TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ‼️

በኒውዮርክ ታይምስ እና በአንዳንድ ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን እየወጣ ያለው የተሳሳተ እና የተዛባ ዘገባ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያሳዘነ መሆኑን አየገለፀ፤ ትክክለኛውን መረጃ እንደሚከተለው ያቀርባል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አብራሪዎች ቦይንግ ባወጣው እና በFAA በፀደቀው በቦይንግ 737 NG እና በቦይንግ 737 ማክስ ያለውን ልዩነት ስልጠና በሚገባ የወሰዱ፣ በቦይንግ 737 ማክስ ወደ አየር መንገዱ ከመግባቱ አስቀድሞ እና በረራ ከመጀመራቸው በፊት የተጠናቀቀ ስልጠና የወሰዱ መሆኑን አየር መንገዱ ያረጋግጣል።

በቀጣይነትም #በኢንዶኔዥያው ላይን ኤር የደረሰውን አደጋ ተከትሎ የአሜሪካው FAA ያወጣው ተጨማሪ መመሪያ ለሁሉም የሚመለከታቸው አብራሪዎች እንዲያውቁት መደረጉንና ደረጃውን የጠበቀ አስፈላጊ ገለፃ ተደርጓል። በዚህም መሰረት የመመሪያው ይዘት ሙሉ በሙሉ በስልጠና ማኑዋል፣ በኦፕሬሽን ዝርዝር መመሪያዎች እና በዕለት ተዕለት ስራዎች ዝርዝር መመሪያዎች ተካተዋል።

በዚህ አጋጣሚ አየር መንገዱ መግለፅ የሚፈልገው ቦይንግ 737 ማክስ ምስለ በረራ አሁን በዓለማችን አከራካሪ የሆነውንና ለአደጋውም ዋና መንስኤ ይሆናል ተብሎ የሚገመተውን MCAS (Maneuvering Characteristics Augmentation System) ችግር ለማሳየት ታስቦ እንዳልተሰራ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአለም አቀፍ የአደጋ ምርመራ ስነ-ስርዓት እና ህጎች መከተል ስላለበት የምርመራውን ውጤት በትዕግስት እየተጠባበቀ ለሚመለከታቸው ሁሉ ማለትም የሀገር ውስጥም ሆነ የአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የአደጋውን መንስዔ መላምት ከማስቀመጥና በተሳሳተ መረጃ ህዝብ ከማሳሳት እንዲቆጠቡ ያሳስባል።

Via የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia