TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

#የህዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤት መስሪያ ቤቶች የጤና ተቋማትና የወጣቶች መዝናኛ በሚገኙባቸው አከባቢዎች 100 ሜትር ርቀት ውስጥ #ማጨስ የሚከለክልን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጸደቀ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከአልኮል መጠጦች ጋር በተያየዘም ከ21 አመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች አልኮል #መሸጥ የሚከለክለውንም ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምጽ #አጽድቋል፡፡

ማንኛውንም #የአልኮል_ምርት በብሮድካስት ሚድያ #ማስተዋወቅ የሚከለክለውን ረቂቅ አዋጅ ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የአሜሪካ ምክር ቤቶች የጆ ባይደንን የምርጫ ውጤት አረጋገጡ።

የሁለቱ ምክር ቤት እንደራሴዎች የተሰጡትን የውክልና ድምጾች (ኤሌክቶራል ቮት) በመቁጠር ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን አረጋግጧል።

ኮንግረስ ጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካማላ ሀሪስን የቀጣዮቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት በማድረግ ያገኙትን ድምጽ #አጽድቋል

የተሰጡት የውክልና ድምጾች የጸደቁት የሁለቱ ምክር ቤት ተወካዮች በፔንሰልቫንያ እና አሪዞና ግዛቶች የቀረበውን ተቃውሞ ውድቅ ካደረጉ በኋላ ነው።

የአገሪቱ ሕዝብ እንደራሴዎች ተሰብስበው ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የምርጫ ውጤት ዙሪያ በመነጋገር ላይ ሳሉ በድንገት በሺህ የሚቆጠሩ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ምክር ቤቱን ሰብረው ገብተው ነበር።

በዚህ የተነሳ ተቋርጦ የነበረው የምክር ቤቶቹ የጋራ ስብሰባ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ቀጥሏል።

ዋሺንግተን ውስጥ የተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የአገሪቱን ምክር ቤት ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ በተፈጠረ ፍጥጫ 4 ሰዎች ሞተዋል።

በተቀሰቀሰው ግርግር ሳቢያ የዋሺንግተን ከንቲባ በከተማዋ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥለዋል።

የካፒቶል ሂል አካባቢም ሙሉ በሙሉ ዝግ እንዲሆን ተደርጓል። ~ BBC

@tikvahethiopiaBot
#TikTok #USAHouse

የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ተሰብስቦ ለዩክሬን ፣ ለእስራኤል እና ለሌሎች የባህር ማዶ የአሜሪካ አጋሮች የ95 ቢሊዮን ዶላር (5,419,427,000,000 ብር) የእርዳታ ጥቅል/ፓኬጅ ረቂቅ ሕግ አጽድቋል

" ቲክቶክ " በአሜሪካ እንዲታገድም ድምጽ ሰጥቷል።

የተወካዮች ምክር ቤቱ በመጀመሪያ ድምፅ የሰጠው በ " #ቲክቶክ " ጉዳይ ሲሆን ባለቤትነቱ የባይትዳንስ የሆነው መተግበሪያ ለአሜሪካ ኩባንያ ካልተሸጠና ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት ካላቋረጠ በመላው አሜሪካ ውጤታማ በሆነ መንገድ #ለማገድ 360 ለ 58 በሆነ ድምጽ ረቂቅ ሕግ #አጽድቋል

" ቲክቶክ " በአሜሪካ ከ170 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት።

በመቀጠል ምክር ቤቱ ፦

➡️ ለዩክሬን 60.8 ቢሊዮን ዶላር (3,422,796,000,000 ብር)፤

➡️ ለእስራኤል 26.4 ቢሊዮን ዶላር  (1,483,211,600,000 ብር)፤

➡️ ለታይዋን እና ለኢንዶ ፓስፊክ ሀገራት  ' ቻይናን ለሚጋፈጡ ' የ8 ቢሊዮን ዶላር (456,372,800,000 ብር) የእርዳታ ድጋፍ በድምሩ የ95 ቢሊዮን ዶላር ጥቅል እርዳታ ረቂቅ ሕግ አጽድቋል

የምክር ቤቱ አባላት የዩክሬን ድጋፍ ሲጸድቅ ፤ " ዩክሬን !! " እያሉ በመጮህ የሀገሪቱን ባንዲራ ሲያውለበልቡ ታይተዋል።

@thiqahEth @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሕዝብ_በዓላት_እና_የበዓላት_አከባበር_ረቂቅ_አዋጅ_.pdf
#Update

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ #አጽድቋል

ረቂቅ አዋጁ የተወሰኑ ማስተካከያዎች እንደተደረጉበት ተመላክቷል።

አዋጁ በ1 ድምፀ ተቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ " አዋጅ ቁጥር 1334/2016 " ሆኖ ነው የጸደቀው።

የጸደቀው አዋጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት ሲሆን ፤ ክልሎች በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ህግ አውጥተው በክልል ደረጃ የሚከበሩ አዋጆችን አከባበር መወሰን ይችላሉ ተብሏል።

ይህ የሚመለከተው እንደ ኢሬቻ፣ ጊፋታ፣ ጨምባላላ፣ አሸንዳ ፣ ሻደይ ፣ አሸንድዬ ፣ ...ሌሎችንም ሲሆን ክልሎች በራሳቸው አዋጆችን አውጥተው አከባበሩን መወሰን እንደሚችሉ ተመላክቷል።

https://t.iss.one/tikvahethiopia/87926

@tikvahethiopia