TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
40/60...

ዛሬ የዋለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ፍ/ብሄር ችሎት የ40/60 እቤት እድለኞች(61ሰዎች) ባቀረቡት የጣልቃ መግባት አቤቱታ ላይ በከሳሽ ወገን ሆነው ጣልቃ እንግባ የሚል አቤቱታ ባቀረቡ ሰዎች አቤቱታ ላይና በ3ኛ ተከሳሽ (የአዲስ አበባ ከተማ የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ) የእግድ ይነሳልኝ (ወይም የኪሳራ ገንዘብ ከሳሾች ያስይዙልኝ) አቤቱታ ተመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

#ውሳኔ_1. በ98 ሰዎች (መቶ ፐርሰንት የከፈሉ ተመስጋቢዎች) ክስ የ2ኛ ዙር የ40/60 እድለኞች ላይ የተጣለው እግድ እንዲነሳ ተወስኗል። ነገር ግን በ98 ከሳሾች ልክ 98 ቤቶች ብቻ ታግደው እንዲቆዮ ተወስኗል።

#ውሳኔ_2. በ61 (የ2ኛ ዙር የ40/60 እድለኞች) በክሱ ጣልቃ የእንግባ ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል

#ውሳኔ_3. ሌሎች በከሳሽ ወገን የጣልቃ እንግባ ጥያቄን ውድቅ አድርጓል

#ውሳኔ_4. የከሳሽ ክስ የማሻሻል ጥያቄን ተቀብሏል

Via Housing in Addis Ababa
@tsegabwolde @tikvahethiopia