TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሱማሌ ክልል‼️

በቱሊ ጉሌድ ወረዳ መስተዳደር በጌሪና በጃርሶ ጎሳዎች መካከል የተነሳ #ግጭት ለሰው ህይወት ህልፈትና ለአካል ጉዳት መንስኤ እየሆነ ይገኛል፡፡

በሶማሊ ክልል መስተዳድር በፋፈን ዞን የቱሊ ጉሌድ ወረዳ ውስጥ በሚኖሩት የጌሪና የጃርሶ ጎሳዎች መካከል በትላንትናው እለት ዳግም ባገረሸ ግጭት ለሰው ህይወት ህልፈትና በርካቶችን ለአካል ጉዳት ዳርጓል፡፡

በዚሁ ግጭት ሳቢያ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ቁስለኞች በሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ጅግጅጋ ከተማ የካራመራ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ለመስማት ተችሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቱሉ ጉሌድ ወረዳ ውስጥ በሚኖሩት የጌሪና የጃርሶ ጎሳዎች መካከል ለብዙ ጊዜ እልባት ሳያገኙ የቆዩ #አለመግባባቶች የነበሩ ሲሆን እነዚሁ አለመግባባቶች #ዘላቂ የሆነ #መፍትሄ ባለማግኘታቸው በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ዳግም ግጭት እንዲያገረሽና ለሰው ህይወት ህልፈትና ለአካል ጉዳት የዳረገ መንስኤ ሊሆን ችሏል፡፡

የሶማሊ ክልል አስተዳደር በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ላሉት አለመግባባቶች ዘላቂ የሆነ መፍትሄ በመስጠት ይኖርበታል።

©rajo
@tsegabwolde @tikvahethiopia