TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ አየር መንገድ #አንድ_ሚሊዮን_ዳያስፖራ ወደ ሀገር እንዲገባ በቀረበው ጥሪ መሰረት ወደ አገር ቤት ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቅናሽ ያለበት መስተንግዶ እንደሚሰጥ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

አየር መንገዱ ከአውሮፓ ፣ ሰሜን አሜሪካና ኬሎችም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲገቡ በራሱ በኩል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚፈለገውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትኬት ቅናሽ እንዲሁም ተጨማሪ የሻንጣ የኪሎ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና አየር መንገዱ የማይበርበትም ሥፍራ ቢኖር፣ ገበያውን ለማምጣት እንደሚሰራ ከአየር መንገዱ መስማቱል ሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚ ቀደምም ሆነ ወደፊትም ለልዩ ልዩ በዓልና ተመሳሳይ ወቅቶች የተለየ ቅናሽ እንዲሁም አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በሌላ አጭር መረጃ ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ''ቢዝነስ ትራቭለርስ '' መጽሄት የሚያዘጋጀውን “የ2021 የቢዝነስ ተጓዦች የአፍሪካ ምርጥ” አሸናፊ ሆኗል።

አየር መንገዱ ሽልማቱን ሊያገኝ የቻለው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያያዘ እየወሰዳቸው ያሉ ቅድመ ጥንቃቄዎች ፣ ከጉዞ ትኬት ጋር በተገናኘ የሚሰጠው ፈጣን ምላሽ እንዲሁም በወረርሽኙ ወቅት ለተከሰቱ የጉዞ መስተጓጐሎች ለሰጠው የተቀላጠፈ የጉዞ ማስተካከያ አገልግሎት እና ተያያዥ መስፈርቶች በቢዝነስ መንገደኞች በመመረጡ ነው።

@tikvahethiopia