TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሺርካ ✦ " 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ✦ " ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር እናቶች ይገኙበታል " - ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ (ለቪኦኤ) ✦ " ጥቃቱን ያደረሰው አሸባሪው ሸኔ ነው " - የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን (ለቪኦኤ) ✦ " እኛ…
#Update

ቤተክርስቲያኗ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በጥብቅ እንደምታወግዝና የጸጥታ ተቋማትም ጥቃት እንዲከላለሉ ጥሪ አቀረበች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ፦
- በሶሌ ሚካኤል፣
- በዲገሎ ማርያም፣
- በሮቤ እንደቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት 36 ኦርቶዶክሳዊያን በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጿል።

በዚሁ ጥቃት በሶሌ ዲገሉ እና ጢጆ ለቡ በተባሉ ቀበሌዎች 28 ኦርቶዶክሳዊያን ከየቤታቸው #ተለቅመው መገደላቸውን ፤ ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ ሴቶችና 21ዱ ወንዶች መሆናቸው መታወቁን አመልክቷል።

በዚህ ጥቃትም እድሜያቸው ከሰባ ዓመት አዛውንት እስከ ሃያ ስምንት ቀን ጨቅላ ሕጻናት እንደሚገኙበት ገልጿል።

#በዛሬው_ዕለት ደግሞ በዲገሉ ማርያም ቤተክርስቲያን 5 ኦርቶዶክሳዊያን መገደላቸውንና የሦስት ኦርቶዶክሳውያን ቤት መቃጠሉን አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም ቤተክርስቲያን በዓለ ማርያምን አክብረው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ 3 ኦርቶዶክሳዊያን ጨለማን ተገን ባደረጉ ነፍሰ ገዳዮች መገደላቸውን ፅ/ቤቱ አስታውሷል።

የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ በሚፈጸመው የኦርቶዶክሳዊያን ጥቃት ዙሪያ በጋራ እየሠሩ እንደሚገኙ የገለፀው ፅ/ቤቱ  " በዚህ ዐይነት የጥቃት ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አንዳንድ አካላት ላይ በመንግሥት በኩል የማያዳግም #ርምጃ_እንደተወሰደባቸው ሀገረ ስብከቱ በላከው ሪፖርት ማረጋገጡን አመልክቷል።

ይህ ዐይነት ሃይማኖት ተኮር ጥቃት በምእመናን ላይ መድረሱ አግባብነት የሌለውና እምነትን በነጻነት የማራመድ መንግስታዊ መብትን የሚጥስ ነው ያለው ፅ/ቤቱ ፤ መሰል ሕገ ወጥ ጥቃትን ለመከላከልና ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት መብቶቻቸውን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ማስከበር እንዲችሉ  ያቋቋሙት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ድርጊቱን በማውገዝ ችግሩ ከመሠረቱ እንዲፈታ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር መፍትሔ መፈለግ ሲገባው በዝምታ በማለፉ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ቅሬታ እንደተሰማት ገልጿል።

" ኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠረ ግድያ እንዲቆምና የወንጀሉ ፈጻሚዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ በሀገረ ስብከቱ ጥረት እየተደረገ ነው " ያለው ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመሆን ፅ/ቤቱም ጉዳዩን የሚከታተለው መሆኑን አሳውቋል።

በሌሎች ስፍራዎች የሚያጋጥሙ ተመሳሳይ ጥቃቶችን በእንጭጩ ለመቅጨትና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ ማበጀት ይቻል ዘንድ አህጉረ ስብከት ችግሮች በሚያጋጥሙ ወቅት በፍጥነት በማሳወቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopia