TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ከጥቂት ወራት በሗላ የአፋር፣ የቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ የሶማሌ፣ የኦሮሞ፣ የአማራ...ፓርቲ እያልን አንሄድም። እንደ ኢህአዴግ ከጫፍ ጫፍ ያሉ ሁሉም #ኢትዮጵያዊያን በነፃነት የሚሳተፉበት አንድ ሀገራዊ ፓርቲ #እንመሰርታለን!!" ጠ/ሚ ዶ/ር #አብይ_አህመድ - ከተለያዩ ክልል ተወካዬች ጋር ሲወያዩ የተናገሩት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በክቡር የኢፌድሪ ጠ/ሚንስተር #አብይ_አህመድ(ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሊተገበር የታቀደው የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክትን ለመደገፍ የቻይና መንግስት #ፍላጎት እንዳለው ገለፀ፡፡ ለዚህም የቻይና መንግስት የባለሞያ ልዑካን ቡድን የከተማ አስተዳደሩ የጀመረውን የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክትን በገንዘብ እና የቴክኒክ ዕገዛ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ከኢ/ር #ታከለ_ኡማ ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል፡፡ በዚህም የቴክኒክ ቡድኑ የቻይና መንግስት ፕሮጀክቱን የሚደግፍበት ሁኔታ ላይ ጥናት የሚያደርግ ይሆናል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ገበታ ለሸገር ከዶክተር አብይ ጋር...!

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ለአዲስ አበባ ወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ምሽት አዘጋጁ።

ለእራት ምሽት ዲፕሎማቶች፣ የኩባንያ ስራ አስኪያጆች፣ የአለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች እና ሎሎች አካላት እንዲሳተፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።

የእራት ምሽቱ ለሸገር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጋር በሚል መሪ ቃል መዘጋጀቱ ነው የተነገረው።

ለተሳታፊዎቹ ባደረጉት ጥሪም አዲስ አበባን #ንፁህና #አረንጓዴ ለማድረግ ተሳትፏችሁ የተያዘውን ውጥን ለማሳካት ያስችላል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፋችሁ ይህን ታላቅ አላማ #ስኬታማ በማድረግ የመዲናዋን ነዋሪዎች አኗኗር ለመቀየር ወሳኝ ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

በአዲስ አበባ ወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ላይ የምታደርጉት ተሳትፎ ለቀጣይ ትውልድ ውብ ከተማን ለማስተላፍ በዋጋ የማይተመን ነው በማለት ገልፀዋል። በዚህ የእራት ምሽት አንድ እራትን 5 ሚሊየን ብር #ለመሸጥ ዋጋ ተቆርጦለታል።

የአዲስ አበባን ዋና ዋና ወንዞች ተፋሰስ #ለማልማት የሚያስችል ፕሮጀክት የ29 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

አዲስ አበባን ለሁለት ከፍለው የሚፈሱ ወንዞች ላይ ያተኮረው ፕሮጀክቱ ከሰሜን አዲስ አበባ እንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንም ታውቋል፡፡ ፕሮጀክቱ በሶስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት እና ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ እና ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እየጎበኙ ነው፡፡

Via ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጌዴኦ ዞን

ክቡር ጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ እባኮት ወደጎዲቲ አምርተው ህዝቡ ያለበትን ሁኔታ ቢጎበኙ መልካም ነው። እጅግ በጣም የተጎዱ ወገኖች በብዛት የሚገኙበት ቦታ እንደሆነ አካባቢው በተደጋጋሚ የጎበኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

በነገራችን ላይ ...

ክብርት የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል የጌድኦ ተፈናቃዮችን በጎበኙበት ወቅት በርካቶች የተጎዱበትን ቦታ ሳይጎበኙ ነው የተመለሱት፤ ይህን ያጫወተኝ በጌዴኦ ተፈናቃዮች ዙሪያ የሚሰራ የህክምና ባለሞያ ነው።

የትኛው አካል ነው ይህ እያደረገ ያለው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ ደብዳቤ ጻፈ በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሠራጨው ደብዳቤ #የሐሰት መሆኑን ጽህፈት ቤቱ ገለፀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መረጃው “በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሠራጨው ደብዳቤ የሐሰት መሆኑን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ማሳወቅ እፈልጋለሁ” ብሏል።

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ እንዲህ ያለ ደብዳቤ እንዳልጻፉ ማሳወቅ እንወዳለን” ብሏል ጽህፈት ቤቱ።

በዚህ አጋጣሚ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዲህ የመሰሉ የሐሰት ዜናዎችን እያጣሩና #በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ ሲልም ጥሪውን አስተላልፏል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኳታር ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከሀገሪቱ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጋር በዶሃ ተወያይተዋል።

Via #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከአዲስ አበባ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ሀሳቦች አዲስ አበባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ባህር ዳር፣ መቐለ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ነቀምት ሂዶ እንደሚሰራውና የኔ ናቸው እንደሚለው ሁሉ አዲስ አበባም ተመሳሳይ ነች፤ #የሁሉም ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ነች ብለዋል። #ODP

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቱ🔝

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ ከኦሮሚያ ክልል ዋና አስተዳዳሪ አቶ #ለማ_መገርሳ ጋር በመሆን ከኢሉባቡር ዞን ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቱ🔝

በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ እና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት አቶ #ለማ_መገርሳ የተመራውና መቱ ከተማን በመጎብኘት ላይ የሚገኘው ልኡክ በከተማው ወደ 66 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ በ3ሺህ 2 መቶ ሔክታር መሬት ላይ ለሚገነባው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ማዕከል መቱ ቅርንጫፍ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል። ልዑኩ በማረሚያ ቤት የተገነባውን የመዝናኛ ማዕከልን በመጎብኘት የመቱ ዩንቨርስቲ መንገድ ፕሮጀክት የመረቀ ሲሆን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋርም ተወያይቷል።

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቱ...

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከመቱ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ከሰዓታት በፊት ተወያይተዋል። #PMOEthiopia

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ዮናስ ከስልጣናቸው ተነሱ...

(ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት @eliasmeseret)

ላለፉት ስምንት አመታት የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል የነበሩት አቶ ዮናስ ደስታ በጠ/ሚር #አብይ_አህመድ ትእዛዝ ከስልጣናቸው ተነስተዋል። አቶ ዮናስ ዛሬ ማለዳ ለአለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በላኩት የፅሁፍ መልዕክት "ወደሚቀጥለው የህይወቴ ምእራፍ ስሸጋገር የተደበላለቀ ስሜት ቢኖረኝም የጠ/ሚር አብይን እርምጃ በፀጋ ተቀብያለሁ" ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ለአራት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ።

በዚህ መሰረት፦

ዶክተር አለሙ ስሜ - የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

አቶ ጃንጥራር አባይ - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር

ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን - በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ

አቶ ገዛኸኝ አባተ - የኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሃምሊን ፊስቱላ ማዕከል መሥራች ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን ሐውልት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በተገኙበት ተመረቀ። ሐውልታቸው የቆመው በአዲስ አበባ ጦር ኃይሎች በሚገኘው የሃምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትሩም ሆስፒታሉን ጎብኝተዋል።

"ዶ/ር ሃሚሊን ለምን እንደተፈጠሩ ያወቁ እድለኛ እናት ናቸው” ጠ/ሚ ዶ/ር #አብይ_አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ተፈናቃዮች እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ" - የሰላም ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ። በሀገሪቱ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ አንድ ሚሊዮን ገደማ ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውንም ገልጿል።

በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን በተመለከተ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ተግባር “በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ እና ክብራቸውን በጠበቀ” መልኩ የተከናወነ ነው ብለዋል። “ተፈናቃዮች አለፍላጎታቸው እየተመለሱ ነው” በሚል የሚቀርቡ ወቀሳዎችም “ሀሰት” ሲሉ ሚኒስትሯ አስተባብለዋል።

ወ/ሮ ሙፈሪሃት በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ሁለት ሚሊዮን 332 ሺህ ገደማ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውሰዋል። ከእነዚህ መካከል ግማሽ ያህሉ የተፈናቀሉት ከመጋቢት 2010 ዓ ም በፊት መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሯ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑት በክልላቸው ውስጥ የተፈናቀሉ መሆኑንም ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ስልጣን ከያዙ ከሚያዝያ 2010 ዓ. ም. ወዲህ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር 1.1 ሚሊዮን ነው ተብሏል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ር ዶ/ር #አብይ_አህመድ የመንግስትን የ2011የሥራ አፈጻጸም ሪፓርት ሰኞ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 8ኛ ልዩ ስብሰባውን ሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2011ዓ.ም ጠዋት ያካሂዳል።

Via #EPA
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢንተርኔት #መዘጋቱ ያስፈለገው የሰዎችን #ህይወት እና ንብረት ከጥቃት ለማትረፍ ነው። ኢንተርኔት ውሀ ወይም አየር አይደለም። ለመዝጋት ምክንያት የሆኑንን ምክንያቶች ካልፈታን ለሳምንት ሳይሆን እስከ ወዲያኛው #ሊዘጋ ይችላል!" ጠ/ሚ ዶ/ር #አብይ_አህመድ

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia