TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Shire #Axum #Mekelle

በሽረ ከተማ ህዝቡ ወደመረጋጋት እና ወደቀደመው ህይወቱ እየተመለሰ መሆኑን ዶ/ር ሙሉ ነጋ (የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ) ለኢቲቪ ተናገሩ።

የወረዳ ፣ የቀበሌ ስራ አስፈፃሚዎች ተመርጠዋል ፤ ወደ ስራም ገብተዋል ብለዋል።

በተመሳሳይ በአክሱም ከተማ የወረዳና የቀበሌ አደረጃጀቶች ተዘርግተዋል ፤ እንቅስቃሴም እንደተጀመረ ገልጸዋል።

መቐለ ከተማ በሚመለከት አሁን ላይ ከተማው ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር እንደሆነና ሰላማዊ ሁኔታ እንዳለ ዛሬ ከመቐለ ከተማ ሆነው አሳውቀዋል።

ህዝቡ ወደስራው እንዲመለስ ፣ በስጋት ከከተማው ሸሽቶ የወጣም እንዲገባ ጥሪ ቀርቧል።

በሌላ በኩል በመቐለ ከተማ የህዝቡ ስጋት ዝርፊያ እንደሆነና ይህም ዝርፊያ እንዲቆም ጥያቄ እንዳቀረበ አንስተዋል ፤ ዝርፊው በቡድን በመደራጀት የሚፈፀም እንደሆነም ዶክተር ሙሉ ገልፀዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከፌዴራሉ መንግስት ጋር በመነጋገር በፍጥነት ይህ ሁኔታ መፍትሄ እንዲያገኝ እየሰራ እንደሆነ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Shire

18,200 ኩንታል የምግብ አቅርቦት የጫኑ 44 ከባድ የጭነት መኪኖች በትላንትናው ዕለት ሽረ እንደገቡ የሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ ክፍፍሉ በሽረ እና በአቅራቢያው ባሉ ቦታዎች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Shire

የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰኞ ምሽት በትግራይ ሽረ ከተማ ተፈናቃዮች ከሚገኙበት አራት ካምፖች ከ500 በላይ ወጣት ወንዶችና ሴቶች በግዳጅ ይዘው መወሰዳቸውን 3 የእርዳታ ሰራተኞች እና አንድ ዶ/ር እንደነገሩት ሮይተርስ አስነብቧል።

የእርዳታ ሰራተኞቹና ዶክተሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኪናዎች ላይ ተጭነው ተወስደዋል ሲሉ ፤ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ተናግረዋል።

ከእርዳታ ሠራተኞች መካከል አንዱ ፥ በርካታ ወንዶች ተደብድበዋል ፣ ስልካቸው እና ገንዘባቸው ተወስዷል ብለዋል።

በአንዱ ካምፕ ውስጥ የሚኖር ክስተቱ በተፈፀመበት ወቅት የተደበቀ አንድ ግለሠብ ወታደሮች ሰብረው ገብተው ሰዎችን በዱላ መደብደባቸው ተናግሯል።

ይኸው ስሙ በሚስጥር እንዲያዝ የጠየቀው ግለሰብ ፥ ወታደሮች በምሽት መጥተው ካምፑን በመክበብ ዋናውን በር በመስበር ያገኙትን ሁሉ በዱላ መደብደብ እንደጀመሩ ገልጾ በወቅቱ የ70 ዓመት አዛውንት መደብደባቸውን እና አንድ አይነስውር አፍነው መውሰዳቸውን ተናግሯል።

እሱ ካለበት ፀሃዬ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ 400 ሰዎች መወሰዳቸውን አስረድቷል።

የመከላከያ ቃል አቀባይ፣ የትግራይ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡበት መልዕክት ቢቀመጥላቸውም ምላሽ አልሰጡም ብሏል ሮይተርስ።

የሰሜን ምዕራብ ዞን ጊዜያዊ ኃላፊ ቴዎድሮስ አረጋይ ፥ ጥቂት መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መወሰዳቸውን አረጋግጠዋል።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ክሱን የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፕሮፖጋንዳ ነው ሲሉ አጣጥለውታል።

ያንብቡ : telegra.ph/Shire-05-25

@tikvahethiopia