TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ክፍያ 4 ብር ሆነ!

የአዲስ አበባ #ቀላል_ባቡር_ትራንስፖርት አገልግሎት በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ለሚደረግ አንድ ጉዞ የሚያስከፍለውን ታሪፍ 4 ብር እንዲሆን መወሰኑን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

የዛሬ ሶስት ዓመት ገደማ ሥራ የጀመረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ለተለያዩ ርቀቶች የተለያየ ታሪፍ ያስከፍላል። ኮርፖሬሽኑ ለአጭር ርቀት 2 ብር፣ ለመካከለኛ ርቀት 4 ብር እንዲሁም ለረጅም ርቀት 6 ብር ታሪፍ የክፍያ ስርዓት ሲጠቀም ነው የቆየው።

ሆኖም ከመጪው ነሐሴ 12 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ በሁሉም ርቀት ለሚደረግ አንድ ጉዞ አራት ብር የትኬት ታሪፍ ብቻ ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኑን ኮርፖሬሽኑ ገልጿል።

የታሪፍ ለውጡ ምቹ የቁጥጥር ስርዓት ለመዘርጋት፣ ከትኬት ህትመት ጋር የተያያዙ ወጪዎችን ለመቀነስ፣ የትኬት ስርዓቱን ዘመናዊ ለማድረግ እንደዚሁም ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም ጠቅሷል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia