TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በተመለከተ፦

ሀ. ለ13ኛው ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዝግጁ የሆኑ የቤቶች ዝርዝር በቁጥር

1. ስቱዲዮ =1,248,
2. ባለ 1 መኝታ = 18,823,
3. ባለ 2 መኝታ = 7,127,
4. ባለ 3 መኝታ = 5,455 ናቸው፡፡

በጠቅላላ የ20/80 ቤቶች ለ13ኛው ዙር ለዕጣ ዝግጁ የሆኑ 32,653 ቤቶች ናቸው

ለ. በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም እየቆጠቡ ያሉ #ተመዝጋቢዎች

1. በስቱዲዮ (ነባር ተመዝጋቢዎች) = 7,744
2. በባለ 1 መኝታ (ነባር ተመዝጋቢዎች) = 40,774
3. በባለ 2 መኝታ (ነባር ተመዝጋቢዎች) = 26,040
4. በባለ 3 መኝታ (አዲስ ተመዝጋቢዎች) =140,186

ሐ. ለ13ኛው ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልገው ዝቅተኛው የቁጠባ መጠን

1. ለስቱዲዮ (ነባር ተመዝጋቢዎች) (ቢያንስ ለተከታታይ 40 ወራት የቆጠቡ) = 151x40 = 6,040 ብር
2. ለባለ 1 መኝታ (ነባር ተመዝጋቢዎች) (ቢያንስ ለተከታታይ 40 ወራት የቆጠቡ) = 274x40 =10,960 ብር
3. ለባለ 2 መኝታ (ነባር ተመዝጋቢዎች) (ቢያንስ ለተከታታይ 40 ወራት የቆጠቡ) = 564x40 = 22,560 ብር
4. ለባለ 3 መኝታ (አዲስ ተመዝጋቢዎች) (ቢያንስ ለተከታታይ 60 ወራት የቆጠቡ) = 489x60 = 29,340 ብር

መ. ለ13ኛው ዙር የ20/80 የዕጣ ፕሮግራም ብቁ (ዝቅተኛ የቁጠባ መጠንን ያሟሉ) ሆነው ለዕጣው ተወዳዳሪ የሚሆኑ የተመዝጋቢዎች ብዛት በቁጥር

1. በስቱዲዮ (ነባር ተመዝጋቢዎች) = 4,544
2. በባለ 1 መኝታ (ነባር ተመዝጋቢዎች) = 28,557
3. በባለ 2 መኝታ (ነባር ተመዝጋቢዎች) = 19,162
4. በባለ 3 መኝታ (አዲስ ተመዝጋቢዎች) = 58,031
.............................................

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በተመለከተ፦

ሀ. ለ2ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕጣ ዝግጁ የሆኑ የቤቶች ዝርዝር በቁጥር

1. ባለ 1 መኝታ = 3,060
2. ባለ 2 መኝታ = 10,322
3. ባለ 3 መኝታ = 5,194

በጠቅላላ ለ2ኛው ዙር ለዕጣ ዝግጁ የሆኑ 18,576 የ40/60 ቤቶች ናቸው፡፡

ለ. በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም እየቆጠቡ ያሉ ተመዝጋቢዎች
1. በባለ 1 መኝታ = 11,699
2. በባለ 2 መኝታ = 57,277
3. በባለ 3 መኝታ = 56,138

በጠቅላላ 125,114 ተመዝጋቢዎች በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም እየቆጠቡ ይገኛሉ።

ሐ. ለ2ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልገው ዝቅተኛው የቁጠባ መጠን (ለሁሉም የመኝታ ዓይነት በምዝገባው ወቅት ከነበረው ጠቅላላ ዋጋ ውስጥ 40% እና ከዚያ በላይ የቆጠቡ ለዕጣው ተወዳዳሪ ይሆናሉ)

1. ለባለ 1 መኝታ = 162,645x0.4 =65,058 ብር
2. ለባለ 2 መኝታ =250,000x0.4 = 100,000 ብር
3. ለባለ 3 መኝታ = 386,400x0.4 = 154,560 ብር

መ. ለ2ኛው ዙር የ40/60 የዕጣ ፕሮግራም ብቁ (ዝቅተኛ የቁጠባ መጠንን ያሟሉ) ሆነው ለዕጣው ተወዳዳሪ የሚሆኑ የተመዝጋቢዎች ብዛት በቁጥር

1. በባለ 1 መኝታ = 5,502
2. በባለ 2 መኝታ = 25,634
3. በባለ 3 መኝታ = 26,126

በጠቅላላ 57,262 ብቁ ተመዝጋቢዎች ለ18,576 የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕጣው ተወዳዳሪ ይሆናሉ፡፡

(የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር )
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተባባሪነት ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ዛሬ ጠዋት ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት ለተፈጠረው ውጥረት መንሥኤ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በውይይቱ ላይ ሁለቱም ወገኖች ተባብረው ለሰላም ለመሥራት ተስማምተዋል። በተጨማሪም ውጥረቱን ለመቀነስ የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

Via #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአየር ኃይል በተከሰተ የምግብ #መመረዝ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ‼️

በኢትዮጵያ አየር ኃይል ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) ጠቅላይ መምርያ የትምህርት ማዕከል ምግብ ቤት በተከሰተ የምግብ መመረዝ፣ 270 ያህል ሠልጣኞች ታመው ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ፡፡

ሪፖርተር ታማኝ የዜና ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው፣ የካቲት 22 ቀን 2011 ዓ.ም. በትምህርት ማዕከሉ ምሳቸውን በመመገብ ላይ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች በሕመም በምግብ አዳራሽ ውስጥ ወድቀዋል፡፡ ከ260 በላይ የሚሆኑ ዕጩ መኮንኖች ሆራ አካባቢ በሚገኘው የአየር ኃይል ሆስፒታልና በከተማው ሆስፒታል እንደተወሰዱ የሪፖርተር ምንጮች አስረድተዋል፡፡

ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ሠልጣኞች #ሕክምና ተደርጎላቸው እንደወጡ፣ የአንድ ተማሪ ሕይወት ግን ማለፉን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

ለሠርግ ዕረፍት ወጥተው የነበሩ የአየር ኃይል የሕክምና ዳይሬክተር፣ ዕረፍታቸውን አቋርጠው የሕክምና ሥራውን ሲያተባብሩ እንደነበር ታውቋል፡፡

ሠልጣኞቹ የአውሮፕላን ጥገናና የማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ተማሪዎች እንደሆኑ የገለጹት ምንጮች፣ ሠልጣኝ አብራሪዎች በወቅቱ በምግብ ቤቱ አዳራሽ ውስጥ እንዳልነበሩ ተነግሯል፡፡

የምግብ መመረዙ በምን ምክንያት ሊከሰት እንደቻለ የፓስተር ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች ወደ ሥፍራው በማቅናት ናሙና እንደወሰዱ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ‹‹ጉዳዩ በምርመራ ላይ ነው፡፡ በባክቴሪያ የመጣው ወይስ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ወንጀል ነው የሚለው እየተጣራ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የአየር ኃይል ዋና አዛዥ አማካሪ የሆኑት ኮሎኔል ባሻ ደገፋ ዜናውን አስተባብለዋል፡፡ ‹‹የታመመም የሞተም ሰው የለንም፤›› ብለዋል፡፡

አየር ኃይል በአሁኑ ወቅት መሠረታዊ የሆነ የለውጥ ፕሮግራም በማካሄድ ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ረፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fana Live‼️ ከኢንተር ኮንቲኔታል ሆቴል የኮንዶሚኒየም እጣ አወጣጥ ስነ ስር ዓት በቀጥታ እየተላለፈ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው‼️

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

#በዕጣ ከሚተላለፉ #ቤቶች ውስጥም 32 ሺህ 653 ቤቶች የ20/80 ቤቶች ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ 18 ሺህ 576 ደግሞ የ40/60 ቤቶች ናቸው።

በዚህም መሰረት በዕጣ ከሚተላለፉ የ20/80 ፕሮግራም ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 248 ስቲዲዮ፣ 18 ሺህ 823 ባለ አንድ መኝታ፣ 7 ሺህ 127 ባለ ሁለት መኝታ እና 5 ሺህ 455 ቤቶች ደግሞ ባለ ሶስት መኝታ ናቸው ተብሏል።

በእነዚህ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ #የሚካተቱት በ1997 ዓ.ም ተመዝግበው በ2005 ዓ.ም በነባር መደብ የተመዘገቡና በ2005 ዓ.ም የአዲስ ባለ ሶስት መኝታ ተመዝጋቢ ደንበኞች ብቻ መሆኑ ነው የተገለፀው።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት በኢንተር ኮንቲኔታል ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች ይጠብቁ🔄
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ #ታከለ_ኡማ በእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት ለእጣ ከቀረቡ ቤቶች ውስጥ ቤቶቹ በተሰሩባቸው አካባቢዎች ላሉ #አርሶ_አደሮችና የአርሶ አደር ልጆች #እጣ_ሳይገቡ እንዲያገኙ የከተማ አስተዳድሩ ውሳኔ ማሳለፉን ተናግረዋል፡፡ ከተማዋ የምታካሂደው የተቀናጀ ልማት ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነትን ያጋገጠ እንዲሆን በማድረግ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ከንቲባው አመልክተዋል፡፡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ #ዣንጥራር_አባይ በእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት አገራዊ የቤት ችግርን ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት ጭምር የቤት ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በዘላቂነት የቤት ችግርን ለመፍታትም የግሉን ዘርፍ ማሳተፍ አማራጭ የሌለው ተግባር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለእጣ ከቀረቡ ቤቶች ውስጥ ቤቶቹ #በተሰሩባቸው አካባቢዎች ላሉ #አርሶ_አደሮችና የአርሶ አደር ልጆች #እጣ_ሳይገቡ እንዲያገኙ የከተማ አስተዳድሩ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ20/80 እና የ40/60 ቤቶች የእጣ ባለእድለኞች #ስም_ዝርዝር እንደደረሰን እናቀርብላችኃለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢንተር ኮንቲኔታል በተካሄደው የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር #ታከለ_ኡማ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ #ለባለእድለኞች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ልማትን በጋራ መጠቀም ተገቢ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው፣ በቤቶቹ ግንባታ ከይዞታቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ለከፈሉት #መስዕዋትነት ዋጋቸውን እንደሚያገኙም አመልክተዋል፡፡ በዚህም ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ልማት ሲባል ከመሬታቸው ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች #ያለእጣ ቤት #እንዲሰጣቸው የከተማ አስተዳደሩ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia