TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የሆነው B-737-800 በበረራ ቁጥር ET338 የተመዘገበው አውሮፕላኑ ዛሬ ማለዳ በኡጋንዳ ሊያርፍ ሲል ከማኮብኮቢያው #ተንሸራቶ የመውጣት #ችግር እንዳጋጠመው አስታወቀ፡፡

በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ኡጋንዳ የበረረው አውሮፕላኑ በኢንቴቤ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ሲሞክር ከማኮብኮቢያ ሜዳው መስመር በመውጣቱ ችግሩ እንዳጋጠመው አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በአውሮፕላኑ ውስጥ በነበሩ መንገደኞችና የበረራ ሰራተኞች ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንና በሰላም ወደ መንገደኞች ማቆያ መወሰዳቸውንም አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

በአጋጠመው የመንሸራተት ችግር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰበትም መግለጫው አመልክቷል፡፡

በችግሩ ምክንያት መስተጓጎል የተፈጠረባቸውን ደንበኞቹን አየር መንገዱ ይቅርታ ጠይቋል፡፡ ቀጣይ በረራ ላላቸው ደንበኞቹም የማመቻቸት ስራ እንደሚሰራ አመልክቷል፡፡

የአደጋውን ምክንያት ለማወቅ በምርመራ ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia