TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም‼️

ኢትዮ ቴሌኮም ያለፉት ስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ክንውኑን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፥ በስድስት ወራት ውስጥ 20 ነጥብ 86 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ 16 ነጥብ 71 ቢሊየን ብር ማግኘቱን #አስታወቀ። ይህም የእቅዱን 80 ነጥብ 1 በመቶ መሆኑን በመግለጫው አመላክቷል።

ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት የተጠቃሚውን #ፍላጎት ለማሟላት የሚያግዙ የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች መስራቱንም ጠቅሷል። በዚህም በቴሌኮም አገልግሎት ላይ ቅናሽ በማድረግ ተጨማሪ ተጠቃሚዎችን የማፍራትና ደንበኞች አገልግሎቱን በብዛት እንዲጠቀሙ የማድረግ ስራዎች ተሰርተዋል ነው ያለው።

ከዚህ ባለፈም የአገልግሎት ጥራት ላይ የማሻሻያ ስራዎች መስራቱንም በመግለጫው አንስቷል። በስድስት ወራት ውስጥም የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚዎችን 44 ነጥብ 91 ሚሊየን ለማድረስ ታቅዶ 41 ነጥብ 1 ሚሊየን አፈጻጸም በማሳየት፥ የእቅዱን 91 ነጥብ 5 ማሳካት መቻሉንም ነው ያነሳው።

ከዚህ ውስጥ የሞባይል 39 ነጥብ 54 ሚሊየን፣ ዳታና ኢንተርኔት 426 ሺህ፣ መደበኛ ስልክ 1 ነጥብ 14 ሚሊየን እንዲሁም የዳታ እና የኢንተርኔት ተጠቃሚ ብዛት 19 ነጥብ 49 ሚሊየን ደርሷል ብሏል።

የቴሌኮም ሽፋኑም አሁን ላይ 43 በመቶ የደረሰ ሲሆን፥ በስድስት ወራት ውስጥ 4 ነጥብ 17 ሚሊየን ደንበኞች ጥሪ አድርገዋል።

በሰጠው አገልግሎትም 16 ነጥብ 71 ቢሊየን የሰበሰበ ሲሆን፥ ሞባይል 63 ነጥብ 2 በመቶ፣ ዳታ እና ኢንተርኔት 18 ነጥብ 7 በመቶ እና አለም አቀፍ ጥሪዎች 5 ነጥብ 5 በመቶ ድርሻ አላቸው።

ካገኘው ገቢ ውስጥም ያልተጣራ ትርፍ 11 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ሲሆን ይህም የእቅዱን 91 በመቶ መሆኑንም ገልጿል።

ከማሻሻያ ስራዎች ጋር በተያያዘም የተንቀሳቃሽ ስልክ ጥሪ የመገኘት አቅም 91 ነጥብ 33 ሲሆን፥ የአዲስ አበባ 98 ነጥብ 49 እንዲሁም የክልሎች ደግሞ 88 ነጥብ 47 መሆኑም ተነስቷል።

የጥሪ መውደቅ ወይም አለመሳካት መጠን ደግሞ 0 ነጥብ 57 በመቶ ሲሆን የኢንተርኔት አገልግሎት የመገኘት መጠን 97 ነጥብ 12 በመቶ ሆኗል።

በስድስት ወራት ውስጥ የፋይበር መስመር መቆራረጥ፣ የቴሌኮም ማጭበርበር፣ የሃይል መቆራረጥ እና የሰው ሃይል አቅም ውስንነቶች የተቋሙ ተግዳሮቶ ነበሩ ተብሏል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በክቡር የኢፌድሪ ጠ/ሚንስተር #አብይ_አህመድ(ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሊተገበር የታቀደው የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክትን ለመደገፍ የቻይና መንግስት #ፍላጎት እንዳለው ገለፀ፡፡ ለዚህም የቻይና መንግስት የባለሞያ ልዑካን ቡድን የከተማ አስተዳደሩ የጀመረውን የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክትን በገንዘብ እና የቴክኒክ ዕገዛ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ከኢ/ር #ታከለ_ኡማ ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል፡፡ በዚህም የቴክኒክ ቡድኑ የቻይና መንግስት ፕሮጀክቱን የሚደግፍበት ሁኔታ ላይ ጥናት የሚያደርግ ይሆናል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቲክቶክ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት " ቲክቶክ " የተሰኘውን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ሊያግድ የሚችል አዋጅ አጸደቀ። አዋጁ የቻይናው #ባይትዳንስ_ኩባንያ ንብረት የሆነው " ቲክቶክ " በስድስት (6) ወራት ውስጥ አክሲዮኖችን #ለአሜሪካውያን ካልሸጠ በመላው አሜሪካ ይታገዳል ብሏል። ይህ አዋጅ በሴኔቱ ጸድቆ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ካልተፈረመበት ህግ ሆኖ ተፈጻሚ አይሆንም ተብሏል። ፕሬዝዳንት…
#ቲክቶክ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዓለም ላይ ትልቅ ተፅእኖ የፈጠረው በቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ የሚተዳደረው " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ በአሉታዊም ይሁን አውንታዊ መንገድ ስሙ ይነሳል።

በቻይና ያለው የቲክቶክ ይዘት እና በተቀረው ዓለም ያለው ልዩነት አለው የሚሉም ብዙ ናቸው።

አንዳንድ ሀገራት ልጆች እና ወጣቶችን ከአጉል ባህል ለመጠበቅ በሚል በሙሉ ሲያግዱት ፣ አንዳንዶች ደግሞ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ከመንግሥት ቁሳቁሶች ፣ ከመ/ቤቶች አግደዋል።

ለመሆኑ ቲክቶክ በቻይና እና በተቀረው ዓለም ይለያያል ?

ትሪስታን ሃሪስ ፤ የቀድሞው የጉግል ሰራተኛ እና ለማህበራዊ ሚዲያ ስነምግባር ተሟጋች ሲሆኑ ፤ በቻይና ያለው የቲክቶክ ይዘት እና በተቀረው ዓለም ያለው ይዘት ልዩነት አለው ባይ ናቸው።

ዶዪን የቻይናው ቲክቶክ ልጆችን / ትውልድ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

" የመተግበሪያው ባለቤቶች ቴክኖሎጅ በልጆች እድገት ላይ ያለው ተጽዕኖ በደንብ አድርገው የተገነዘቡ ናቸው " የሚሉት እኚሁ የማህበራዊ ሚዲያ ስነምግባር ተሟጋች ፤ " በቲክቶክ የሀገር ውስጥ (ቻይና) ስሪታቸው ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ፦
* በቤት ውስጥ ሊያደርጓቸው የሚችሏቸው የሳይንስ ሙከራዎችን፣
* የሳይንስ እና ሌሉች ሙዚየም ኤግዚቢቶችን
* የሀገር ፍቅር ቪዲዮዎችን፣
* ትምህርታዊ የሆኑ ቪዲዮዎችን ያሳያሉ " ብለዋል።

እንዲህም ሆኖ እራሱ በሀገሪቱ ያሉት ታዳጊዎች / ልጆች በቀን ውስጥ በቲክቶክ ላይ የሚያጠፉት ሰዓታቸው የተገደበ መሆኑንም አንስተዋል።

በዩኤስ እና ቻይና በታዳጊዎች ላይ አንድ የተደረገ ጥናት እንደነበር የሚያነሱት ተሟጋቹ ይኸውም " ወደፊት የምትፈልጉት የምኞት ስራ ምንድን ነው ? " የሚል እንደሆነ በዚህም ውጤቱ ፦
- በዩኤስ ውስጥ ቁጥር 1 የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ፤
- በቻይና ደግሞ ቁጥር 1 #የጠፈር_ተመራማሪ የሚል እንደነበር ገልጸዋል።

ከዚህ ወራት በፊት የቲክቶክ ዋናው ስራ አፈፃሚ በአሜሪካ ኮንግረስ ቀርበ ጠንካራ ጥያቄ በቀረበባቸው ወቅት አንዱ የተነሳው ፤ በቻይና ያለው ቲክቶክ ለልጆች የሚያስተዋውቀው ፦
° ሳይንስ
° የሒሳብ / ሌሎች የትምህርት ቪድዮዎችን ነው ፤ የሚያዩበት / የሚቆዩበት ሰዓትም ገደብ አለው ዩኤስ ውስጥ ግን የሚገፉት ቪድዮዎች ልጆች ራሳቸውን እንዲጎዱ የሚያደርግ ነው ይህ ለምን ? የሚል ነበር።

ቲክቶክ ሱስ የማስያዝ አሰራር እንዳለው የሚያነሱ ሌሎች ባለሞያዎች የሰዎችን ስሜት በማንበበ ረጅም ጊዜ እዛ ላይ እንዲያሳልፉ ያደርጋል ባይ ናቸው።

ለታዳጊዎ/ልጆች ተብሎ የተለየ ስሪት ስለሌለው ይተቹታል።

በቲክቶክ ላይ የመቆያ ጊዜ እንደ #ፍላጎት እና ያልተገደበ መሆኑም በተለይ ለወላጆች ፈተና እንደሆነ ያነሳሉ።

ምንም እንኳን በተለይ #አሜሪካውያኑ እያደረሰ ነው የሚሉት የማህበራዊ ተፅዕኖው እንዳለ ሆኖ ከደህንነትና ከቻይና ጋር ባላቸው ሁኔታ እንዲታገድ ወይም ድርሻ #እንዲሸጥላቸው በይበልጥ ቢፈልጉም በርካቶች በትውልድ ላይ ቀውስ እየፈጠረ ነው ፣ ቁጥጥርም የለው በሚል እንዲታገድ / የይዘት ቁጥጥር እንዲደረግበት ይፈልጋሉ።

ከዚህ በተቃራኒው ቲክቶክ በዩኤስ ሆነ በሌላው ዓለም የበርካታ ወጣቶችን ህይወት በገንዘብ ቀይሯል።

በርካቶችን ለብዙሃን አስተዋውቋል። ብዙ ገንዘብ እንዲሰሩም አድርጓል። አልጎሪዝሙ በትንሽ ድካምና ስራ ሚሊዮኖች ጋር ማድረስ መቻሉ ሰዎች በአንድ ሌሊት ብቻ የዝና ማማ ላይ ቁጭ እንዲሉ አድርጓል።

ከደህንነት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ሰፊ ጉዳዮች አስተዳዳሪዎቹ የተጠቃሚዎችን ምንም መረጃ ለቻይና መንግሥት አሳልፈው እንደማይሰጡ ደጋግመው ተናግረዋል። ሌሎች ወቀሳዎችንም አጥብቀው ይሞግታሉ።

@tikvahethiopia