TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የፈረንሳዩ ኤሊሴይ ቤተ-መንግስት ለውጭ ሀገር ሚድያዎች ዛሬ ያስተላለፈው መልእክት እንደሚጠቁመው የሀገሪቱ ፕሬዝደንት #ኢማኑኤል_ማክሮን ኢትዮጵያን መጋቢት 3 እና 4 ይጎበኛሉ። ጠ/ሚር አብይ ፈረንሳይን ጥቅምት ላይ በጎበኙበት ወቅት ፕሬዝደት ማክሮን ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ጋብዘዋቸው ነበር።

Via Elias Mesert
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የገቢዎች ሚኒስቴር ከጥቅምት እስከ የካቲት ግብራቸውን በታማኝነትና በወቅቱ አለመክፈላቸው በኦዲት ተረጋግጦ ፍሬ ግብሩን ከነአስተዳደራዊ ቅጣትና ወለድ እንድከፍሉ የተወሰነባቸው ከ1 ሺህ 237 ድርጂቶች ላይ 10 ቢሊዮን 134 ሚሊዮን ብር ገቢ እንዲያደርጉ እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ሚስቴር መስሪያ ቤቱ ከንቅናቄው ጋር ተያይዞ በርካታ ግብር ከፋዮች በወቅቱና በታማኝነት ግብራቸውን እየከፈሉ በመሆናቸው የገቢዎች ሚኒስቴር ላቅ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ነገር ግን ለሀገር መግባት የሚገባውን ግበር በማጭበርበር እና በመሰወር ለህግ ተገዥ ባልሆኑ ድረጂቶች ላይ የሚዎስደውን ህጋዊ እርምጃ ከምንጊዜውም በላይ አጠነክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡

ይህ መረጃ በከፍተኛ ማጭበርበር እና ግብር ሥወራ ተጠርጥረው ወደ ፌደራል ፖሊስ የተላኩትን አያካትትም።

ድርጂቶቹ ተስማምተው የሚከፍሉትን ግብር በመክፈል ሂደት ላይ እከገቡ ድረስ ለጊዜው ስማቸውን መግለጽ አስፈላጊ ሆኖ አላገኘነውም፡፡

ዝርዝር የተከናወነውን ሥራ ተከታትለን ለህዝባችን መረጃውን ይፋ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ሀገራዊ ገቢዋ የአደገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ታላቅ የግብር ንቅናቄ በማድረግ ከህዝባችን ጋር በመሆን ከፍተኛ ሥራ እየሰራ ይገኛል፡፡

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብዙ ጊዜ #ቀላል ነው ብለን የተናግርነው አንድ ቃል የሌላውን ሰው #ቅስም ይሰብራል። ያንኮታኩታል። ድባቅ ይመታል። ከአፋችን የሚወጡት ቃላቶቻችን እጅግ ትልቅ ሀይልን የተሞሉ ናቸው። ይህ የቃላት ሀይልም #በመልካምነት ካልተዋጀ ቃላቱን በሚቀበለው ሰው ላይ ትልቅ ችግር ሊፈጥር ይችላል።  ስለዚህ በእያንዳንዱ ካፋችን በሚወጡ ቃላት ላይ !ቁጥብ እንሁን። ከዚህ በፊት ያስቀየምናቸውም ሰዎች ካሉ ዛሬ !ይቅር እንዲሉን ለመጠየቅ ትክክለኛው ጊዜ ነው። ዛሬ ነገ ይቅርታ እጠይቃለሁ ስትል ልዩነታችሁ ይበልጥ እየሰፋ ይሄዳል። ማስተካከልም የሚከብድበትና የማይቻልበት ሁኔታ ላይም ይደርሳል። አንተ ግን ዛሬ ትልቅ እድል አለህ። በአንድ የአፍ ወለምታ ያስቀየምከውን ሰው ዛሬ ይቅርታ ለመጠየቅና በድጋሚ ጓደኝነታችሁን ለመቀጠል ዛሬን በህይወት ኖረህ ሌላ እድል ተሰቶሀል። ይህንን እድልህን ይቅርታ በመጠየቅ አሳልፈው። ውስጥህንም ሲረብሽህ የነበረውን የሁልጊዜ ሀሳብ ከላይህ ላይ ተገላገለው።  ይቅርታ መጠየቅ የበታች አያደርግም። ይቅርታ መጠየቅ መዋረድ አይደለም። ጥፋትን አውቆ ይቅርታ መጠየቅ ትንሽ መሆን አይደለም ትልቅ መሆን እንጂ!

Via ብሩክ የሺጥላ
@tsegabwolde @tikvahethipia
#update ትላንት ማምሻውን ለፕሬዝዳንት #ኡሁሩ_ኬንያታ በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ ፕሬዚዳንቱ በንግግራችው አዲስ አበባ #የኬንያኖችም የሁሉም ከተማ መሆንውን ገልጸዋል። በተያያዥነትም የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት #እንደሚደግፉ ገልጸው የኬንያ ባለሀብቶች በገበታ ለሸገር ከጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና #ኢትዮጵያዊያን ጎን እንደሚቆሙ #ቃል_ገብተዋል

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikbahethiopia
Forwarded from Venture Addis (Nati Girma)
እንኳን ለ123ኛው የአድዋ በዐል በሰላም አደረሳችሁ! #ቀዳማዊ @VentureAddis
ኢትዮ ቴሌኮም ለምን ለአድዋ ድል በአል የ "እንኳን አደረሳችሁ" መልእክት ዘንድሮ አላደረስክም ሲባል መልሱ "መሸብኝ" ሆነ!

Via Eliyas Mesert
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ ጥዋት ኤርትራ #አስመራ ገብተዋል። መሪዎቹ አስመራ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የክልሎች የጋራ ምክክር መድረክ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ እየተካሄደ ነው። በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት የሚካሄደው የምክክር መድረኩ ትኩረቱን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረገ መሆኑ ነው የተገለፀው። በጋራ የምክክር መድረኩም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂምን እና ሌሎች የሚመለከታቸው የክልልና የፌዴራል መንግስት ተወካዮች ተገኝተዋል።

Via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"መንገድ ለሰው" - ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን አዲስ አበባ-#CarFreeDayEthiopia

ፎቶ፦ samy(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia