካል ምህንድስና ' ተመራቂ ተማሪዎች ከፈተናው ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ማቅረባቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ወይም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ተማሪዎችን #ቅሬታ የሚያስተናግዱበት መንገድ ካለ ጠይቆ የሚያሳውቅ ይሆናል።

#ማስታወሻ ፦ የመውጫ ፈተና ውጤት የሚታየው በ result.ethernet.edu.et ላይ Username በማስገባት ነው።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በወርሃ ጥቅምት 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት በትግራይ ክልል ደረጃ የሃዘን ቀን ይታወጃል። በትግራይ ደረጃ የሚታወጀው የሃዘን ቀን የክልሉ የአርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል። ምክር ቤቱ መስከረም 20 /2016 ዓ.ም ባካሄደው የመጀመሪያ ስብሰባው በአፅንኦት እንዳለውና ህግ ሆኖ እንዲሰራ ባፀደቀው መመሪያ መሰረት አዋጁ ከፀደቀበት ቀንና ሰአት ጀምሮ ለመርዶ ተብሎ…
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ ከምሽት አንስቶ ለሶስት ቀናት በክልል ደረጃ የሀዘን ቀን ሆኖ ይውላል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደር በምክትል ፕሬዜዳንት ማዕረግ የፀጥታ እና ደህንነት ኃላፊ ጀነራል ታደሰ ወረደ ከጥቅምት 2 ጀምሮ የሀዘን ቀን እንደሚታወጅ ይፋ አድርገዋል።

" 3 የብሄራዊ ሀዘን ቀን ይኖሩናል " ያሉት ጄነራል ታደሰ ይህ ሁሉንም ትግራዋይ የሚመለከት ሀዘን ነው ብለዋል።

" ሁሉም ትግራዋይ በትግራይ ውስጥ ሆነ በመላው ኢትዮጵያ ፤ እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኘው ለሰማዕታት ክብር የሚሰጥበት የሃዘን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ጄነራል ታደሰ የሃዘን ቀኑ ጥቅምት 2 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ #ከምሽት ጀምሮ ይከናወናል ብለዋል።

ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የሃዘን ቀን የክልሉ ባንዴራ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ፣ የመንግስትና የግል ሚድያዎች ሰማዕታትን የተመለከቱ መልእክቶች እንደማያስተላልፉ ተነግሯል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተደር ይህን የሀዘን ሂደት የሚያውክ ማንኛውም ነገር የተከለከለና በህግ የሚያስጠይቅ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia