TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል⬇️

በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት ከመደገፍና ከማሳደግ ውጪ ሌላ #አማራጭ እንደሌለ የደኢህዴን ሊቀ መንበር በመሆን በድጋሚ የተመረጡት ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል ገለፁ።

ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል 10ኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ድርጅታዊ ጉባዔ #መጠናቀቅን ተከትሎ ለጉባኤተኛው የማጠቃለያ መልእክት አስተላልፈዋል።

ወይዘሮ ሙፈሪያት በማጠቃለያ ንግግራቸው፥ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በለውጥ ሂደት ላይ መሆኗን ገልፀው፤ የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና ጉባዔተኛው ለውጡ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መስራት አንዳለባቸው ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ ለውጥ #ለማደናቀፍ ሌት ተቀን የሚሰሩ ሀይሎች እንዳሉ ሊቀመንበሯ ገልፀዋል።

እነዚህ ሀይሎች 10ኛው የደኢህዴን ጉባዔ እንዳይሳካም ሲንቀሳቀሱ ነበር ያሉት ወይዘሮ ሙፈሪያት፤ ከሀዋሳ ውጪ በህዝቦች መካከል #ግጭት ለመፍጠር ገንዘብ ተመድቦላቸው #ሲንቀሳቀሱ እንደነበረ ከክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ጋር በተሰራ ስራ ለማወቅ መቻሉን አንስተዋል።

የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና ጉባዔተኛው ይህንን በመገንዘብ እነዚህን የጥፋት ሀይሎች በንቃት መጠበቅና ማጋለጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ የለውጥ ሂደት ከመደገፍና ካማሳደግ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም ያሉት ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት፥ ከዚህ ውጨ ያለው አማራጭ #የጥፋት አማራጭ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ስለዚህ የለውጥ ጉዞውን በማሳከት ሂደት የደኢህዴን አባላት፣ አመራሮች እና የጉባኤተኛው ሚና አጅግ የላቀ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ከነገ ጀምሮ #በሀዋሳ ከተማ የሚካሄደው 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በማድረግ እንዲሁም የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ርብርብ መቀጠል ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።

በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የደኢህዴን ጉባዔተኞች ልክ በደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ያደረጉትን የነቃ ተሳትፎ፣ ዴሞክራሲያዊ ሂደትና ሰላማዊ ሁኔታን እንዲያስቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት አክለውም፥ 10ኛው የደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ በዚህ መልኩ የተሳካ ሆኖ በመጠናቀቁም እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ብለዋል።

ጉባዔው የተሳካ እንዲሆን የሀዋሳ ከተማ እና የሲዳማ ዞን እንዲሁም የልግ ባለሀብቶች ላደረጉልት አቀባበል እንዲሁም የኢህአዴግ ጉባዔን ለማስተናገድ እያደረጉ ላለው ዝግጅት ለአመራሩ እና ለህዝቦች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️የህዝብ የወካዮች ምክረ ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል የስራ መልቀቂያ አቀረቡ። ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል መልቀቂያቸውን በዛሬው እለት እየተካሄደ ባለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው ያቀረቡት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር በሚዘጋጀው የሴቶች ሰላም ኮንፍረንስና ጀግኒት ፕሮግራም ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ የሰላም ሚኒስትሯ #ሙፈሪያት_ካሚል፣ ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው ይገኛሉ ተብሏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሰላም ሚኒስቴር⬆️

የሰላም ሚኒስትሯ ክብርት #ሙፈሪያት_ካሚል የተጠሪ ተቋማት አመራሮችን በቢሯቸው አግኝተው አነጋገሩ።

ሚኒስትሯ የሰላም ሚኒስቴር ስምንቱ ተጠሪ ተቋማት አመራሮችን በትናንትናው እለት አግኝተው አነጋግረዋል፡፡

ተቋማቱ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ይወጡ ዘንድ ሰባት ስትራቴጂክ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ስራዉ የተጀመረ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

እነዚህም እቅድ፣ የሰው ኃይልና መዋቅር፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን፣ ሞደርናይዜሽንና አይቲ፣ የሰላምና ህግ ማስከበር፣ የህግ ማእቀፍ እና የሪሶርስ ሞቢላይዜሽንና ፋይናንስ ጉዳዮችን ወጥነት ባለው መንገድ ዘመኑ በሚጠይቀው አሰራር እንዲቃኝ ለማድረግ የታሰበ ነው፡፡

