TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የተኩስ ልውውጡ ምክንያት በአፓርታማው ጠባቂ(ፌደራል ፖሊስ) እና በሌሎች የፌደራል ፖሊሶች መካከል የተፈጠረ #አለመግባባት እንደነበረና በተኩስ ልውውጡም 2 አባሎች #ህይወታቸው ሲያልፍ 4 አባሎች ላይ #ቀላል ጉዳት መድረሱን ኮማንደር ብርሃነ ለetv በስልክ መስመር ገብተው ገልፀዋል። #በነዋሪዎች ላይ የደረሰ ምንም ጉዳት የለም።

ቦሌ መንገድ በሚገኘው የፓርላማ አባላት መኖሪያ አፓርታማ አካባቢ ከሌሊት ጀምሮ በነበረው የተኩስ ልውውጥ የቦሌ መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ መቆየቱ ታውቋል። እንዲሁም ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድም ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ነበር። አሁን ላይ መንገዶቹ መከፈታቸው ተከፍተዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቲቪ (ጤና ይስጥልኝ ኢትዮጵያ), ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእርቀ ሰላም ውይይት ተጀመረ!

በምዕራብ ጎንደር ዞን ነጋዴ ባሕርና አካባቢው የሚኖሩ #የአማራና #የቅማንት ህዝቦች ተወካዮች የእርቀ ሰላም ውይይት ጀምረዋል፡፡ ውይይቱ ነጋዴ ባሕር ከተማ ላይ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡ የእርቀ ሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ያደረጉት ከሁለቱም ወገኖች የኃማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ የውይይቱም ዓላማ አሁን ላይ ያለው #አለመግባባት እንዲያበቃና ወደቀደመው መከባበርና አንድነት ለመመለስ ነው፡፡ የሰዎች ሞትና የንብረት ውድመት እንደማይጠቅምና ተጎጅዎችም ራሳቸው መሆናቸውን ተወያዮቹ ተናግረዋል፡፡

#ከግጭት ይልቅ የቀደመውን #አንድነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡ ‹‹የጥፋቱ መንስኤ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ከሆነ ህግን ተከትሎ መንግስት ሊፈታው ይገባል፤ እኛ ሰላማዊ ነዋሪዎች ነን፤ ሰላማችንን ልንጠብቅ ይገባናል›› ነው ያሉት፡፡ በጥፋቱ የሚጠየቁ ግለሰቦች ካሉም በጋራ ሆነን ተጠርጣሪዎችን ለህግ እንዲቀርቡ እናደርጋለን ብለዋል ተወያዮቹ፡፡

‹‹መንግስት የሚደርሰው ጥፋት ከተከሰተ በኋላ ነው፤ ስለዚህ ለጥፋቱ የድርሻውን ይውሰድ፤ እኛም ችግሩን ወደ ሌላ ሳንገፋ የድርሻችንን ልንወስድ ይገባል›› ብለዋል፡፡ ለዘራፊዎች በራቸውን መክፈት ሳይሆን ሰላማቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡

የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል #አማረ_ገብሩ በውይይቱ ላይ ተገኝተው የሀገር መከላከያ ሰራዊት #ህይዎትን_ለማትረፍ ቅድሚያ እንደሚሰጥ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ ‹‹ሕዝብ ከሌለ ሀገር የለም፤የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚችል መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው አለ፤ ከሕዝብ የምንጠብቀው ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠትና ለችግሮች መፍትሔ መስጠት ነው›› ብለዋል፡፡ ሰራዊቱን ሕዝቡ እንዲደግፈውም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

#በእርቀ_ሰላም ውይይቱ እንዲሳተፉ ከአካባቢው 16 ቀበሌዎች ጥሪ ቀርቦላቸው እንደነበር ተገልጧል፡፡ አብዛኛዎቹ ተሳትፈዋል፤በተለያዩ ምክንያቶች ከሁለቱም ወገኖች ለውይይት ያልተገኙ የቀበሌ ተወካዮችም አሉ፡፡ ሁሉን አቀፍ የጋራ መግባባት እንዲኖር ለማድረግም ለየካቲት 15/2011 ዓ.ም ሕዝባዊ ውይይት ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዞ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹የክህደት ዘመን ላይ ደርሰናል›› ሕወሓት

‹‹ትዕግሥት ሁሌ ስለማይሠራ ዕርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል›› ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል
.
.
የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር #ደብረ ጽዮን_ገብረሚካኤል ‹‹ሕገ መንግሥቱ እየተጣሰ ትዕግሥት የሚባል ነገር ሁሌ አይሠራም፣ ዕርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፤›› ሲሉ ለክልሉ ቴሌቪዥን ተናገሩ፡፡

በአገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ሕገ መንግስቱ የሚጣስበት እና በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠሩ #ጥቃቶች የሚሰነዘሩበት ነው ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ፡፡

ሕወሓት 44ኛ አመት የምሥረታ በዓሉን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ድርጅቱ እና ደጋፊዎቹ የምሥረታ በዓሉን የሚያከብሩት በኢትዮጵያ የተጀመረው ዕድገት ወደ ኋላ እየተቀለበሰ ባለበት ወቅት ነው ብሏል፡፡

ለተጠቀሰው ችግር ዋነኛው መንስኤ የኢሕአዴግ አመራር ውስጥ የተፈጠረው #አለመግባባት እና የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት መሆኑንም መግለጫው ይናገራል፡፡

‹‹የክህደት ዘመን ላይ ደርሰናል›› የሚለው የሕወሓት መግለጫ ትችቱን እንደሚከተለው ያቀርባል፡፡

‹‹በስመ ለውጥ ለአገራቸው ክብርና ሉዓላዊነት መረጋገጥ ዕድሜ ልካቸውን የደከሙና የለፉ የሚረገሙበትና የሚብጠለጠሉበት፣ በአገሪቱ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በዜጎች ላይ የተለያዩ በደሎችና ግፍ የፈጸሙ፣ እንዲሁም የአገራቸውን ሉዓላዊነት አሳልፈው የሰጡ ብቻ ሳይሆን፣ ከሌሎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር አብረው አገርና ሕዝብ የወጉ የሚመሠገኑበትና ክብር የሚሰጥበት የክህደት ዘመን ላይ ደርሰናል፤››

ይሁን እንጂ የአገሪቱ ሁኔታ ሕወሓት ካወጣው መግለጫ በተቃራኒ እንደሆነ በርካቶች ይገልጻሉ።

ከምንጊዜውም የተሻለ ዴሞክራሲ የሰፈነበት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የቆሙበትና ቀደም ሲል ለተፈጸሙ ጥሰቶችም ፍትሕ የተሰጠበት መሆኑን የአገሪቱ የፖለቲካ ልሂቃን፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የተለያዩ የውጭ መገናኛ ብዙኃንና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ በይፋ እየተናገሩ ናቸው።

በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችና የዜጎች መፈናቀል መኖር እርግጥ ቢሆንም፣ የፖለቲካ ሽግግር ከዚህ የፀዳ ሊሆን እንደማይችል ነገር ግን ይህ ችግር እየደበዘዘ መሄድ እንዳለበትና በአሁኑ ወቅትም መረጋጋት መኖሩን ያስረዳሉ።

ሕወሓት በፖለቲካ ማዕከሉ ላይ የነበረው ተፅዕኖ በመቀነሱ የመገፋት ስሜት ሊጫነው እንደሚችል፣ ይኼንንም የሚያባብሱ የፖለቲካ ትግሎች በኢሕአዴግ ውስጥ መቀጠላቸው በግልጽ የሚታይ ቢሆንም፣ ጉዳዩን ከሕዝብ ጋር ማገናኘት ስህተት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ልሂቃን በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ የሚያነሱት ሐሳብ ነው።

የካቲት 13፣ 2011

ምንጭ - ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

"ፀግሽ ባሁኑ ሰአት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ምክንያቱ #ባልተረጋገጠ ጉዳይ ፀጥታው አስጊ ሁኔታላይ ይገኛል። የሚመለከተውም አካል ጉዳዩን አጥንቶ መፍትሔ እንዲያበጅልን።"

ውድ ተማሪዎች እባካችሁ #ከግጭት እና #አለመግባባት ርቃችሁ ለሀገራችሁ ሰላም እና እድገት እንድትሰሩ በTIKVAH-ETH ስም እንጠይቃለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አለመግባባቱ ተፈቷል...ወሎ ዩኒቨርሲቲ‼️

ከቀናት በፊት #በወሎ_ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ በተማሪዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረው #አለመግባባት መፈታቱን የዩኒቨርሲቲው አኃላፊዎችና ተማሪዎች ተናገሩ፡፡ ባለፈው ማክሰኞ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ በከሚሴና አጣዬ አካባቢዎች ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ በዩኒቨርሲቲው በተቀሰቀሰ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱንና ሌሎች መጠነኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው ህክምና ተሰጥቷቸው ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሳቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ዶ/ር #አባተ_ጌታሁን ለዶየቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ በተማሪዎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የዞን ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የተማሪ ተወካዮች ባደረጉት ጥረት ችግሩ መፈታቱንም አስታውቀዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ብርሀኑ አሰፋ እርቅ መፈፀሙን አረጋግጠው የተቋረጠው ትምህርት የፊታችን ሰኞ እንደሚጀመር መናገራቸውን የባህርዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን ዘግቧል፡፡ ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ፕሮግራሞች የሚያስተምራቸው ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎች አሉት፡፡

ምንጭ-የጀመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የባሕር በር ጉዳይ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው " - ኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ? " ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። ከሶማሌላንድ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ከዓላማው ውጪ የሆኑ የተሳሳቱ መረጃዎች ተሰራጭተዋል። የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ሳይሆን…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

" ... ለሶማሊያ በችግር ጊዜ ብዙ ድጋፍ ያላደረጉ #አንዳንድ_ተዋናዮች ራሳቸውን እንደ እውነተኛ ወዳጆቿ አድርገው ለማሳየት እየሞከሩ ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ?

- ኢትዮጵያ ለሶማሊያ #ሰላም እና #ደህንነት ያላትን ቁርጠኝነት በውድ ልጆቿ #ደም እና #ላብ በግልፅ አሳይታለች።

- ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ድንበር ተጋርተው የሚኖሩ ጎረቤቶች ብቻ ሳይሆኑ የጋራ የሆነ ቋንቋ፣ ባህል እና ህዝብ የሚጋሩ ወንድማማች ሀገራት ናቸው።

- ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የሚያስተሳስሩ ጉዳዮች ጠንካራ ናቸው ፤ እጣ ፈንታችን የማይነጣጠል ነው።

- ከሶማሌላንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ለኢትዮጵያ የንግድ ግንኙነት የሚሆን የባህር አገልግሎት የሚሰጥ የትብብር እና አጋርነት ስምምነት ነው። ስምምነቱ በየትኛውም ሀገር ላይ ሉዓላዊነትን የሚጥስ / የሚገዳደር / በግዳጅ የየትኛውንም ሀገር ሉዓላዊነት የሚረግጥ አይደለም።

- እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ለሶማሊያ በችግር ጊዜ ብዙ ድጋፍ ያላደረጉ አንዳንድ ተዋናዮች ራሳቸውን እንደ እውነተኛ ወዳጆቿ ለማሳየት እየሞከሩ ነው። ለዚህ ደግሞ ያነሳሳቸው ለሶማሊያ ያላቸው ወዳጅነት ሳይሆን #ለኢትዮጵያ_ያላቸው_ጥላቻ / የጠላትነት ስሜት መሆኑ ግልጽ ነው።

- እነዚህ ተዋናዮች አጀንዳቸው የአፍሪካ ቀንድ ሰላም ፣ መረጋጋት እና ደህንነት አይደለም። ሊዘሩ የፈለጉት #አለመግባባት እና #ትርምስን ነው። እየታየ ያለው ነገር ውጥረት የሚያባብስ እንዲሁም ደግሞ አጋጣሚውን ለመጠቀም ለሚፈልጉ የውጭ ተዋናዮች ፍላጎት ብቻ የሚያገለግል ነው።

- ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመስረተ ሁሉን አቀፍ ቀጠናዊ ትስስርን ለመፍጠር ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር በትብብር መንፈስ ለመስራት እየጣረች ነው።

- ኢትዮጵያ ውጥረትን ከሚፈጥሩና ከሚያባብሱ መግለጫዎች፣ ንግግሮች እና ትርክቶች ይልቅ ቀጣይነት ያለው ውይይት ማድረግ የተሻለ አማራጭ እንደሆነ በጽኑ ታምናለች።

#AmbassadorRedwanHussien #X

@tikvahethiopia