TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ባህር ዳር-የሰላም ዋጋ ስንት ነው?🔝

በዛሬው ዕለት #በባህርዳር ከተማ "የሰላም ዋጋ ስንት ነው?" በሚል የጎዳና ላይ #የሰላም_ጉባኤ ተካሂዷል።

Via NAH(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከባሌ ጎባ🔝

"ሰላም ፀግሽ እንዴት ነህ ባለፈው ግዜ በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ደርሶ እንደነበር፥ #እሳቱም ለ1 ሳምንት ዘልቆ እንደነበር ይታወቃል። ይሁን እንጂ ዛሬም እሁድ 15/07/2011 በድጋሚ በፊት ከነበረው #በይዘት_ጨምሮ እየተቃጠለ ነው። እባክህ የሚመለከተው አካል በፍጥነት መፍትሔ እንዲያደርግ።" ባህራን ሶሎሞን ነኝ ከባሌ-ጎባ ከተማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

#በባሌ_ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በድጋሜ #የእሳት_ቃጠሎ ተከሰተ። ከሳምንታት በፊት ስድስት ቀናት የዘለቀ ቃጠሎ በፓርኩ ውስጥ መከሰቱ ይታወሳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ🔝

በባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ #በድጋሜ የእሳት ቃጠሎ ተከሰተ። ባለፋት ሳምንታት ለተከታታይ ስድስት ቀናት እንዲሁ በጥበቃ ቦታው ላይ የዚህ አይነት የእሳት ቃጠሎ በመነሳት ስፋት ያለው በአስታ ደን የተሸፈነ የፓርኩ አካል መውደሙ የሚታወቅ ነው።

በሌሎቹ የጥበቃ ቦታዎቻችንም ቢሆን እንዲሁ የዚህ አይነት ቃጠሎ በሰው ሰራሽ ችግር ምክኒያት በተደጋጋሚ የሚከሰት ሲሆን በመከላከያ ሠራዊት፣ በፌደራል ፓሊስ፣ በፈቃደኛ ወጣቶችና በአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ እርብርብ እየተደረገ የተነሳውን እሳት መቆጣጠሩ የተለመደ ነው።

የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በአገራችን ከሚገኙት ከፍተኛ ተራሮች መካከል የቱሉ ዲምቱ እና የሰናቴ ፕላቶዎች የሚገኙበት በመሆኑ አብዛኛው የመሬቱ አካል በአስታ ዛፎች የተሸፈነ ነው። በተጨማሪም የዚህ እጽዋት ዝርያዎች በቀላሉና በፍጥነት በእሳት የሚቀጣጠል ከመሆኑም በተጨማሪ ወደ ስሩ አካባቢ ያለው ግንድ እሳቱን ይዞ ስለሚቆይ የጠፋ ይመስልና ንፋስ ሲያገኝ እንደገና ይቀጣጠላል። ይህ ባህሪው አካባቢውን ከእሳት ለመታደግ አስቸጋሪ ያደርገዋል።

አሁን ላይ በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ቀናትን ያስቆጠረ ሲሆን እንደተለመደው እሳቱን ለመቆጣጠር የፀጥታ ሃይሉና ህብረተሰቡ ወደ ቦታው በመሄድ እሳቱን እያጠፋ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም የቃጠሎውን መንስሄ ለማወቅ በሚደረገው ጥረት የአካባቢው ፓሊስ #የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በህግ #ቁጥጥር_ስር አውሎ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን የፓርኩ ሃላፊ አቶ አስቻለው ገልፀውልናል።

Via ኢ.ዱ.ል.ጥ.ባ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች
ፎቶ፦ TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት/ኢጋድ/ የ100 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንግ ግዢ በቅርቡ እንደሚፈጽም አስታውቋል። ኢጋድ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ለመግዛት ቃል ከገባው 250 ሺህ የአሜሪካን ዶላር 100 ሺህ ያክሉን በቅርቡ እንደሚገዛ የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ አምባሳደር ማህቡብ ሟሊም ገልጸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ዶክተር አምባቸው መኮንን የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ትናንት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ምክትል ሊቀ መንበሩን እና አዳዲስ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚዎችን መርጧል። በዚህ መሰረት

1. አቶ ደመቀ መኮንን የአዴፓ ሊቀመንበር

2. ዶ/ር አምባቸው መኮንን ምክትል ሊቀመንበር

3. አቶ ላቀ አያሌው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ( አዲስ)

4. አቶ መላኩ አለበል የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ

5. አቶ ምግባሩ ከበደ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ

6. አቶ ዮሀንስ ቧያለው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ( አዲስ)

7. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ

8. አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ

9. አቶ ብናልፍ አንዱአለም የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ

10. አቶ ተፈራ ደርበው የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

11. ዶክተር ይናገር ደሴ የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

12. አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

13. አቶ ፀጋ አራጌ የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆነው መመረጣቸውን ከአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ናዝራዊት ቻይና ውስጥ #በሞት እንድትቀጣ አልተፈረደም!"

ቻይና ውስጥ ላለፉት #ሶስት_ወራት እፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ እስር ላይ ስለምትገኘው #ናዝራዊት_አበራ በዛሬው ዕለት የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ #ነቢያት_ጌታቸው ከአለም አቀፉ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር ቆይታ አድርገው ነበር። የሰጡት መረጃምይህንን ይመስላል፦

"ቻይና ሀገር ያሉ የኛ የቆንስላ ፅ/ቤት ሰራተኞች ሶስት ግዜ እስር ቤት ሄደው አይተዋታል። የመጨረሻው ጉብኝት እንደውም ያለፈው አርብ ነበር። ላረጋግጥልህ የምችለው የሞት ፍርድ ተፈረደባት የሚባለው ውሸት መሆኑን ነው። ሂደቱ ገና ነው። የሀገሪቱ አቃቤ ህግ ገና ክሱን ያቀርባል። ከዛ በሁዋላ ነው ጉዳዩ ፍርድ ቤት ሄዶ የሚወሰነው። እስካሁን እፅ ነክ በሆነ ወንጀል ተጠርጥራ ነው ያለችው። እንደ ዜጋችን አሁን መጠየቅ የምንችለው የኮንሱላር ድጋፍ ማረግ ነው። እሱን ደሞ እያገኘን ነው። #ትክክለኛ_ፍርድ እንድታገኝ እና ጠበቃ የማግኘት መብት እንዲኖራት ክትትል ይደረግበታል። የፍርድ ደረጃ ላይ ሲደረስም clemency (ምህረት) የሚጠየቅበት ሁኔታ የተለመደ ነው። እነሱም ያሉን ጉዳዩ በቻይና ህግ የተያዘ ነው ብለውን ነው።"

ምንጭ፦ ETHIO-NEWSFLASH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የ˝ፀረ- ጥላቻ ንግግር˝ን አዋጅ አያረቀቀ ነዉ፦

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከ˝ፀረ ጥላቻ ንግግር˝ አዋጅ በተጨማሪ በርካታ ህጎችን በማሻሻል ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡ በጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ እንደተናገሩት የ˝ፀረ ጥላቻ ንግግር˝ አዋጅን የሰዎችን የመናገር ነፃነት #ሊገድብ በማይችል መልኩ እና ከህግ መንግስቱ ጋር #ሊጋጭ በማይችል መልኩ ለማፅደቅ አስፈላጊ ጥናቶች ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ ከሌሎች ህጎች ፈጥኖ የሚጸድቀው ይህ ˝የፀረ ጥላቻ ንግግር˝ አዋጅ ኢትዮጵያ ላይ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ብሄሮች እና ማንነቶች ላይ በጥላቻ ንግግር ምክንያት የሚደርሰውን ችግር እና ግጭት ለማስቀረት እንደሚያግዝ አቶ ዝናቡ ተናግረዋል፡፡

Via Arts TV World
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትግራይ ክልል ምክር ቤት የትግራይ መልሶ መቋቋም ተቋም/ትእምት/ ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት እንዲሆን የቀረበለትን ሀሳብ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡ ምክር ቤቱ 5ኛ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባኤ ከትላንት ጀምሮ በሶስት የክልሉ ቢሮዎች ስራ አፈጻጸምና በቀረቡለት ረቂቅ አዋጆች ውይይቱን ቀጥሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Free_Nazrawit_Abera
(ከቴዲ አፍሮ)

ኢትዮጵያዊቷ እህታችን ወ/ሪ ናዝራዊት አበራ በየዋህነቷ ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በሃገረ ቻይና ወህኒ ቤት ትገኛለች።

ወጣቷ መሃንዲስ ናዝራዊት አበራ ለእስር የበቃችበትና የተከሰሰችበት ወንጀል እስከ ሞት ቅጣት ሊያስፈርድባት እንደሚችልም ቤተሰቦቿ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በመቅረብ እየተናገሩ ነው። የናዝራዊት ቤተሰቦች ቻይና የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሚችለው መንገድ ሁሉ እየተባበራቸው እንደሚገኝ እየተናገሩ ቢሆንም ከጉዳዩ መክበድ ጋር በተያያዘ የመንግሥት፣ የሁሉም ኢትዮጵያውያን፣ የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማትና የመገናኛ ብዙኃንን ርዳታና ድጋፍ የሚያስፈልግበት አስጨናቂ ጊዜ ላይ መድረሳቸውን አሳውቀዋል። በናዝራዊት ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወላጅ እናቷ ግማሽ አካላቸው የማይታዘዝ (Paralyze) መሆኑንም በሚያሳዝን ሁኔታ ተረድተናል።

በዚህም መሰረት የሞት አደጋ የተደገነባትን እህታችንን ለመታደግ በሚያስፈልገው ሁሉ ለመተባበር፣ በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ ሳይሆን ሰው በመሆናችንም ጭምር አቅማችን የሚፈቅደውን ሁሉ ለማድረግ ከናዝራዊትና ከቤተሰቦቿ ጎን መቆማችንን እናሳውቃለን።

በናዝራዊት ቤተሰቦችና ጓደኞች በኩል የተጀመረውን የኦንላይን ፊርማ የማሰባሰብ ሂደት በኩልም ጉዳዩ የበለጠ አለም አቀፍ ትኩረት እንዲኖረው ሁላችንም ወደ ድረገፁ በመግባት እንድንፈርምም ጥሪያችንን ለመላው ኢትዮጵያውያን እናቀርባለን።

https://www.change.org/p/the-prime-minister-office-of-ethiopia-free-nazrawit-abera-from-guangzhou-prison
ከሁሉም በላይ ሁሉን ማድረግ የሚቻለው ፈጣሪያችን እግዚአብሔር እህታችን ላይ ከተደገሰባት የሞት አደጋ ይታደጋት ዘንድ በፀሎት እንለምነው።

ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)
#update የመከላከያ ሠራዊትን ደንብ ልብስ በመልበስ በአምቦ ከተማ ዘረፋ ሊፈጽሙ የነበሩ ሁለት ጥንዶችን ይዣለሁ ብሏል ፖሊስ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ትናንት በኅብረተሰቡ ጥቆማ የተያዙት ቀበሌ 2 አራዳ በሚባል ቦታ ነው፡፡ በቤታቸው በተደረገ ፍተሻም 1 ሽጉጥ፣ 4 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮችና የመከላከያ ደንብ ልብሶች እንደተገኘ ኢዜአ ፖሊስን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹አዲስ አበባ የሁሉም #ኢትዮጵያውያን ከተማ እንደሆነች የኢህአዴግ እህት ፓርቲዎች ያምናሉ፡፡ ይህን ባለማመን የኃይል ርምጃን የሚያስተናግድ የፖለቲካ ርዕዮት አይኖርም፡፡›› አዴፓ
.
.
''አዴፓ በስግብግብነት የታሪክ እና የቦታ ሽሚያ ውስጥ አይገባም፡፡'' አዴፓ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ማዕከላዊ ኮሜቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው በፓርቲው የሁለት ቀናት የውይይት ጭብጦችና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ማዕከላዊ ኮሜቴው በክልሉ ያለውን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮች ለሁለት ቀናት ገምግሟል። ለውጡን ለማስቀጠል የሚረዱ ተግባራት ጥሩ ቢሆኑም በሂደቱ ግጭቶች እና የሰላም ውስንነቶች መፈጠራቸውንና አመራሩን የማጠናከር ሥራ መሠራቱን የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ዮሐንስ በመግለጫው ላይ አንስተዋል።

በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ከባለፉት ዓመታት በተለየ መንገድ ከእኛ ጋር አብሮ ለመሥራት ፍላጎት እያሳዩ ነው›› ያሉት የጽሕፈት ቤት ኃላፊው ወጣቶች በለውጡ የተጋረጡ ችግሮችን በመታገል የአማራን ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት ፓርቲው እንደሚያመሠግን ተናግረዋል፡፡

ተፎካካሪ ፓሪቲዎች የያዛችሁትን ዓለማ ለማሳካት በሕጋዊ መንገድ ለምታደርጉት እንቅስቃሴ አዴፓ ድጋፍ ያደርጋል ያሉት ሀላፊው ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍልም የአካባቢውን ሰላም በሚያስከብርበት ወቅት አልፎ አልፎ ችግሮች መታዬታቸውንም በመግለጫው አንስተዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ቀናት በባሕር ዳር እና ደሴ የታዩ ችግሮች ከኅብረተሰቡ የሰላም ፍላጎትና የንቃት ደረጃ የማይመጥኑ ደካማ ድርጊቶች እንደነበሩ ነው የተናገሩት፡፡ ኅብረተሰቡ እና የፀጥታ ኃይሎች ችግሩ ወደ አስከፊ ደረጃ እንዳይሄድና በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መቆጣጠር መቻላቸው የሚደነቅ እንደሆነም ማዕከላዊ ኮሚቴው መገምገሙን በመግለጫቸው አመላክተዋል፡፡

አቶ ዮሐንስ በአዴፓ እና ኦዴፓም ሆነ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን ተናግረዋልው፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ፖለቲካ ታፍኖ የነበረ በመሆኑ የልዩነት ሐሳብ ቅራኔ ይመስላል፤ ግን ጤናማ የአስተሳሰብ ለውጥ ነው፡፡ በድሮ ኢህአዴግ ብዙ የታፈኑ ድምፆች ስለነበሩ ልዩነቶች አይንፀባረቁም፤ ሕዝቡም አልለመደውም፡፡

አሁን እነዚህ የዴሞክራሲ እና የሐሳብ
ብዝኃነቶች ሲስተናገዱ ሕዝቡ ሊደናገጥ አይገባም፡፡ በእኛ እና ኦዴፓ መካከል ልዩነት የተፈጠረ መስሏቸው የሚቦርቁም አሉ፤ ለእነዚህ መርዷቸውን ንገሯቸው፡፡ እኛ የኢትዮጵያን የወደፊት ዕድል ብሩህ ለማድረግ እየሠራን ነው›› ብለዋል፡፡

‹‹ከትግራይ መንግሥት ጋርም ዘራፊዎችን አሳልፎ አለመስጠቱ እንጂ ሌላ ቅሬታ የለንም›› ያሉት አቶ ዮሐንስ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር በሂደት በደም እና በዝምድና የተሳሰረው የአማራና የትግራይ ሕዝብ ዘራፊዎችን አብረው እንደሚታገሉም የፓርቲያቸው እምነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

‹‹አዴፓ በስግብግብነት የታሪክ እና የቦታ ሽሚያ ውስጥ አይገባም፡፡ ከሌሎች ሕዝቦች የተለዬ ጥቅም ለአማራ በማምጣት ለሌሎች ስጋት እንዲታይም አይሰራም›› ነው ያሉት፡፡ አዲስ አበባ
የሁሉም ኢትዮጵያውያን ከተማ እንደሆነች የኢህአዴግ እህት ፓርቲዎች እንደሚያምኑ በመግለጽ ይህን ባለማመን የኃይል እርምጃን የሚያስተናግድ የፖለቲካ ርዕዮት አንደማይኖርም ጠቁመዋል፡፡

‹‹አሁን የሚፈጠሩት ችግሮች በጭቆናው ዘመን ታፍነው የነበሩ የተከማቹ ድምፆች ውጤት ናቸው፡፡ የሕዝቡ መከፋት እና መቆጨት ደግሞ ለለውጡ መልካም ጫና መሠረት የጣሉ ናቸው›› ብለዋል አዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ዮሐንስ ቧያለው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ ኩባንያ በ737 ማክስ አውሮፕላን የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር ማሻሻያ ላይ ባዘጋጀው ስብሰባ እንደማይሳተፍ አስታወቀ። ቦይንግ ከመላው ዓለም ለተውጣጡ ከ200 በላይ የአውሮፕላን አብራሪዎች፣ የቴክኒክ ባለሙያዎች እና ባለሥልጣናት በቦይንግ 737 ማክስ የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር ማሻሻያ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ አቶ አስራት በጋሻው በስብሰባው "እስካሁን ለመሳተፍ እቅድ የለንም" ሲሉ ለሬውተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ IOT ተማሪዎች ላለፉት ቀናት ውሃ በመጥፋቱ እጅግ በጣም እንደተቸገሩ ተናግረዋል። የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia