TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19

ኬኒያ ከሰሜን ጣሊያን ወደ ሃገሯ የሚደረጉ በረራዎችን አገደች፡፡ የሃገሪቷ ባለስልጣናት ዛሬ እንዳስታወቁት በጣሊያን በተለይም ሰሜናዊ የሃገሪቷ ክፍል ቬሮና እና ሚላን እየጨመረ በመጣው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት በረራዎችን አግዳለች፡፡

ውሳኔው የተላለፈው በኬኒያ የጣሊያን ኤምባሲ የሰጠውን የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ኬኒያ ወረርሽኙ አሳሳቢ ወደሆነባቸው ሃገራት የምታደርገውን በረራ ከማቋረጥ በተጨማሪ ከጣሊያን፣ደቡብ ኮሪያና ኢራን ወደ ሃገሯ የሚገቡ ሰዎችን ለ14 ቀናት በለይቶ ማከሚያ ክፍል ውስጥ እንዲቆዩ እያደረገች መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

#ኢትዮኤፍኤም #አባይነሽሽባባው
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia