TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን የፊታችን መጋቢት ወር ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ
አስታወቁ። ፕሬዚዳንት ማክሮን ኢትዮጵያን የሚጎበኙት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት መሆኑም ታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የፕሬዝዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን መንግስት በነዳጅ ላይ ተጨማሪ ቀረጥ አስከትሎ በፓሪስና አካባቢዋ ሰዎች ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ የፈረንሳይ መንግስት በፓሪስ ከተማ ብቻ 8 ሺህ የፖሊስ አባላትን አሰማርቶ አመፁን ለማስቆም ያደረገው ጥረት ብዙም ውጤታማ አልሆነም ተብሏል፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ብቻ ፓሪስ ውስጥ በሰልፈኞች በፖሊሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከ135 በላይ ሰዎች #ቆስለዋል፡፡

ምንጭ፦ ሲ ኤን ኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፈረንሳይ‼️

ተቃውሞ የበረታባቸው የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ዝቅተኛ ወርሃዊ የደመወዝ ጣሪያ በ100 ዩሮ እንዲያድግ ወሰኑ።

ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን ዝቅተኛ የወር ደመወዝ ጣሪያ በ100 ዩሮ እንዲጨምር መወሰናቸውን ትናንት በቴሌቪዥን ባደረጉት ብሄራዊ ንግግር ይፋ አድርገዋል።

የፓሪስና ሌሎችም ከተሞች ጎዳናዎች “ቢጫ ሰደርያ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለሳምንታት አስተናግደዋል።

የፈረንሳይ መንግስት በነዳጅ ሽያጭ ላይ ታክስ ለመቁረጥ መወሰኑን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አቅጣጫውን የመንግስትን ፖሊሲዎች ወደ መቃወም ቀይሯል።

ማህበራዊ እና ኢኮኖያዊ ፍትህ የለም ያሉት የሀገሪቱ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ግብግብ ሲገጥሙ ተስተውሏል።

ትናንት ምሽት በቴሌቪዥን ቀርበው ብሔራዊ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ማክሮን ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ ዝቅተኛ የደመወዝ ጣሪያ በ100 ዩሮ እንደሚጨምር ተናግረዋል።

ከመደበኛ የስራ ሰዓት በተጨማሪ በሚሰሩ ስራዎች ከሚገኝ ገቢ ታክስ እንዳይቆረጥ እንደሚደረግ ቃል ገብተዋል።

ከ2 ሺህ ዩሮ በታች ጡረታ ከሚያገኙ ሰዎች የሚቆረጠው የማህበራዊ ዋስትና ክፍያ ጭማሪ እንዲሰረዝ መወሰናቸውን ጠቁመዋል።

የፈረንሳይ መንግስት በነዳጅ ላይ ሊጥል የነበረውን የግብር ጭማሪ ባሳለፍነው ሳምንት መሰረዙ ይታወቃል።

በፈረንሳይ የተቀቀሱ ተቃውሞዎችን 84 በመቶ ዜጎች (በብዛት መካከለኛ ገቢ ያላቸው ቡድኖች) እንደደገፏቸው የዳሰሳ ጥናቶች ያሳያሉ።

ማክሮን በንግግራቸው የግል ቀጣሪዎችም ከቻሉ ለሰራተኞቻቸው ዓመታዊ ቦነስ (ማበረታቻ ክፍያ) እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

ላለፉት አንድ ዓመት ተኩል በሌሎች ጉዳዮች ላይ በማተኮራችን ለዜጎቻችን ትኩረት አልሰጠንም፤ ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ ዜጎቻችንን የሚጠቅሙ ማህብራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን የሚፈጥሩ ስራዎችን እንሰራለን ነው ያሉት።

በፈረንሳይ ለአራት ሳምንታት የዘለቀው አውዳሚ ተቃውሞ በኢኮኖሚዋ ላይ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ ማድረሱና ለሰዎች ህይወት ህልፈት ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

ምንጭ፦ሮይተርስና አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፈረንሳዩ ኤሊሴይ ቤተ-መንግስት ለውጭ ሀገር ሚድያዎች ዛሬ ያስተላለፈው መልእክት እንደሚጠቁመው የሀገሪቱ ፕሬዝደንት #ኢማኑኤል_ማክሮን ኢትዮጵያን መጋቢት 3 እና 4 ይጎበኛሉ። ጠ/ሚር አብይ ፈረንሳይን ጥቅምት ላይ በጎበኙበት ወቅት ፕሬዝደት ማክሮን ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ጋብዘዋቸው ነበር።

Via Elias Mesert
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሟቾቹ ጥቂቱ፦

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሮቶኮል ሻሀድ አብዲሻኩር በአውሮፕላን አደጋው ከሞቱት አንዱ መሆኑን ራዲዮ ዳልሰን ተብሎ የሚጠራው የሶማሊያ የግል ሚዲያ ዘግቧል።

ከዚህ በተጨማሪ የስሎቫኪያ የፓርላማ አባል ሚስቱንና ልጁን አጥቷል። የስሎቫክ ናሺናል ፓርቲ አባል የሆነው የፓርላማ አባል አንቶን ሄርንኮ ፌስቡክ ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት ባለቤታቸውና ሁለት ልጆቻቸው በአደጋው እንዳጡ ገልፀዋል።

የምግብና መስተንግዶ ድርጅት ታማሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ #ጆናታን_ሴክስ በአደጋው ከሞቱት መካከል አንዱ ናቸው። በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ብዙ ቁጥር ያላቸው ሬስቶራንቶች ባለቤት የሆነው ይህ ድርጅት የህልፈታቸውን ዜና ያሳወቀው በፌስቡክ ገፁ ነው።

በጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቤተሰብ፣ ዘመድና ወዳጆቻቸውን እየጠበቁ ለነበሩም የህልፈታቸው ዜና ተነግሯቸዋል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ የሶስት ሟቾችን በትዊተር ገፁ ላይ ያሰፈረ ሲሆን ከቤተሰቦቻቸውም ጋር ለመገናኘት ጥረት እያደረገ እንደሆነ ገልጿል።

#የአልጀዚራ_ጋዜጠኛ በትዊተር ገጿ እንዳሰፈረችውም የተባበሩት መንግስታት መልእክተኞች ከሟቾቹ መካከል ናቸው።
የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ ስብሰባ በኬንያ መዲና ናይሮቢ ለመካፈል ሲጓዙ እንደነበር ተገልጿል። በዚህ ስብሰባ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ላልይበላ🔝

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን ለሥራ ጉብኝት ዛሬ #ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው የኢትዮጵያ ቆይታ የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚጎበኙ ታውቋል። የላልይበላ ነዋሪዎችም ኢማኑኤል ማክሮንን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ እና ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እየጎበኙ ነው፡፡

Via ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ቤታችን እየነደደ ነው” ኢማኑኤል ማክሮን

ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን እና መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ላይ ለተነሳው ሰደድ እሳት አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያስፈልገው ገለጹ። መሪዎቹ በአማዞን ደን ለተነሳው እሳት አስቸኳይ መፍትሄ መስጠትና ጉዳዩ በቡድን ሰባት ሃገራት ስብስባ ላይ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል። ማክሮን ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰው፥ በትዊተር ገጻቸው ላይ “ቤታችን እየነደደ” ነው ሲሉ አስፍረዋል። የአማዞን ህልውና የዓለማችን አንገብጋቢው ጉዳይ ነው ሲሉም የሁኔታውን አሳሳቢነት ገልጸውታል።

ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ትኩረትን ይሻል የሚሉት ማክሮን ሃገራቸው በምታስተናግደው የቡድን ሰባት አባል ሃገራት ስብሰባ ላይም አጀንዳ ሊሆን እና አስቸኳይ መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባም ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብራዚል በተለይም በአማዞን ክልል የሚነሳው የእሳት አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን መረጃዎች ያመላክታሉ።

በደኑ ከቀናት በፊት የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም አድማሱን እያሰፋ ከፍ ያለ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።
የአየር ንብረት ለውጥ ተቆርቋሪዎች ደግሞ ለተነሳው እሳት የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮን ይወቅሳሉ። ፕሬዚዳንቱ ገበሬዎችና ከደን ውጤቶች የጣውላ ምርት አምራቾች ደኑን እንዲጨፈጭፉ ፈቅደውላቸዋል በሚል ትችቱ በርትቶባቸዋል። እርሳቸው ግን ውንጀላውን ያስተባብላሉ፤ የማክሮንን አካሄድም “በብራዚል ጉዳይ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የታለመ” በሚል አጣጥለውታል።

Via #ቢቢሲ/#fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዚዳንት ማክሮን በኮቪድ-19 ተያዙ።

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ዛሬ ጠዋት ይፋ አድርጓል፡፡

ማክሮን ምልክቶችን ካሳዩ በኋላ ባደረጉት ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ነው ጽ/ቤቱ የገለጸው፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ለ ሰባት ቀናት ራሳቸውን እንደሚያገሉም ስካይ ኒውስን ዋቢ አድርጎ #አልዓይን ዘግቧል፡፡ ይሁንና ፕሬዜዳንቱ ስራቸውን እንደሚቀጥሉ ተገልጿል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia