TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የትምህርት_ፍኖተ_ካርታ ሰነድ⬆️

አንድ የቻናላች ወዳጅ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት መምህር #ዳንኤል_መኮንን በትምህርት ፎኖተ ካርታው ላይ ያወጣውን መረጃ ተመልከተው በሚል ልኮልኛል። እኔም መምህሩን በቻናሉ ስም በማመስገን መረጃውን እንደወረደ አቅርቤላችኋለሁ።

የትምህርት ፍኖተ ካርታ በጥቂቱ⬇️

◾️የዩኒቨርስቲ ቆይታ #ሶስት አመት የነበረው ወደ 4 አመት ከፍ ያለ ሲሆን ሁሉም ተማሪዎች በመጀመሪያ አመት ተማሪ ሲሆኑ የተለያዩ የማህበረሰብ ሳይንስ ኮርሶች ማለትም እንደ ጂኦግራፊ፣ አንትሮፖሎጂ፣ ሶሶሎጂ፣ስነ ምግባር የመሳሰሉ ኮርሶችን በመውሰድ ማህበረሰባቸውን እንዲያውቁ ይደረጋል። የመጨረሻ አመት ተማሪ ሲሆኑም ከ4 ወር እስከ 8 ወር ወደ ሌላ አካባቢ በመሄድ አገልግሎት ይሰጣሉ (ኢንተርንሺፕ)።

◾️የመምህራን ጥቅማ ጥቅም በተገቢው መልኩ ይከበራል።

◾️አጠቃላይ ፈተና በ6ኛ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ይሰጣል።

◾️ፍኖተ ካርታው ለ12 አመት ያገለግላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሔሊኮፕተር ተከሰከሰ‼️

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር በደቡብ ሱዳን አቢዬ ግዛት #ተከስክሶ ሶስት ሰዎች ሞቱ። በአደጋው የሞቱት #ሶስት ሰዎች የሔሊኮፕተሩ የበረራ #ሰራተኞች ናቸው። ከቆሰሉ ስምንት ተሳፋሪዎች ሶስቱ በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ተብሏል።

የምዝገባ ቁጥሩ UNO 379P የሆነው የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል (UNISFA) ቅጥር ግቢ ውስጥ በተከሰከሰበት ቅፅበት 23 መንገደኞች ጭኖ ነበር። የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል እንዳስታወቀው ኤምአይ ስምንት (MI-8) የተባለው ሔሊኮፕተር በተከሰከሰበት ቅፅበት ካዱግሊ ከተባለ ቦታ ወደ አቢዬ በመቀየር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች አሳፍሮ ነበር። 

በአደጋው ስምንት መንገደኞች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሶስቱ በአስጊ ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በአስጊ ኹኔታ ውስጥ የሚገኙት ተሳፋሪዎች በካዱግሊ በኩል ወደ አዲስ አበባ መወሰዳቸውንም አክሎ ገልጿል። በመግለጫው መሠረት ቀሪዎቹ አምስት መንገደኞች በአቢዬ በሚገኝ ሆስፒታል እገዛ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ሔሊኮፕተሩን ለመከስከስ ያበቃው ምክንያት እስካሁን አልታወቀም። በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ገብሬ አድሐና ጉዳዩ እየተመረመረ መሆኑን ተናግረዋል። "ዛሬ ከሰዓት በኋላ በተፈጠረው ክስተት እጅግ አዝነናል። በአደጋው ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እንገልፃለን" ብለዋል ሜጀር ጄኔራል ገብሬ። 

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተር የተከሰከሰው መደበኛ የወታደሮች ዝውውር መርኃ-ግብር ተሰማርቶ በነበረበት ወቅት መሆኑን የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል ያወጣው መግለጫ አትቷል። ለተባበሩት መንግሥታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል ወታደሮች #በብቸኝነት ያዋጣቸው ኢትዮጵያ 4,500 አባላት ያሉትን ኃይል አሰማርታለች።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ናዝራዊት ቻይና ውስጥ #በሞት እንድትቀጣ አልተፈረደም!"

ቻይና ውስጥ ላለፉት #ሶስት_ወራት እፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ እስር ላይ ስለምትገኘው #ናዝራዊት_አበራ በዛሬው ዕለት የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ #ነቢያት_ጌታቸው ከአለም አቀፉ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር ቆይታ አድርገው ነበር። የሰጡት መረጃምይህንን ይመስላል፦

"ቻይና ሀገር ያሉ የኛ የቆንስላ ፅ/ቤት ሰራተኞች ሶስት ግዜ እስር ቤት ሄደው አይተዋታል። የመጨረሻው ጉብኝት እንደውም ያለፈው አርብ ነበር። ላረጋግጥልህ የምችለው የሞት ፍርድ ተፈረደባት የሚባለው ውሸት መሆኑን ነው። ሂደቱ ገና ነው። የሀገሪቱ አቃቤ ህግ ገና ክሱን ያቀርባል። ከዛ በሁዋላ ነው ጉዳዩ ፍርድ ቤት ሄዶ የሚወሰነው። እስካሁን እፅ ነክ በሆነ ወንጀል ተጠርጥራ ነው ያለችው። እንደ ዜጋችን አሁን መጠየቅ የምንችለው የኮንሱላር ድጋፍ ማረግ ነው። እሱን ደሞ እያገኘን ነው። #ትክክለኛ_ፍርድ እንድታገኝ እና ጠበቃ የማግኘት መብት እንዲኖራት ክትትል ይደረግበታል። የፍርድ ደረጃ ላይ ሲደረስም clemency (ምህረት) የሚጠየቅበት ሁኔታ የተለመደ ነው። እነሱም ያሉን ጉዳዩ በቻይና ህግ የተያዘ ነው ብለውን ነው።"

ምንጭ፦ ETHIO-NEWSFLASH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Share #ሼር

ለጠቅላላ ሀኪሞች የወጣ የኮንትራት ቅጥር ፦

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በዞን ጤና መምሪያ እና በልዩ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ክፍት የስራ መደብ ላይ ተፈላጊውን ችሎታ የሚያሟሉ ሀኪሞችን በኮንትራት ቅጥር አወዳድሮ መመደብ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

👉 የስራው መደቡ መጠሪያ - ጠቅላላ ሀኪም
👉 የሙያ መስመር /ተፈላጊ ችሎታ - በጠቅላላ ህክምና በዲግሪ የተመረቀ/ች
👉 የስራ ልምድ- #ዜሮ_ዓመት
👉 ብዛት - 379 (#ሶስት_መቶ_ሰባ_ዘጠኝ )
👉 ደመወዝ - 9,056
👉 የስራ ቦታ - በእጣ ነው የሚለየው

ማሳሰቢያ ፦

1ኛ. በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በሚመደብበት በማንኛውም ዞን / ልዩ ወረዳ ሄደው ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ /የሆነች።

2ኛ. በዕጣ ከጤና ቢሮ ለዞን/ልዩ ወረዳ ሲመደቡ ዞን/ልዩ ወረዳ በሚሰጠው በማንኛውም ጤና ተቋማ /ምደባ / ቦታ ሄደው ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች።

3ኛ. በማንኛውም የመንግስት ተቋም ውስጥ ያልተቀጠረ /ያልተቀጠረች

የመመዝግቢያ ጊዜ ፦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት። (ከተሰጠው ቀን ውጭ የሚመጣ አይስተናገድም)

የመመዝገቢያ ቦታ ፡ በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ሲሆን ኦርጂናል የትምህርት እና የሙያ ፍቃድ ማስረጃ ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር መያዝ እንዳትዘነጉ።

የፈተናው ቀን : በቀጣይ ይገለፃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle መቐለ ያሉ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ለማየትና ለመጠየቅ እየተዘጋጁ ያሉ ዜጎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በቀን የሚያደርገውን በረራ ቁጥር እንዲጨምር እየጠየቁ ይገኛሉ። ሄርመን የተባለችና በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነች የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል፤ እናት እና አባቷ በመቐለ እንደሚኖሩ ገልፃ በረራ መጀመሩን በመስማቷ እጅግ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባት ገልፃለች። ትላንት…
#AddisAbaba #Mekelle

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመቐለ ያለው የቴሌኮም መሰረተ ልማት እንደተስተካከለ በየዕለቱ የሚካሄደውን በረራ እንደሚያሳድግ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በሰጡት ቃል አየር መንገዱ የአውሮፕላን ችግር እንደሌለበትና በቀን አራትም፣ አምስትም በረራ ማድረግ እንደሚችል ገልፀዋል።

አቶ መስፍን ጣሰው ፤ " አሁን የተቸገርነው መቀለ የቴሌኮም አገልግሎት ስለሌለ የስልክ ግንኙነት እንኳን ማድረግ አልቻልንም። ከእዛ ለሚመለሱት እንኳን የ boarding pass እና የ baggage process እየተደረገ ያለው አዲስ አበባ ነው። የቴሌኮም ጥገናው እየተሰራ እንደሆነ አውቃለሁ፣ ስለዚህ ይህ እንደተስተካከለ እኛም በራራውን እንጨምራለን። " ሲሉ አሳውቀዋል።

" ይህ ምናልባት በመጪው #ሶስት እና #አራት ቀናት ሊስተካከል ይችላል። " ሲሉም አክለዋል።

በሌላ በኩል ከየአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ጋር በተያያዘ 3 ሺህ የነበረው አሁን እስከ 9 ሺህ እየተሸጠ እንደሆነ ይነገራል ይህ ለምን ሆነ? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

" ዘጠኝ ሺህ የተሸጠው business class ነው " ያሉት አቶ መስፍን " የeconomy class ትኬት ቀድመው የገዙ ሶስት ሺህ ብር ገደማ ነበር፣ በአለም አቀፍ አሰራር መሰረት ትንሽ ዘግይቶ የሚገዛ ደግሞ ወደድ ይላል፣ አራት ሺህ ገደማ ገብቷል " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ለበረራ የሚጠቀምበት አውሮፕላን 138 ሰው የሚጭን ቦይንግ 737 መሆኑን ጠቁመዋል።

" ወደፊት ፍላጎቶችን እያየን ከዛም በላይ የመጫን አቅም ያላቸውን አውሮፕላኖችን መጠቀም እንችላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

#ኤልያስመሰረት

@tikvahethiopia