በኦሮሚያ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው‼️
የአዲስ አበባ መስተደድር በትናንትናው ዕለት ከ51 ሺህ በላይ የጋራ መኖርያ ቤቶችን በዕጣ ማስተላለፉን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
የተቃውሞ ሰልፎቹ በሻሸመኔ፣ በጅማ፣ በአዳማ፣ በባሌ ሮቤ፣ በጭሮ፣ በሻምቡ፣ በአሰላ፣ በአጄ፣ በአዳባ፣ በጉደር፣ በሂርና፣ በከሚሴ(ወሎ)፣ በቁሉቢና በመሳሰሉት ከተሞች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
ተቃውሞው ከመስተዳድሩ ወሰን ውጭ የነበሩና አርሶ አደሮችን በማፈናቀል በኮዬ ፈጬ፣ በቦሌ አራብሳና ቱሉ ዲምቱ በመሳሰሉ አከባቢዎች የተገነቡት የጋራ መኖርያ ቤቶች እየቀረበባቸው የነበረው ቅሬታ ተገቢው ምላሽ ሳይሰጥበት በዕጣ ለማስተላለፍ መወሰኑ እንደሆነ ታውቋል።
መስተዳድሩ የተወሰኑ የጋራ መኖርያ ቤቶችን ያለዕጣ ለተፈናቃዮች እና ቤተሰቦቻቸው ማስተላለፉን ቢገልፅም ሕገ መንግሥታዊው የወሰን ጉዳይ እልባት ባላገኘበት ሁኔታ በድንገት መፈጸሙ የሕዝቡን ቁጣ ቀስቅሷል።
በተለይ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አርሶ አደሮቹ በግፍ በተፈናቀሉበት ወቅትም ሆነ አሁን በሁነቱ ላይ እንደውጭ ተመልካች ዝምታን መምረጡ ብዙዎችን ያነጋገረ ጉዳይ ሆኗል። አስቸኳይ የመፍትሔ እርምጃ ካልተወሰደም ሁኔታው ተባብሶ ወደ አደገኛ አቅጣጫ ሊሄድ እንደሚችል ሁኔታዎች እያመለከቱ ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በተከሰው ሁኔታና በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሊሰጥ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
Via ጉለሌ ፖስት
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የሂውማን ራይትስ ዋች የምስራቅ አፍሪካ ተመራማሪ ፈሊክስ ሆርን ጠ/ሚር አብይ በክልሉ እያበረከቱ ያለውን ሚና አድንቆ "በሀገር ውስጥ ግን በአማራ እና ትግራይ ክልሎች እንዲሁም ሌሎች ቦታዎች ላይ ተመሳሳይ (የማስታረቅ) ሚና አለመጫወታቸው አሳሳቢ ነው" ብሎ የትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል።
Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መጋቢት 29 በሚጀመረው የህዝብና ቤት ቆጠራ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችና #የተፈናቀሉ ዜጎችን ያማከለ ቆጠራ እንደሚካሄድ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችንና የተፈናቀሉ #ዜጎችን ጉዳይ በተመለከተ እያንዳንዱ ክልል ከለውጡ በኋላ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ ከሁለት ወራት በፊት ስብሰባ ተደርጎ መገምገሙን በኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነትና መረጃ አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ሳፊ ገመዲ ገልጸዋል፡፡ በዚህም ሁሉም ክልል የየራሱን ሪፖርት ካቀረበ በኋላ፣ የቆጠራ ኮሚሽኑ መሰረታዊ ነጥቦች ላይ በሰፊው ውይይት አድርጎ ውሳኔ ማስተላለፉን ኃላፊው አመልክተዋል፡፡ በዚህም ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የህዝብና ቤት ቆጠራውን ለማካሄድ እንደ አማራጭ ክልሎች በአስቸካይ ተነጋግረው ችግሮችን በፈቱባቸው አካባቢዎች የቆጠራ ካርታ መሰራቱንም ገልጸዋል፡፡ አቶ ሳፊ እንደሚሉት ክልሎች ችግሩን መፍታት ባልቻሉባቸውና የቆጠራ ካርታ ባልተሰራባቸው አካባቢዎች ‘’ልዩ የቆጠራ ቦታ’’ ‘’Special Enumeration area’’ ተብሎ ተይዞ ቆጠራው ይካሄዳል።
Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል በ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የማስፋፊያ ግንባታ እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል።
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 9 ፐርሰንቱ የኢትዮጵያ ህዝብ እርዳታ ፈላጊ ሆኗል ተባለ። መንግስት ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው 8.8 ሚልዮን ኢትዮጵያውያን የሰብአዊ #እርዳታ ይሻሉ ብሏል። ከፍተኛው እርዳታ ፈላጊ በኦሮሚያ ክልል (3.88 ሚልዮን) ሲሆን የሶማሌ ክልል 1.8 ሚልዮን ተረጂዎች አሉበት። በአማራ ክልል ደሞ ወደ 980,000 እርዳታ ፈላጊዎች እንዳሉ ገልጿል። ለዚህም መንግስት የ1.3 ቢልዮን ዶላር ገንዘብ #ያስፈልገኛል ብሎ ለእርዳታ ድርጅቶች እና ለጋሽ ሀገራት ጥሪ አቅርቧል። ከእርዳታ ፈላጊዎች ውስጥ 3.1 ሚልዮኑ ተፈናቃዮች ሲሆኑ ይህም በብሄር ተኮር ግጭት የተሰደዱ ናቸው ተብሏል።
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት(https://www.facebook.com/Elias-Meseret-517243322140049/)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት(https://www.facebook.com/Elias-Meseret-517243322140049/)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
❤1
በኦሮሚያ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ‼️
(20/80ና 40/60)
የ20/80ና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ይፋ ከመሆን ጋር ተያይዞ ቦታው የኦሮሚያ ነው በሚል ከ10 በላይ በሚሆኑ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞዎች ተቀስቅሰዋል።
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ የተገነቡባቸው አካባቢዎች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሆነው የአዲስ አበባ መስተዳድር ውሳኔ የሚያሳልፈው እንዴት ነው፤ ለተፈናቃዮቹ አርሶ አደሮች የተሰጠው ካሳ እዚህ ግባ የማይባል ነው፤ የተቀናጀው ማስተር ፕላን ቅጥያ ነው የሚሉ ሀሳቦችን ተቃዋሚዎቹ አንስተዋል።
#በምስራቅ_ኦሮሚያ ጪሮ ከተማ ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ ሰልፈኛ " በዚህ ተቃውሞ ላይ ዋነኛ መልዕክታችን በአዲስ አበባ አካባቢ ያሉት መሬቶች ለኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ሊመለስ ይገባል" የሚል ነው። ተቃዋሚው ጨምሮም ለብዙዎች ሞት ምክንያት የሆነው አወዛጋቢው የተቀናጀ ማስተር ፕላን ሊመለስ አይገባም ብሏል።
ተቃውሞዎቹ በሻሸመኔ፣ ጪሮ፣ ጂማ፣ አሰላ፣ አዳማና ሂርና ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተስፋፉ ሲሆን በሻሸመኔ አካባቢ የሚገኙ ሰልፈኞች "ኦዲፒ ያልነውን ረስታችሁታል፤ መሬታችን የደም ስራችን ነው" የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ነበር።
በትናንትናው ዕለት 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል የዕጣ ማውጫ ስነ ስርአት ለተጠቃሚዎች የተላለፈ ሲሆን፤ ከአካካቢው ለተነሱ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ያለ እጣ እንዲሰጣቸው በከተማው አስተዳደር ካቢኔና በቤቶች አስተዳደር ውሳኔ መሰረት ያለ ዕጣ እንዲተላለፍ መወሰኑን ምክትል ከንቲባ #ታከለ_ኡማ በትናንትናው ዕለት ገልፀዋል።
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ሲገነቡ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ያልደበቁት ምክትል ከንቲባው "በተለይም የእርሻ መሬታቸውን ለነዚህ ተግባራት ሲሉ የለቀቁና ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ቀውስ የተዳረጉ የአርሶ አደር ቤተሰቦችና ልጆቻቸው ህመማችሁ የእኛ መሆኑን እንድታውቁ" የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።
ምክትል ከንቲባው ይህንን ቢሉም ኦሮሚያ ውስጥ ተቀስቅሶ ለረጅም ጊዜ ለዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለትና ከ2006 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ቅጥያ ነው የሚሉ ትችቶችም እየተሰሙ ነው።
ምንም እንኳን የተቀናጀው ማስተር ፕላን ከፍተኛ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ውድቅ ቢደረግም የቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባና ኦህዴድ ሊቀ መንበር አቶ ኩማ ደመቅሳ ጉዳዩ ከመፈናቀል ጋር አብሮ ስለመጣ እንጂ "ተራማጅ አስተሳሰብ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ማስተር ፕላኑ አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል" ብለው ለቢቢሲ መናገራቸው የሚታወስ ነው።
ምንም እንኳን ከመንግሥት በኩል ምንም አይነት መግለጫ ባይሰጥም በቅርቡ ከውጭ ሀገር የተመለሰው የተባበሩት ኦነግ በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ያለውን ድንበር መወሰን ያለበት የኦሮሚያ ክልል ነው የሚል ነው።
በ13ኛው ዙር የ20/80 ቤቶች 32ሺ 653 ቤቶችና በ2ኛ ዙር የ40/60 ቤቶች ለተጠቃሚዎች የሚተላለፉ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ 1ሺ 248 ስቱዲዮ፣ 18ሺ 823 ባለ አንድ መኝታ፣ 7ሺ 127 ባለሁለት መኝታ እና 5ሺ455 ደግሞ ባለ ሶስት መኝታ መሆናቸው ተገልጿል።
በ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የሚካተቱትም በ1997 ተመዝግበው በ2005 ዓ.ም በነባር መደብ የተመዘገቡና በ2005 ዓ.ም የአዲስ ባለ ሶስት መኝታ ተመዝጋቢ ደንበኞች መሆኑ ተገልጿል።
Via BBC አማርኛ

#update አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ አካባቢ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል የስራ ባልደረባውና #ባለቤቱ የሆነችውን የፖሊስ አባል ዛሬ ረፋድ ላይ በጥይት #መግደሉ ተሰማ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ምክትል ሃላፊ ኮማንደር #ተስፋዬ_ምትኩ ለኢዜአ እንደገለጹት ተጠርጣሪው የፖሊስ አባል የሆነችውን የትዳር አጋሩን ስድስት ኪሎ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ መግደሉን አረጋግጠዋል። መንስኤው ገና #በመጣራት ላይ ቢሆንም ግድያው የተፈፀመው በመካከላቸው በተፈጠረው ጊዜያዊ አለመግባባት መሆኑም ታውቋል።
Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethioia
Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethioia