TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሁኔታው አሁንም አሳሳቢ ነው...

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ያለው #የፀጥታ ሁኔታ አሁንም #አሳሳቢ መሆኑን አብመድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡ ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አባወረኛ አካባቢ ነዋሪዎች ለአብመድ እንደተናሩት ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ #ቆሟል፤ ቀስት #የሚያስወነጭፍም የለም፡፡ ጥቃት አድራሾቹ በከፊል ወደ #ጫካ ውስጥ #ሸሽተዋል፤ በከፊልም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ‹‹በዚህም ግልጽ የሚታይ ግጭት የለም፤ የሰላም ድባብ ግን #አይታይም›› ብለዋል፡፡

ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ከትናንት ምሽት 12፡00 አካባቢ ጀምሮ እስካሁን ግጨት አለመኖሩን ገልጸው ያንዣበበ #ስጋት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ ትናንት ቤቶች መቃጠላቸውንና የተናገሩት እኚሁ አስተያየት ሰጪ ዛሬ ከሰዓት በኋላ #የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ ቅድመ ዝግጅት እንዳለ በመጠቆም መንግሥት #ጥፋት እንዳይደርስ እንዲቆጣጠር #አሳስበዋል፡፡ ‹‹ወንዶች ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን እያሸሹ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ ትናንት ሙሉ በሙሉ ቤተሰባቸውን ከአካባቢው ያሸሹ ሰዎችም አሉ፤ የትናንቱ ጥቃት አድራሽ ቡድንም ዛሬም ለሌላ ጥፋት እየተንቀሳቀሰ በከፊል በቁጥጥር ሥር ሲውል ተመልክቻለሁ፡፡ ቀስትና የጦር መሣሪያ የያዙ ቡድኖች ወደ መንደር 49 እየተንቀሳቀሱ አባት በለስ ወንዝ ድልድይ ላይ መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ይዘዋቸዋል›› ብለዋል አስተያየት ሰጪው።

በበለስ ከተማ መንደር ሁለት ነዋሪ የሆኑ አስተያየት ሰጪም የጦር መሣሪያና ቀስት የያዙ ከ30 በላይ ሰዎች በለስ ወንዝ አካባቢ መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ረፋድ 3፡30 አካባቢ #ተይዘው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹አባወረኛ ላይ ብዙ ነገር ወድሟል፤ የክልሉ መንግሥት ምን እንደሚያደርግ #አናውቅም፤ እንዲያውም የመንግሥት ባለስልጣናት ሴራ እንዳለበት እናምናለን፡፡ የምናደርገው ግራ ገብቶናል›› ብለዋል ነዋሪው፡፡

መንግሥት ግጭቶችን ከማብረድ በውጥን ላይ ማስቀረትን ትኩረት እንዲሰጥ ያሳሰቡት ነዋሪዎቹ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ኃይል በብዛት ወደ አካባቢው እንዲገቡና ለረዥም ጊዜ ቁጥጥር እንዲያደርጉ በተለይም ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚኖር የሚሰጋውን ጥቃት እንዲያከሽፉም ጠይቀዋል፡፡ ‹‹አሁን ግጭቱ ያለው ቀይና ጥቁር በሚል ነው፤ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የፌዴራል መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ ካልፈለገ ሁኔታው አሳሳቢ ነው›› ብለዋል አስተያዬት ሰጭዎቹ፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia