TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Breaking

በኒውዚላንድ ሁለት መስጊዶች ላይ በታጠቁ ሀይሎች በተፈጸመ ጥቃት 49 ሰዎች ሲገደሉ 20 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተነገሯል፡፡ የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ጥቃቱ የሽብር ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በጥቃቱ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለጽም ጉዳዩ በመንግስት ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው ነዋሪዎቹ የጁማ ሰላት ላይ እንዳሉ የታጠቁ ኃይች ወደ እምነት ቷማቱ በመግባት በከፈቱት የተኩስ ሩምታ ነው ተብሏል፡፡ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል መንግስት የአካባቢው ነዋሪዎቹ ከቤታቸው እንዳይወጡና የተለየ እንቀስቃሴ ካለ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ማስተላለፉም ነው የተገለጸው፡፡ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 6 ተጠርጣዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተገለጸ ሲሆን÷ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ሶስቱ ሴቶች ናቸው ነው የተባለው፡፡

ምንጭ፡- ቢ ቢ ሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢ/ር ታከለ ኡማ ከፈረንሳይ ኩባንያዎች ጋር ተወያዩ፡፡ ከፈረንሳዩ ፕረዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የልዑካን ቡድን ጋር ወደ አዲስ አበባ የመጡት ግዙፍ የፈረንሳይ ኩባንያዎች እና የፋይናንስ ተቋማት በዛሬው ዕለት ከኢ/ር ታከለ ኡማ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ኩባንያዎቹ በስማርት ሲቲ ግንባታ ፣ በትራንስፖርት ፣ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ፣በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ፣ በስፖርት ማዘውተርያ ግንባታ እና በትምህርት ዘርፍ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ኢንቨስት እና የፋይናንስ ድጋፍ በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ ከኢ/ር ታከለ ኡማ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የከተማውን ነዋሪ ህይወት ለመቀየር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው የፈረንሳይ ኩባንያዎች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚኖራቸው ተሳትፎ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡ በመጨረሻም ከሁለቱም ወገን ምክክር የተደረገባቸው ጉዳዮች በአፋጣኝ ወደ ተግባር እንዲቀየሩ ሁኔታዎችን የሚያመቻች ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የ14ኛው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድሮች በባሕር ዳር ተጀምሯል፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጌዴኦ‼️

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ #ሙፈርያት_ካሚል ከአጎራባች አካባቢ ተፈናቅለው በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ ተጠልለው የሚገኙ ዜጎችን #እየጎበኙ ነው፡፡ ሚኒስትሯ በገደብ ወረዳ ገደብ ስታዲየም የተጠለሉትን እነዚህን ተፈናቃዮች አጽናንተዋል፡፡ መንግስት ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በዚህ ወቅት ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትሯ ከተፈናቃይ ተወካዮች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል፡፡ በአሁኑ ወቅት በገደብ ወረዳ ከ96ሺ በላይ ተፈናቃዮች ተጠልለው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

ምንጭ፡- ኢ. ዜ. አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ካናቢስ

በአማራ ክልል ደምበጫ ወረዳ ከካናቢስ ለሚዘጋጅ መድሃኒት የፋብሪካ ግንባታ ፍቃድ እንዳልሰጠ መንግስት አስታወቀ።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን የካናቢስ ምርትን በሀገሪቱ ለመድኀኒትነትም ሆነ ለሀገር ውስጥና ለወጪ ንግድ ማምረት የጤና ሚኒስቴር ፍቃድም ሆነ እውቅና አልሰጠም ብለዋል።

ሚኒስትሩ በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ሀገራት ለሚመጡ ባለሀብቶችም የካናቢስ ምርት የሚከለከል መሆኑን በተደጋጋሚ ማሳወቃቸውን ነው ያስታወቁት።

የአማራ ክልል መንግስትም ባወጣው መግለጫ አንድ አንድ አካላት በሀገርና በዜጎች ጤንነት ላይ አደጋ ከሚያደርሰው የካናቢስ ዕፅ መድሃኒቶች ለማምረት የሚያስችል ፋብሪካ በደንበጫ ወረዳ ለመገንባት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

ሆኖም በክልልም ሆነ በከተማ ደረጃ ለዚህ አይነት ፋብሪካ ፍቃድ እንዳልተሰጠ የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን፥ ፍቃድ የሰጠ አካል ካለም በአፋጣኝ እንዲመልስ አሳስቧል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
•ሀዋሳ
•አዲስ አበባ

በአዲስ አበባና በሀዋሳ ከተማ የምትገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ለጌዴኦ ተፈናቃዮች ድጋፍ እና እገዛ ለማድረግ ተዘጋጁ። በምግብ፣ በንፅህና መጠበቂያ፣ በአልባሳት...በቻላችሁት አቅም ድጋፍ የምታደርጉባቸውን መንገዶች እናሳውቃችኃለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በድሬዳዋ ከተማ የትራፊክ ህግ በማስከበር ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ የትራፊክ ፖሊስ በባለ 3 እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ ተገጭቶ ህይወቱ አልፏል፡፡

ረዳት ኢኒስፔክተር #ዮናታን_ባልቻ የተሰኘው የትራፊክ ፖሊስ በድሬዳዋ ከተማ ከሳቢያን መልካ ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሚወስደው በግንባታ ላይ በሚገኘው አዲስ መንገድ የቁጥጥር ስራ እያከናወነ ባለበት ወቅት ነው አደጋው የደረሰበት።

የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዋና ሳጅን #ባንተ_አምላክ ግርማ እንደተናገሩት ሟቹ ስራውን እያከናወነ ባለበት ሰዓት ሲኖትራክ መኪና ባለ 3 እግር መኪናውን ሲገጨው ከቁጥጥር ውጭ በመውጣቱ የትራፊክ ፖሊሱ ላይ ጉዳት አድርሷል። በትራፊክ አደጋው በስራ ላይ የነበረ ሌላ የትራፊክ ፖሊስ ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport UEFA Champions League------Quarter Final Draw

AFC Ajax vs Juventus
Liverpool FC vs FC Porto
Tottenham Hotspur vs Manchester City
Barcelona vs Manchester United

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ቴሌቶን ተዘጅቷል‼️

በአማራ ክልል እና ከክልሉ ውጭ #የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡

ነገ መጋቢት 7 ቀን 2011ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ተዘጋጅቷል፡፡

በአማራ ክልል እና ከክልሉ ውጭ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ነው 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብሩ የሚያስፈልገው፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት ተፈናቃዮቹን ለመርዳት በጊዜያዊነት የሰብዓዊ ዕርዳታዎችን እያደረገ መሆኑንና በዘላቂነት ደግሞ መልሶ ለማቋቋም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የሚፈለገውን የገንዘብ መጠን እና የቁሳቁስ ድጋፍ ለመሰብሰብም ነገ መጋቢት 7 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ቴሌቶን ለማዘጋጀት መርሀ-ግብር ተይዟል፡፡

በዝግጅቱ ዕርዳታ ከመሰብሰብ ባሻገር የአብሮነት እና የአንድነት መልዕክቶች እንደሚተላለፉም ታውቋል፡፡

አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለበትን የምጣኔ ሀብት ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት #ከተመረጡ አካላት ብቻ ዕርዳታ የመሰብሰብ ሥራዎችም ተጀምረዋል፡፡ በዚህም ከባለሀብቶች፣ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ከዲያስፖራዎች እና ሌሎች አካላት ዕርዳታ ለማግኘት ንዑስ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ተግባር መገባቱንም አልማን ዋቢ አድርጎ አብመድ ዘግቦ ነበር፡፡

የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶኑ 90 ሺህ 736 ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡ ከቤታቸው ተፈናቅለው ለሚገኙ አርሶ አደሮች የክረምት ጊዜ ከመድረሱ በፊት ለእርሻ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማሟላትም ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

ተልዕኮውን ‹‹አግዛለሁ›› የሚል እና ዕርዳታ ለማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ቅን ዜጋ በተለያዩ ባንኮች በተከፈቱ የሒሳብ ቁጥሮች ማስገባት እንዲችልም ቁጥሮቹ ይፋ ተደርገዋል፡፡

በዚህ መሠረት፡-

•ዓባይ ባንክ የሒሳብ ቁጥር፡ 25 62 11 25 41 58 017፣

• አቢሲኒያ ባንክ የሒሳብ ቁጥር፡ 16 24 11 37፣

•የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥር፡ 10 00 25 82 50 811 ናቸው፡፡

በሸራተን አዲስ ሆቴል በሚኖረው መርሀ-ግብር በቀጥታ ስልክ እየደወሉ ድጋፋቸውን መግለጽ ለሚፈልጉ ሁሉ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥሮች አገልግሎት እንደሚሰጡ ተነግሯል፡፡ ቁጥሮቹም፡-

09 08 91 91 91
09 08 92 92 92
09 08 93 93 93
09 08 94 94 94 ናቸው።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Sport የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ድልድል ይፋ ሆኗል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በመጠለያ ጣቢያ የነበሩ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው #መመለስ ጀመሩ። ባለፉት ጊዘያት በወቅታዊ ግጭትና አለመረጋጋት ምክንያት ተፈናቅለው  በአይምባ መጠለያ ጣቢያ ከነበሩት መካከል የነባሩ  ጭልጋ ወረዳ ነዋሪዎች ወደቀያቸው መመለስ ጀምረዋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia