TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኡቡንቱ - 'እኔ ነኝ ምክንያቱም እኛ ነን'

ቲክቫህ ቤተሰቦች - አርባ ምንጭ❤️

ኡቡንቱ - እኛ አንድ ሰብዓዊ ቤተሰብ መሆናችን ላይ የተመሠረተ የአፍሪካ ጥንታዊ ፍልስፍና ነው። እኛ ወንድምና እህት ነን። እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን፡፡ አንድ ሰው የሚበላው ሲያጣ ሁሉም ሰዎች በዚህ ረሃብ ይሰቃያሉ። አንዱ ሲበደል ሁላችንም ህመሙን ይሰማናል፡፡ አንድ ልጅ በሚሰቃይበት ጊዜ እንባዎች በሁሉም ሰው ጉንጮዎች ላይ ይፈስሳሉ፡፡ የእኛን ተቀዳሚ ሰብአዊነት በመገንዘብ፣ እኛን አንድ የሚያደርግ ጠንካራ ትስስር፣ የሰው ልጆችን በሙሉ የሚያስተሳስር የማይጠፋ ቦንድ ነው።

#Ubuntu #ኡቡንቱ #አርባምንጭ #Day2

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ጋሞዞን #ፒስሞዴል

(AFRIKHPRI FOUNDATION)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Day3 #አርባምንጭ #ኡቡንቱ

ዛሬ በአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃግብር እጅግ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።

"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"

"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"


ለሁሉም አካላት ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን!

#TIKVAH_FAMILY

#ፒስሞዴል #ቲክቫህኢትዮጵያ

#ጋሞዞን #አርባምንጭፖሊቴክኒክኮሌጅ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Day3 #አርባምንጭ #ዊዝደምአካዳሚ

"የነገ ተስፋችሁ እኛነንና ፍቅርን አስተምሩን"

ዛሬ ከሰዓት በኃላ በነበረን መርኃግብር "በዊዝደም አካዳሚ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት" ተማሪዎች ጋር ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል። ተማሪዎቹ ልዩ ልዩ የባህል ፕሮግራሞችን አዘጋጅተው የጠበቁን ሲሆን በህጻናት ግጥሞች ቀርበዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ አባቶች ተገኝተው ልጆቹን የመረቁ ሲሆን የአርባ ምንጭ የህክምና ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል #ጋሞዞን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት

የ"ኡቡንቱ አርባ ምንጭ" የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአሁን ሰዓት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተገኙበት በሃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ይገኛል።

"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"

"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"

ዝርዝር መረጀዎች ይኖሩናል!

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል #ጋሞዞን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው መርኃ ግብራችን ላይ ታዳጊ ህጻናት እንዲህ በማለት መልዕክታቸውን አቅርበዋል፡-

"እኛ ህጻናት የእናንተው ልጆች ነን ለሀገራችንም ተምረን ተስፋ የምንሆናት ትውልዶች እኛ ነን፡፡ በፍቅር አድገን ወላጆቻችንንና ሀገራችንን ማገዝ እንመኛለን፡፡"

"እኛ ህጻናት ፍቅር ያስፈልገናል፡፡ የወደፊት የሀገራችን ተስፋዎች እኛ ነንና ታላላቆቻችን ፍቅር ልታስተምሩን ይገባል"

"መልካምነትን የምንማረው ከታላላቆቻችን ነውና እባካችሁ መልካምነትን በተግባር አስተምሩን"

"አባቶቻችን ትላንት እርጥብ ሳር ይዘው ለሰው ልጅ እንዴት ክብር መስጠት እንዳለብን አስተምረውናልና እኛ ህጻናት ከልባችን እናመሰግናቸዋለን"

ይህንን መልዕክት በኮልታፋ አንደበታቸው ካቀረቡ በኀላ በትህትና ዝቅ ብለው የአባቶችን ጉልበት ስመዋል አባቶችም ህጻናቱን መርቀው የሰላም ምልክት የሆነውን ነጭ ባንዲራ አበርክተውላቸው ልጆቻቸው በሰላም እንዲኖሩ በሙሉ አቅማቸው ለሰው ልጅ ክብርና ለሰላም እንደሚተጉ ቃል ገብተውላቸዋል፡፡

#ጋሞዞን #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል #ሃይሌሪዞርት

@tikvahethiopia @tsegabwolde