TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እጅግ_በጣም_አሳሳቢ

የዛሬ መጋቢት 9 ሁኔታ ፦

- 600 ከፍተኛ ክትትል እና ፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች

- በአንድ ቀን በቫይረሱ የተያዙ 2,057 ይህ 26% ሀገራቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ ነው (#እስካሁን_ከፍተኛው) በማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ (COMBAT) ወቅት እንኳን ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር አስመዝግበን አናውቅም ፤

- 10 ሕይወታቸው ያጡ ዜጎች

በዛሬው ቀን ከተመረመሩት ዉስጥ 8 ክልሎች ከፍተኛ (ከ20% በላይ) የበሽታ ስርጭት ታይቶባቸዋል ፦

1. ሲዳማ-45%
2. ድሬዳዋ-40%
3. አዲስ አበባ-26%
4. ኦሮሚያ- 31%
5. ደቡብ- 20%
6. አማራ- 20%
7. ቤንሻንጉል-29%
8. ሐረር- 23%

ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#እጅግ_በጣም_አሳሳቢ

የዛሬ የኮቪድ19 ሪፖርት ምን ይመስላል ?

- 624 ከፍተኛ ክትትል እና ፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች
- 24% ሀገራቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ
- 16 ሕይወታቸው ያጡ ዜጎች

በዛሬው ቀን ከተመረመሩት ዉስጥ 6 ክልሎች ከፍተኛ (ከ20% በላይ) የበሽታ ስርጭት ታይቶባቸዋል ፦
1. ሲዳማ-48%
3. ድሬዳዋ-22%
3. አዲስ አበባ-25%
4. ኦሮሚያ- 25%
5. ደቡብ- 21%
6. አማራ- 24%

በፀና የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እጅግ ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች ከፍተኛ የሆነ #የኦክስጅን እጥረት አጋጥሟል።

በፍጥነት የመከላከያ መንገዶች ትግበራ ወደ አስገዳጅነት እንዲገባ ካላደረግን እና ሁላችንም በሚገባ ካልተጠነቀቅን የከፋ ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል ከእነዚህ ቁጥሮች በላይ ምስክር የለም::

ሁላችንም የበሽታውን ስርጭት በመግታት የራሳችን እና የምንወዳቸው ቤተሰቦቻችን ሕይወት እናድን።

ያዕቆብ ሰማን
ጤና ሚኒስቴር
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AlertEthiopia😷 ባለፉት 24 ሰዓት 23 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። በተመሳሳይ ከተደረገው 7,423 የላብራቶሪ ምርመራ 1,949 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ትላንት 530 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። በአጠቃላይ 194,524 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,741 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 151,172 ሰዎች አገግመዋል። በአሁን…
#እጅግ_በጣም_አሳሳቢ

26% ሀገርአቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ።

ዛሬ ከተመረመሩት ዉስጥ 5 ክልሎች ከፍተኛ (ከ20% በላይ) የበሽታ ስርጭት የታየባቸው ፦

• ሲዳማ-37%
• ድሬዳዋ-26%
• አዲስ አበባ-29%
• ቤንሻንጉል ጉሙዝ - 27%
• ሐረር - 25%

በፀና የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ በመጨመሩ በአዲስ አበባ እንዲሁም በተወሰኑ የክልል ከተሞች ገጥሞ የነበረውን የኦክስጅን እጥረት በተለያዩ አማራጮች ለመፍታት እየተሞከረ እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት ዳይሬክተር ያዕቆብ ሰማን አስታውቀዋል።

አቶ ያዕቆብ ፥ ከጥቂት ቀናት በኃላ የኦክስጅን እጥረቱ ችግር ሙሉ በሙሉ ይፈታል ተብሎ እንደሚታመን ገልፀዋል።

እየተመዘገቡ ያኑት ቁጥሮች "የከፋ ጊዜ" ሊመጣ እንደሚችል የሚያሳዩ ስለሆነ ሁሉም ለራሱ እና ለቤተሰቦቹ ሲል ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

#መኖር_እየቻልን_አንሙት

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Attention😷 በአንድ ቀን 2,097 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ። ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 8,171 የላብራቶሪ ምርመራ ነው 2,097 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው። በተመሳሳይ ባለፉት 24 ሰዓት የ28 ሰዎች ህይወት አልፏል። ትላንት 1,336 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። አጠቃላይ 196,621 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህም መካከል 2,769 ሰዎች…
#እጅግ_በጣም_አሳሳቢ

- 26% ሀገራቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ
- 28 ሕይወታቸው ያጡ ዜጎች
- 769 ከፍተኛ ክትትል እና ፅኑ ህክምና የሚፈልጉ

በዛሬው ቀን ከተመረመሩት ዉስጥ 5 ክልሎች ከፍተኛ (ከ20% በላይ) የበሽታ ስርጭት ታይቶባቸዋል ፦
1. ደቡብ - 56%
3. ድሬዳዋ - 24%
3. አዲስ አበባ - 25%
4. ቤንሻንጉል ጉሙዝ - 23%
5. ሐረር - 25%

NB : ሶማሊ እና ትግራይ ዛሬ ምንም ናሙና አልመረመሩም።

ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በአዲስ አበባ ሀርመኒ ሆቴል ለዓለም ዓቀፉ የቁርዓን ውድድር ማጣሪያ ሲካሄድ ውሏል። የፊታችን እሁድ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የቁርኣን ሂፍዝ ውድድር እንደሚካሄድ ይታወቃል። በዚህ ልዩ ውድድር ላይ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የመጡ ተወዳዳሪዎች መካከል ዛሬ የማጣሪያ ውድድሩ እየተካሄደ ሲሆን ውድድሩ በዓለም ዓቀፍ ዳኞች የተመራ ነበር። በእሁዱ ውድድር የሶማሌ ክልሉ ተወላጅ…
#እጅግ_በጣም_አስቸኳይ

በነገው ዕለት የዓለምዓቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር መዝጊያ ፕሮግራም በስታድየም ይደረጋል ተብሎ የተገለጸ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁንና አንዳንድ ዶክመንቶች በጊዜ ባለማሟላታቸው እንዲሁም አዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የተቆፋፈረና ምቹ ባለመሆኑ የመዝጊያው ፕሮግራም ከስታዲየም ውጪ እንዲደረግ ተወስኗል።

ስለዚህም ህዝቡን ይቅርታ እየጠየቅን ከዚህ ጋር የተያያዙ ዝርዝር ጉዳዮችን በቀጣይ ጊዜያት የምናሳውቅ ይሆናል።

ማሳሰቢያ ፦ ከሀገሪቱ ጫፍ እስከ ጫፍ ወደ አዲስ አበባ እየመጣችሁ ያላችሁ እንግዶች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይህንን በመገንዘብ ሳትለፉ ባላችሁበት እንድትከታታሉ እንጠይቃለን።

(አዘጋጅ ፦ ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር)

የነገውን ፕሮግራም ተካፋይ ለመሆን ስትጠብቁ የነበራችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን የአዘጋጆቹን መልዕክት ያልሰሙ ካሉ #ሼር አድርጓቸው / ላኩላቸው።

@tikvahethiopia
#ትኩረት

በአማራ ክልል፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በዚህ ሰዓት የፀጥታ ችግር መኖሩን በወረዳው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።

ያለው ሁኔታ #እጅግ_በጣም ከፍተኛ የሆነ ትኩረት የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለው የፀጥታ ስጋት " ለነፍሳችን ሰግተናል " ያሉ ነዋሪዎች የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ እና ሁኔታው እንዲረጋጋ ጠይቀዋል።

ዛሬ በወረዳው ለተፈጠረው የፀጥታ ችግር ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረግን ነው።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ፤ "ሰንበቴ በአሁኑ ሰአት ጭንቅ ውስጥ ገብታለች ፤ ዱኣ ወይም ፀሎት ትፈልጋለች!! የሚመለከተው የመንግስት ባለድርሻ አካላትን ልዩ ትኩረት ትሻለች። " ሲል አንድ አጭር ፅሁፍ አሰራጭቷል።

ወረዳው ይህንን ከማለት ውጭ ስለጉዳዩ ምንም የሰጠው ዝርዝር መረጃ የለም።

በአጣዬ በኩልም ስጋት መኖሩን ቤተሰቦቻችን እየገለፁ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በአካባቢው ካሉት የቤተሰብ አባላቱ ሁኔታውን ለመከታተል ጥረት ያደርጋል።

ይህ የሀገራችን ቀጠና ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጊዜ የፀጥታ ችግር ሲከሰትበት እና የሰዎች ህይወት ሲቀጠፍበት ፣ ንብረትም ሲወድምበት እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia