TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#udate ሳምንታዊ የመንግስት መግለጫ⬇️

በኢትዮጵያ #የህግ የበላይነትን ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ።

የአገሪቷን ሰላም፣ ልማት እና ዴሞክራሲ ለማረጋገጥ የህግ የበላይነት መከበር እንዳለበት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው ሳምንታዊ የመንግስት አቋም መግለጫው አመልክቷል።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ ለህዝቦቿ ተስፋ ሰጪ ከመሆኑ በላይ ከአገር አልፎ ለአጎራባች የአፍሪካ አገሮች ጭምር ተምሳሌት መሆኑን የታወቁ የዓለም ፖለቲካ ተንታኞችና ተቋማት እየመሰከሩለት መሆኑን ጠቅሷል።

ይሁን እንጂ ለውጡን የማይደግፉ ቡድኖች አንዳንድ አደናቃፊ ተግባራትን ሲፈፅሙ እንደሚስተዋል አመልክቷል።

እነዚህ አካላት ከሰሞኑ በቡራዩ እና በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ባስነሱት ግጭት የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ “የዜጎች ጥሪትም ወድሟል” ሲል አመልክቷል።

“የንፁሃን ዜጎችን ደም ማፍሰስ፣ አካል ማጉደል እና ለዓመታት ለፍተውና ደክመው ያፈሩትን ሃብት በመዝረፍና በማውደም፤ ሁሉም የሚረባረብለትን የለውጥ ጉዞ ለማጠልሸት መስራት ለማንም ትርፍ አያስገኝም” በማለትም አስገንዝቧል።

በመሆኑም በደረሰው ጉዳት ህዝብ እና መንግስት አዝነዋል ያለው የመንግስት መግለጫ “ድርጊቱ የየትኛውንም ብሄር የማይወክል እና ክስተቱ ለውጡን የሚያፋጥን እንጂ ሊያደበዝዝ አይችልም” ብሏል።

በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ማሸነፍና ሥልጣን መያዝ የሚቻለው የተሻለ ሃሳብ በማቅረብ ተወዳድሮ በማሸነፍ እንጂ #በአመጽና በኃይል ሊሆን እንደማይችልም በመግለጫው ተመልክቷል።

የህግ የበላይነት ባልሰፈነበት ሁኔታ የአገሪቷን #ሰላም፣ ልማት እና ዴሞክራሲ ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ መንግስት ኃላፊነቱን ለመወጣት ከመቼውም ጊዜ በላይ ለህግ የበላይነት #መከበር በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቆም ብለን እናስብ‼️

#ሰውን እንደሰው የሚያከብር ማህበረሰብ ካልተፈጠረ የኢትዮጵያ ችግር መቆሚያ ያለው አይመስለኝም። ዛሬ ለምንሰማቸው አሳዛኝ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ብዙ የሚጠየቁ አካላት ቢኖሩም ዛሬ ያለነው በተለይም ፊደል ቆጥረናል የምንል ሰዎች ስለሰውነት ብዙ መጮኸ አለብን! በምንችለው ቋንቋ ሁሉ ሰው ክቡር መሆኑን ላገኘነው ሰው ሁሉ እንናገር።
.
.
የኢትዮጵያ ችግር ዴሞክራሲ እና ነፃነት ብቻ አይመስለኝም። ሌሎች መሰረታዊ ችግሮች አሉብን! እውነተኛ ዴሞክራሲ እንኳን ቢመጣ እንጠቀምበት ይሆን?? የሚለውም ነገር ያሳስበኛል።
.
.
የሀይማኖት አባቶች፣ መምህራን፣ አርቲስቶች፣ጋዜጠኞች፣ በተለይ በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ አክቲቪስት ነን የምትሉ ሰዎች ሌት ተቀን ለሰው #መከበር ልትሰሩ ይገባል! ሌላው ቀስ ብሎ ይደርሳል። ሰው እንደሰውነቱ ባልተከበረበት ሀገር ስለምንም ነገር ማውራት አይቻልምና።
.
.
ለሰው ክብር የሌለው ግለሰብ፣ ቤተሰብ እንዲሁም ማህበረሰብ የሚፈጠር ከሆነ የዚህች ሀገር እጣፋንታ መጥፎ ሊሆን ይችላል።
.
.
የTIKVAH-ETH ቤተሰቦቻ አሁን ባለነበት ቦታ ሆነን የሰው ፍጡር ምን ያህል ክብር እንዳለው እንነጋገር፣ እንወያይ። በየሀይማኖቶቻችን እና ባለንም እውቀት ለትንንሽ እህት ወንድሞቻችን ስለሰውነት እናስተምራቸው።

ሰው ይከበር!
#ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ደብረፅዮን‼️

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ለሀገርና ለህዝቦች ሉአላዊነት #መከበር እስከ አሁን ያበረከተው አስተዋጽኦ የሚደነቅ መሆኑን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ገለጹ፡፡ ዶክተር ደብረጽዮን ሰባተኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በዚሁ መግለጫቸው እንዳሉት መከላከያ  ሰራዊቱ ለልማትና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ወሳኝ የሆነውን የህገ-መንግስትና የህዝቦች ሉአላዊነት ያለምንም መሽራረፍ እንዲከበሩ  አርአያነት ያለው ተግባር እያከናወነ ነው፡፡

”በተለይም የሀገራችንና ጎረቤት ሀገራት  ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሰራቸው ስራዎች ከሀገራዊ ፋይዳው አልፎ በዓለም አቀፍም አርአያነት ያለው ነው” ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ሃገራት የተፈጠሩ ግጭቶች ለማረጋጋት በተሰማራበት ሁሉ #በድል_ማጠናቀቁ የህዝባዊነቱ እና የዓላማ ፅናቱ ማሳያ መሆኑን  አስታውቀዋል፡፡

የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ለሀገርና ለህዝቦች ሉአላዊነት መከበር ፣ ለፍትህና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላበረከተው አስተዋጽኦ #አድናቆታቸውን በመግለጽ አመስግነዋል፡፡

ዶክተር ደብረጽዮን መከላከያ ሰራዊቱ  የሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ወዳድ ህዝቦች አለኝታ እንደሚሆን በመተማመን የትግራይ ህዝብና መንግስት ከጎኑ  እንደሚቆሙ ማረጋገጣቸውን ለክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የሰጡትን መግለጫ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia