በሻሸመኔ አሰቃቂ ግድያ ሊመሰክር የነበረው ሰው ደብዛው ጠፍቷል‼️
.
.
ሻሸመኔ ላይ ሰው #ገድለው በመስቀል በአስከፊ ግድያ ወንጀል የተከሰሱ ወጣቶች ላይ ሊመሰክር የነበረው ሰው #ደብዛው_ጠፍቶብኛል ሲል የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።
#በሻሸመኔ_ከተማ ነሐሴ ስድስት ቀን 2010 ዓ.ም አንድን ወጣት #ቦንብ ይዟል በሚል ገድለው የዘቅዝቁ ወጣቶች መኖራቸው ይታወሳል። በዚህ በአሰቃቂ ግድያ ወንጀል ከተከሰሱ ስድስት ሰዎች መካከል ሁለቱ የዕድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደባቸው እና የተቀሩት አራት ተጠርጣሪዎቸ ደግሞ ምስክሩ ደብዛው በመጥፋቱ በነጻ መለቀቃቸውን የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል አቃቢ ህግ አቶ #አሽማው_ሰይፉ ገልጸዋል። ተከሳሾች የምስክሩን ደብዛ አጥፍተዋል የሚል ግምት እንዳለ የገለጹት አቶ አሽማው፤ ምስክሩ ባስመዘገበው ስልክ ቁጥርም ሆነ በአድራሻው ተፈልጎ እስከአሁን ሊገኝ አለመቻሉን ተናግረዋል።
በተለያዩ #ማህበራዊ_ሚዲያዎች ጨመሮ በግለሶችና በተቋማት የሚገኙ የምስል እና ድምጽ ማስረጃዎች እንደምስክርነት ለምን ጥቅም ላይ አልዋሉም የሚል ጥያቄ ከአዲስ ዘመን የቀረበላቸው አቶ አሽማው፤ የምስልና ድምጽ #ማስረጃዎቹ ከፖሊስና ከተለያዩ አካላት ለፍርድ ቤቱ መቅረባቸውን ተናግረዋል። ይሁንና ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ #ቅንብረ የተደረገበት ስለመሆኑ እና ስላለመሆኑ ማረጋገጫ ባለማግኘቱ ማስረጃው ፍርድቤቱን ሊያሳምን አልቻለም።
እንደ አቶ አሽማው ከሆነ፤ አራቱ ተከሳሾች በነጻ ቢለቀቁም የሰው ምስክሩ በተገኘ ሰዓት ክሱ መጀመሩ አይቀርም። በፍርድ ሂደቱ ላይ የአራቱ ሰዎቸ በነጻ መለቀቅ በአቃቤ ህግ በኩል ተቀባይነት ባለማግኘቱ ይግባኝ ተጠይቄ ውሳኔ እየተጠበቀ ይገኛል ብለዋል።
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን(የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia

" ' ሳር ቤት አካባቢ በአውቶብስ ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈፀመ ' እየተባለ በቲክቶክ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ሀሰተኛ ነው " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ፤ ሀሰተኛ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ።
ፖሊስ ፤ የከተማው ሰላም መሆን እንቅልፍ የነሳቸው አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች የተለያዩ የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ስጋት ላይ ለመጣል በቻሉት መጠን ሁሉ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል።
እነዚህ አካላት ህዝቡ ደህንነት እንዳይሰማውና ከተማውም ሰላም አንደሌለው ለማሳየት ብዙ ሞክረው አልሳካ ሲላቸው የፈጠራ ሀሰተኛ ወሬ በማህበራዊ ሚዲያ ይዘው መጥተዋል ሲል ገልጿል።
ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ ጥቃት ለመፈፅም በህቡዕ የተደራጀ ቡድን እንዳለ በማስመሰል ሳር ቤት አካባቢ አውቶቡስ ላይ #ቦንብ_ማፈንዳቱን የሚገልፅ የፈጠራ ወሬ እያሰራጩ ይገኛሉ ብሏል።
" ይህ ከእውነታ የራቀ በአዲስ አበባ ሰላም የለም ለማስባል ሆን ተብሎ የተሰራጨ የሀሰት መረጃ ነው " ያለው ፖሊው ሁሉም የከተማው ነዋሪ ይህን ሊገነዘብ ይገባል ብሏል።
ፖሊስ ፤ የከተማዋን ሰላም የማይፈልጉ አካላት የሌት ተቀን ህልማቸውን " ቲክ ቶክ /#TikTok " በተባለው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየገለፁ ናቸው ብሎ " በአዲስ አበባ ያለው ሰላም አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል ፖሊስ ከመቼውም ጊዜ በላይ የፀጥታ ስራውን እያከናወነ ይገኛል " ሲል ገልጿል።
ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችን ከትክክለኛው ቦታ የማግኘት ባህሉን ሊያዳብር እንደሚገባ አሳስቧል።
ሀሰተኛ መረጃን በሚያሰራጩ አካላት ላይም በህግ አግባብ ተገቢው እርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል።
@tikvahethiopia