TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ተጠንቀቁ

UNICEF 2,800 ሰራተኞችን ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል ?

UNICEF ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚዘዋወረውን አይነት ምንም የቅጥር ማስታወቂያ #አላወጣም

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምትመለከቱት አይነት ሀሰተኛ የቅጥር ማስታወቂያ በስፋት እየተዘዋወረ ነው።

ማስታቂያው UNICEF በትግራይ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ለሚገኙ ዜጎች በ3 የስራ መደቦች የተመዘገቡ ሰራተኞችን አሰልጥኖ ለመቅጠር ይፈልጋል የሚል ነው።

በዚሁ ሀሰተኛ የቅጥር ጥሪ ፤ በባችለር ዲግሪ ፣ በማንኛውም ትምህርት መስክ ፣ በ0 ዓመት ፣ በ24,700 ብር ደመወዝ 2,800 ሰራተኞች እንደሚፈለጉ ይገልጻል።

በጣም የሚያስገርመው የስራው አመልካቾች የሚያመለክቱበት ሀሰተኛ አድራሻ የተቀመጠ ሲሆን በዚሁ አድራሻ ተመዝጋቢዎች የማመልከቻ ፎርም ሲሞሉ 1,000 ብር በCBE Birr ወይም በTelebirr ቀድመው እንዲከፍሉ ይጠይቃል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ይህ ፍፁም ሀሰተኛ እንዲሁም በርካታ ወጣቶችን ለማጭበርበር እየተደረገ ያለ እንቅስቃሴ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከUNICEF ተጨማሪ መረጃ ያገኘ ሲሆን በኦንላይን እየተሰራጨ ያለው ሀሰተኛ የቅጥር ማስታወቂያ መሆኑን ገልጿል።

UNICEF የስራ ዕድል የሚያስተዋውቀው በይፋዊ ድረገፁ unicef.org/careers/ ላይ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል። ከዚህም ባለፈ በየትኛውም የቅጥር ሂደት ገንዘብ እንደማያስከፍል እንዲሁም የባንክ መረጃን እንደማይጠይቅ አሳውቋል።

@tikvahethiopia