ስትራቴጂክ ኮሚቴዎቹ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጥናት አድርገውና ተቋማቱ ያሉበትን ሁኔታ ተንትነው እንዲያቀርቡ እንደሚጠበቅም ታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ በአገር ውስጥና በቀጠናው የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃት ይወጣ ዘንድ ተቋማቱ ያላቸውን አሰራር ከመሰረቱ አጥንቶ
ለችግሮቻቸው መፍትሔ መስጠትና ዘመን ተሸጋሪ የሆኑ አሰራሮችን መተግበር ግዴታ እንደሆነም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የሰላም ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት አብዛኞቹ የሰው ኃይላቸው ገበያው ከሚያቀርበው የሰው ኃይል ላይ ተጨማሪ ብቃትና እሴት ማከልን የሚጠይቅ መሆኑ የተነሳ ሲሆን የአቅም ግንባታና ሞደርናይዜሽን ስራው ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ተነስቷል፡፡

አብዛኞቹ ተጠሪ ተቋማት መዋራቸው ብዙ ጉድለት ያለበትና መሻሻል የሚጠይቅ መሆኑ፣ አንዳንዶቹም የተቋቋሙበትን አዋጅ ወደ መመሪያና ሊያሰሩ ወደሚችሉ የአሰራር ማእቀፎች ያለቀየሩ፣ የዘመነና ግልጽ አሰራር ያልተዘረጋላቸው እንደሚበዙ የተነሳ ሲሆን ትኩረት ተደርጎ
ማስተካከል እንደሚገባም አመራሮቹ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በሰላም ዙሪያ ማኅበረሰቡ የድርሻውን የሚወጣበት (Mobilization Strategy) እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ላይ ቀርቧል፡፡

የሰላምና ደኅንነት ዘርፉ ነገን አሻግሮ የሚያሳይ ዘመኑ የደረሰበትን አሰራር የሚከተል የ10 ዓመት የእቅድ ፍኖተ ካርታ እንደሚያስፈልገውና ይህንን ለማዘጋጀትም ሁሉም ተቋማት እንዲረባረቡ ክብርት ሚኒስትሯ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ሰላም የሁሉም ህዝብና አገራችን ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ተቋማት ድምር ውጤት መሆኑ ታውቆ ሁሉም ለሰላሙ መረባረብ አንዳለበትም ሚኒስትሯ አክለው ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ EPRDF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ🔝

ለዘመናት በአንድነትና በፍቅር የቆዩ በወላይታና ሲዳማ ብሔረሰቦች መካከል ተከስተው የነበረውን አለመግባባትን በማስወገድ በፍቅር፣ በይቅርታና በዕርቅ አንድነታቸውን ዳግም እንዲቀጥሉ የሚያስችል #የዕርቀ_ሰላም_ኮንፈረንስ በወላይታ ሶዶ ተካሂዷል፡፡

ኮንፈረንሱ ከቀናት በፊት በሲዳማ ዞን የተጀመረ ሲሆን በተቀመጠለት መርሃ ግብሩ መሠረት በወላይታ ሶዶም ከሁለቱም ብሔረሰብ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተደርጓል፡፡

የወላይታ ዞን ተጠባባቂ አስተዳደር አቶ #ዳጋቶ_ኩምቤ በኮንፈራንሱ መክፈቻ እንደተናገሩት በወላይታና ሲዳማ ብሔረሰብ መካከል ያለው አንድነት ከብረት የተጠናከረ ነው፤ በመሆኑም ዛሬ በሚናደርገው መድረክ አንድነታቸውን እናስቀጥላለን እንጅ አንፈጥርም ብለዋል፡፡ ስለሆነም ተከስተው የነበረውን አለመግባባትን በማስወገድ፤ ያለፈውን በመተው ወደፊት በመጓዝ ሁላችንም በሁሉም ዘርፍ አስፈላጊ ለሆነው ሠላም ዘብ መቆም ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ሚሊዮን_ማትዎስ በኮንፈረንሱ ተገኝተው እንደተናገሩት ሁለቱም ብሔረሰቦች ሠላም ፈላጊ ናቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የህዛባችን ሠላም የሚያደፈርሱ የትኛውም ኃይል ለሠላም ጤንቅ ናቸውና ፈልፍለን እያወጣን ለሁለቱም ህዝቦች ጋራ ተጠቃሚነት፣ ለሠላምና ለዴሞክራሲ መስፈን እንሠራለን ብለዋል፡፡

የኢፌዴሪ ሠላም ሚኒስተር ወ/ሮ #ሙፈሪያት_ካሚል እንደተናገሩት ስለ ሠላም የሁለቱም ህዘቦችና ሽማግሌዎች ያዉቃሉ፤ ጥበብ ጥበበኞች ዘንድ ትገኛለች፤ ዕዉቀትም በአስተማር ዘንድ፡፡ በመሆኑም ዛሬ በሁለቱ ህዝቦች ሠላም ፍላጎት መሠረት የዕርቅ ማዕድ ተቋዳሽ ሆነናል፡፡ ለሁላችንም እንኳን ደስ አለን ብለው የወላይታና ሲዳማ አንድነት አይበጠስም፣ አይሰበርም ይልቁንስ ሊበጥስ የሚጥር ኃይል ይበጠሳል እንጅ በማለት አንድነት ይበልጥ ይጠናከራል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ ገልለተኛ አካል የሆነ የዕርቅ ሽማግሌም ከሐምሌ 23/2010 ዓ.ም ጀምረው የተሠራውን የዕርቅ ሂደቱንና ከሁለቱም ህዝቦች በኩል የተነሱና በጋራ መስማማት የተዳረሱ ጉዳዮችን በሪፖርት መልክ አቅርበዋል፡፡ በተነሱ ሀሳቦችም ሁለቱም በኩል የተገኑ ሽማግሌዎች ይቀር መባባላቸውን ዕርቅና ፍቅር እናውርድ ብለው በመስማማታቸው መሠረት ዕርቁ ልፈፀም መቻሉንም አስረድተዋል፡፡

ሽማግሌዎችም ከሁሉ በላይ ከጌታ ጋር ያለንን አንድነታችን ስናጣክር ሌላው ሁሉ ይሆናል የመንግስት አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ወደ ፈጣር እንቅርብ ፣ ያለፈውን እንተው ወደ ፊት እንጓዝ በማለት መክረዋል፡፡

በመድረኩም ከሁሉም ቤተ ክርሲቲያን የተገኙ መሪዎችም የፀሎትና ቃል ስብከት ፕሮግራም አድርገዋል ይህም የወላይታና ሲዳማ የጥንት መሠረቱ ወንጌል ነው ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻ ከሁለቱም ብሔረሰብ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን የሰጡት ላለፈው ይቅር ተባብለዋል፡፡ በመሆኑ የባህላዊ ዕርቅ ሥርዓትም ተደርጓል፡፡

ምንጭ፦ የወላይታ ሶዶ ከተማ ባ/ቱ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መገናኛ ብዙሃን  ከጥላቻና መለያየት ይልቅ በኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ የሰላም ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ። “ሚዲያ ለሰላም” በሚል አገር አቀፍ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አካላት የፓናል ውይይት ትላንት ተካሂዷል። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ስራቸውን በትኩረት መስራት እንዳለባቸው የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል አሳስበዋል። መገናኛ ብዙሃን በህዝቦች መካከል #ግጭቶችን ከመፍጠርና ከማራራቅ ይልቅ አንድነትና መተባበርን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ህዝብ እንደ ህዝብ #ሊጣላ አይችልም ከፍቅር ውጪ የሚያውቀው አጀንዳ የለውም” የኢህዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበር እና የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰላም ሚኒስቴር‼️

ከ1 ሚሊየን በላይ #ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያ ቀያቸው መመለሳቸውን የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል የተቋማቸውን የ6 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካች ምክር ቤት ለውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ አቅርበዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትሯ በሪፖርታቸው ከህብረተሰቡ ጋር በተቀናጀ ተግባር 1 ሚሊየን 20 ሺህ ያህል ዜጎችን ወደ ቀያቸው መመለስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ቀሪ ተፈናቃዮችን በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ሙሉ በሙሉ የማቋቋም ስራ እንደሚያከናውንም ተናግረዋል፡፡

በጋምቤላ፣ ደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች በተመረጡ 12 ወረዳዎች ግጭቶች ከመከሰታቸወው በፊት የግጭት መንስኤዎችን የመለየትና ቀድሞ መከላከል ስራ መጀመሩንም ጠቁመዋል፡፡

በተለያዩ ግጭቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች እለታዊ እርዳታና ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችሉ ስራዎች ባለፉት 6 ወራት መሰራታቸውንም አንስተዋል፡፡

ለሰላም ግንባታ መሰረት መጣሉን የተናገሩት ሚኒስትሯ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት የግጭት መንስኤዎችን ለመለየት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ከ900 በላይ በግጭት ወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ክትትል እየተደረገ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፥ ክልሎች በወንጀሉ በዋናነት በመሳተፍ ለተጠረጠሩ ግለሰቦች ሽፋን ከመስጠት ይልቅ አሳልፈው ለህግ እንዲሰጡም ጠይቀዋል።

ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው የተዘረፉ ንብረቶችን ለማስመለስ እየተሰራ ሲሆን÷ በቃጠሎና ሌሎች ምክንያቶች የወደሙ ንብረቶችን አቅም በፈቀደ መጠን ለመገንባት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለማስቆም ምንጩን የማጥራት ስራ መጀመሩን ጠቅሰው፥ ህገ ወጥ የገንዘብና የሰዎች ዝውውርም ከሌሎች #የወንጀል ድርጊቶች ጋር ተመጋጋቢ ስለሆነ÷ ወደ ፊት በትኩረት ከሚሰራባቸው ነጥቦች መካከል መሆኑንም ጠቅሰዋል።

via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia