TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች‼️

"የፀጥታ እና የደህንነት ስጋት እንዳይኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል።"
*
*
*
ነባርና አዲስ ተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንና የተማሪ ቤተሰቦችና ተማሪዎች #ከጸጥታና #ደህንነት ሥጋት ነጻ ለማድረግ #ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

የተማሪችን አቀባበል አስመልክቶ በዩኒቨርሲቲው በተካሄደ የምክክር መድረክ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲጎለብት የድርሻቸውን
ሚና እንደሚወጡ ባለድርሻ አካላት ጠቁመዋል፡፡
*
*
*
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት አስራ አንድ አመታት ሰላም የሰፈነበት የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ በሃገር አቀፍ ደረጃ ሠላማዊ ዩኒቨርሲቲ መባሉ ይታወሳል፡፡ በዚህም በበርካታ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ዘንድ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ እየሆነ መጥቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2020 ከሃገሪቱ ምርጥ አምስት እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን የሚያስችለውን ተግባር በማከናወንና የተማሪዎች ቅበላ አቅሙን በማሳደግ የትምህርት መርሃግብሮቹን መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሻሻል ፍላጎትን መሰረት አድርጎ እየሰራም ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የ2011 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላን አስመልክቶ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት ተጠሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና የሚመለከታቸው አካላትን በማሳተፍ ምክክር በማድረግ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በምክክር መድረኩ ተገኝተው መግለጫ የሰጡት የዩኒቨርቲው አካዳሚክ ጉዳዩች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ወንድሙ ወልዴ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን በማስፈንና የተማሪ ቅበላ አቅሙን 29ሺህ በማድረስ በትጋት እየሰራ መቆየቱን ነው የተናገሩት፡፡

ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስፈን እንዲቻል ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በቅርበት ሲሰራ መቆየቱን የተናገሩት ም/ፕሬዝዳንቱ፣ ከወቅታዊ ሃገራዊ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ስጋት ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘርፈ ብዙ ስራ ከሚመለከታቸው ባለከድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱንም አውስተዋል፡፡

ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲሰፍን ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ መንግስትና ተቋሙ ልዩ ክትትል የሚያደርግና የተማሪ ቤተሰቦችና ተማሪዎች ከጸጥታና ከደህንነት ስጋት ነጻ ለማድረግ የሚያስችል ስራ መሰራቱንም ም/ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ እንዲቻል አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ በበቂ ሁኔታ መደረጉን የተናገሩት ዶ/ር ወንድሙ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በተለይም የጸጥታ አስከባሪዎች፣በጎ አድራጎት ማህበራት፣የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙላት ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተናገዱ ሂደት በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመድረኩ በመሳተፍ መግለጫ ከሰጡት መካከል የሃገር ሽማግሌዎችን በመወከል አቶ ሚልኪያስ ኦሎሎ እና የሃይማኖት ተቋማትን በመወከል አቶ ሰይፉ ለታ እንደገለጹት ሠላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተናገዱ ሂደት ሁሉም ባለድርሻ በባለቤትነት ሊሳተፍ ይገባል ብለዋል፡፡

ወላይታና አካባቢው እንግዳ ተቀባይ መሆኑንና አሁን ላይ ከተማሪ ቅበላ ጋር በተያያዘ አንዳች የሚያሰጋ የጸጥታና የደህንነት ስጋት እንደሌለ ጭምር ተሳታፊቹ አውስተዋል፡፡

የወላይታ ሶዶ ከተማ ፍትህና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አንዱዓለም አዳነ አካባቢውን ከደህንነትና ከጸጥታ ስጋት ነጻ በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማጠናከር ከአቀባበል ጀምሮ በዘላቂነት ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችል ተግባር ዘርፉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

በዩቨርሲቲው የሰላም ፎረም ጽ/ቤት ፕሬዝዳንት ተማሪ በረከት አፈወርቅ ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ አቀባበል እንዲኖር ለማስቻል በተማሪዎች አደረጃጀት ዘርፍ የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንና አዳዲስ ተማሪዎችን ከዩኒቨርሲቲውና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ለማላመድ መዘጋጀታቸውን ተናግሯል፡፡

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የህግ ት/ቤት ዲን እና የወላይታ በጎፈቃደኞች ማህበር አባል መምህር ተከተል ለቤና አዲስና ነባር ተማሪዎችን የመቀበሉን ተግባር ከማሳካት ረገድ ማህበሩና የማህበሩ አባላት ጉልህ ተሳትፎ እንደሚኖራቸው ጠቁሟል፡፡

ተማሪዎችን በበጎ ፈቃድ ለማገልገል የማህበሩ አባላት ከምንጊዜውም በበለጠ ዝግጅት ማድረጋቸውንና አቀባበሉንም ደማቅ ለማድረግ
ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርበው እየሰሩ መሆናቸውን መምህር ተከተል አውስቷል፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2011 የትምህርት ዘመን ከ 15 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተናግድ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 3 ሺህ 4 መቶ ያህሉ አዲስ ገቢ ተማሪዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

የመደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 10 እስከ 14 ባሉት ጊዜያት ውስጥ እንደሚካሄድ የዩኒቨርሲቲው ሬጅስተራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት መግለጹም ይታወቃል፡፡

ምንጭ፦ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia